Vehicle rental
የካፋ ዞን ፋይናንስ መምሪያ በ2019 በጀት ዓመት በዞን ማዕከል ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ እቃዎች መግዛት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ/ግ/ጨ/ ቁጥር 02/2019
የካፋ ዞን ፋይናንስ መምሪያ በ2019 በጀት ዓመት በዞን ማዕከል ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ
- ሎት 1 ለካፋ ዞን ግብርና መምሪያ ከተለያዩ ቦታዎች የጭነት አገልግሎት መኪና ኪራይ አገልግሎት
- ሎት 2. ለካፋ ዞን ፖሊስ መምሪያ ከፍተኛ የፖሊስ አመራሮች 13 ሰውን የመጫን አቅም ያለው የህዝብ ማመላለሻ መኪና ኪራይ አገልግሎት
- ሎት.3.ለሴክተር መ/ቤት ለደንብ ልብስ ተጠቃሚዎች ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ እና
- ሎት -4- ለካፋ ዞን ሥራና ክህሎት መምሪያ የቢሮ ኪራይ አገልግሎት ግዥዎችን በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ተጫራቾች በመጋበዝ እንደሚከተለው እስከ በጀት ዓመቱ ማብቂያ ማለትም እስከ ሰኔ 30 ቀን 2019 ዓ.ም ግዥን ለማወዳደር ይፈልጋል።
ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች፡-
- ከሎት ከ1 እስከ 4 ድረስ ላሉት በዘርፉ ተጫራቾች የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ፣ በጨረታ ላይ እንዲሳተፉ ከገቢዎች ባለስጣን የተሰጠ የምስክር ወረቀት ማስረጃ ፣ የቫት፣ የቲን፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት እና ሌሎች መረጃዎች ፎቶ ኮፒ አያይዞ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች ከላይ የተጠቀሱትን መረጃዎች የጨረታ ዶክመንት ሊገዙ ሲመጡ ኦርጅናሉን እና የማይመለስ ፎቶ ኮፒ አቅርበው እንዲመሳከር የማድረግ ግዴታ አለባቸው። በመሆኑም ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 500.00 /አምስት መቶ ብር/ ካፋ ዞን ገቢዎች ባለስልጣን ቅ/ጽ/ቤት ቀርበው በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት ለተከታታይ 15 ቀናት ካፋ ዞን ፋይናንስ መመሪያ ግዥ ንብ/አስ/ር ዳይሬክቶሬት በመቅረብ መግዛት ይችላሉ ።
- ለእያንዳንዱ ሎት ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ C.PO (Certified payment order) በጥሬ ገንዘብ እና በቼክ ብር 80,000.00 / ሰማኒያ ሺህ ብር/ በካፋ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ግዥ ክፍያ ንብ/አስ/ ስም በማሰራት ከጨረታው ሰነድ ጋር በማዘጋጀት አያይዞ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ ሠነዱ ላይ በመጻፍ በሰም/በሙጫ/ በታሸገ ኤንቨሎፕ
- ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15 ተከታታይ ቀናት በካፋ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ግዥ ንብ/አስ/ በመቅረብ ለዚሁ ሥራ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
- የጨረታው ሳጥን በ16ኛው ቀን በ3፡30 ሰዓት ታሽጎ በዚያው ዕለት ከጠዋቱ 4:00 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በካፋ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ይከፈታል። የጨረታ መዝጊያ እና መክፈቻ ቀን ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል። በመክፈቻው ዕለት የተጫራቾች ወይም ህጋዊ ተወካዮች ያለመገኘት የጨረታ መክፈት ሂደት አያስተጓጉልም። 15 ተከታታይ ቀናት የተባለው ቅዳሜና እሁድ ጨምሮ የሚቆጠር ነው።
- አሸናፍው ድርጅት ከላይ በሎት የተዘረዘሩትን ሎት 1. ፣ ሎት -2- እና ሎት -4- በስተቀር ሌሎች ሎቶችን ዕቃዎች በሙሉ በራሱ ወጪ ካፋ ዞን ፋይናንስ መምሪያ አቅርቦ የማስረከብ ግዴታ አለበት።
- ተጫራቾች አሰሪው መ/ቤት ያዘጋጀውን የቴክኒካል ዶክመንት መጠይቅ ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።
- ተወዳዳሪዎች ጨረታ ለማስገባት ሲመጡ ሎት 1. ፣ ሎት -2- እና ሎት -4- በስተቀር ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች በሙሉ ናሙና ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን ናሙና ያላቀረበ ተወዳዳሪ ድርጅት ዋጋው አይታይለትም።
- ተጫራቾች ያሸነፉበትን የጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ ለማስያዝ ፈቃደኛ መሆን አለባቸው።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 047 331 1826 እና 047 331 2484
በመደወል መጠየቅ ይቻላል።
ካፋ ዞን ፋይናንስ መምሪያ
Tender details
- Deadline: 2026-08-17
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን በ3፡30
- Bid opening: 2026-08-17 12:00
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን በ4፡00
- Region: South West Ethiopia Region
- Publishing entity: Keffa Zone Finance and Economic Development Bureau
- Bid bond: ለእያንዳንዱ ሎት 80,000.00 (ሰማኒያ ሺህ ብር)
- Bid document price: 500 (አምስት መቶ ብር)
- Published on: Addis Zemen (Aug 01, 2026)
- Posted at: 2026-08-01T07:25:45.000Z