Glass, chemicals and packaging materials

የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ የስኳር ማሸጊያ ከረጢት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር MSF/LP/11/2026

የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ከዚህ በታች የተገለፀውን የስኳር ማሸጊያ ከረጢት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል::

ጥቅል አንድ የስኳር ማዳበሪያ ከረጢት (PP sugar bag)

በመሆኑም ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን እንዲወዳደሩ ይጋብዛል ::

1. ሕጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው፣የዘመኑን የሀገር ውስጥ ገቢ ግብር አጠናቀው የከፈሉና ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡

2. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ድርጅቶች ለጥቅል አንድ የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰአት ሜክሲኮ አደባባይ ፊሊፕስ ህንፃ ግዥ ቡድን 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 215 የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ ገዝተው በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡

3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ሲገዙ የንግድ ፈቃድ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

4. ተጫራቾች ከሚያቀርቡት ሠነድ ጋር የታደሰ የንግድ ፈቃድ የአቅራቢዎች የምዝገባ ሠርተፍኬት እና ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 300,000 (ሦስት መቶ ሺህ) በሲ.ፒ.ኦ /C.P.O/ ወይም የባንከ ዋስትና /Bid bond guarantee/ በሲ.ፒ.ኦ ማቅረብ አለባቸው ::

5. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በራሳቸው የዋጋ ማቅረቢያ (Proforma invoice) ላይ በማዘጋጀት በሰም በታሸገ ፖስታ በማድረግ እ.አ.አ ነሐሴ 12 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ሜክሲኮ ፊሊፕስ ሕንጻ ቢሮ ቁጥር 119 ማቅረብ ይኖርባቸዋል ፡፡

6. ጨረታው በዕለቱ ነሐሴ 12 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ ቢሮ ቁጥር 119 ውስጥ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል ፡፡

7. ፋብሪካው ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ስልክ ቁጥር፦ 0115-505 607, 0115-505 633

ሜክሲኮ አደባባይ ፊሊፕስ ሕንፃ

አዲስ አበባ

የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ


Tender details

  • Deadline: 2026-08-18
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-08-18 10:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Metehara Sugar Factory
  • Bid bond: 300,000.00 ብር
  • Bid document price: 300.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Aug 01, 2026)
  • Posted at: 2026-08-01T08:38:23.000Z
← Back to all tenders