Central Ethiopia
ሀላባ ዞን የዌራ ወረዳ ፋይናንስ የጽ/መሣሪያ እና ሌሎች አላቂ የጽዳት ዕቃዎች፣ የሞተር ሣይክል፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ጀነሬተር እና ፈርኒቸር በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የሀላባ ዞን የዌራ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ለሴ/ጽ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
- 1ኛ/ የጽ/መሣሪያ እና ሌሎች አላቂ የጽዳት ዕቃዎች (ሎት-1)
- 2ኛ/ የሞተር ሣይክል (ሎት-2)
- 3ኛ/ ኤሌክትሮኒክስ (ሎት-3)
- 4ኛ/ ጀነሬተር ሎት 4)
- 5ኛ/ ፈርንቸር (ሎት-5)
በዚህ መሠረት :-
- በዘርፉ የተሰማራችሁ የዘመኑን የታደሰ ንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለበት፡፡
- የአቅራቢነት እና የግብር ከፋይነት ምስክር ወረቀት ያላቸው፡፡
- የቫት ተመዝጋቢነት ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡ ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የተከፈሉበት ኪሊራንስ ማቅረብ ይኖረባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100/አንድ መቶ/ በመክፈል ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባለው ተከታታይ የስራ 21 ቀናት ከግዥ/ፋይ/ንብ/አስ/የስ/ሂደት ሰነዱን ገዝተው መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ 5000 (አምስት ሺህ) በባንክ የተረጋገጠ COP ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን እያንዳንዱን አንድ ኦርጅናል ፣አንድ ኮፒ በማዘጋጀት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 21 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ቢሮ ቁጥር 01 ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በ22ኛ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፤ በዕለቱ ተጫራቾች ያለመገኘታቸው ጽ/ቤቱን ጨረታውን ከመክፈት የሚያግደው ነገር አይኖርም፡፡
- የጨረታው መክፈቻ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ ያሸነፈባቸውን ዕቃዎች ለወረዳው/ፋይ/ጽ/ቤት ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታውአሸናፊ የውል ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ 10% ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጽ/ቤቱ የተሸለ አማራጭ ከተገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፉል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ፡- በስ/ቁ 09-16-12-04-32/09-1672-17-30 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የሀላባ ዞን የዌራ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-08-26
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ22ኛ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-08-26 10:30
- Bid opening (note): ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ22ኛ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
- Region: Central Ethiopia
- Publishing entity: Halaba Zone Wera Woreda Finance Office
- Bid bond: 5000.00 ብር ለእያንዳንዱ ሎት
- Bid document price: 100.00 ብር ለእያንዳንዱ ሎት
- Published on: Addis Zemen (Aug 01, 2026)
- Posted at: 2026-08-01T07:39:15.000Z