UPS, inverters and batteries
ዓድዋ ድል መታሰቢያ ለ2019 በጀት አመት EV charger(ኤሌክትሪክ መኪና ቻርጀር ዕቃዎች) በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ መለያ ቁጥር አ/ድ/መ/001/2019ዓ.ም
ዓድዋ ድል መታሰቢያ ለ2019 በጀት አመት EV charger(ኤሌክትሪክ መኪና ቻርጀር ዕቃዎች) በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ ፈቃደኛ የሆናችሁ ተጫራቾች እንድትሳተፉ እየጋበዝን ዝርዝሩ ከታች ባለው ሰንጠረዥ ተመላከቷል።
|
ምድብ ቁጥር |
የሚገዙ ዕቃዎች አይነት |
የጨረታ ማስከበሪያ(CPO) ብር |
|
ሎት 1 |
EV changer ኤሌከትሪክ መኪና ቻርጀር ዕቃዎች |
15,000 |
ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
1. በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸውና የታክስ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ።
3. ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
4. አቅራቢነት የምዝገባ የምስከር ወረቀት ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል።
5. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር የያዘ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 600(ስድስት መቶ ብር) በዓድዋ ድል መታሰቢያ ስም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተከፈተው አካውንት ቁጥር 1000613546867 በመክፈል ደረሰኝ/ስሊፕ/ ይዞ በመቅረብ መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን ይህ ጨረታ በአየር ላይ የሚቆየው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10/አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት ቅዳሜን ጨምሮ ይሆናል።
6. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ ፋይናንሽል ኦርጅናልና ኮፒ እና ቴክኒካል ኦርጅናልና ኮፒ ለብቻቸው ፖስታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
7. ጨረታው በ10ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰአት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡30 ላይ 12 መሰብሰቢያ ክፍል ቢሮ ቁጥር 214 ይከፈታል።
8. ተጫራቾች የጨረታ አሸናፊ ሆነው የሚገኙበት እቃዎችን በአጠቃላይ ዋጋ 10 ፐርሰንት የውል ማስከበሪያ በማስያዝ የግዥ ውል ስምምነት መፈራረም ይኖርባቸዋል።
9. አሸናፊ ድርጅት የሚቀርቡትን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት እስከ ተቋሙ ንብረት ክፍል ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
10. የጨረታ ሰነድ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ጨረታው ከሚከፈትበት ዕለት ጀምሮ ለ60 ቀናት ይሆናል።
11. መስሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- ፒያሳ አራዳ ህንጻ ፈት ለፊት የዓድዋ ድል መታሰቢያ ፋይናንስና አስተዳደር
ዳ/ዳይሬክተር
ስልክ ቁጥር +251 93 060-0429 / 09-19-61-29-35
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የዓድዋ ድል መታሰቢያ
Tender details
- Deadline: 2026-08-12
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰአት
- Bid opening: 2026-08-12 12:00
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰአት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አድዋ ድል መታሰቢያ
- Bid bond: 15,000.00 ብር
- Bid document price: 600.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Aug 01, 2026)
- Posted at: 2026-08-01T08:57:26.000Z