Addis Ababa
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቦሌ ክ/ከተማ የወረዳ 11 አስተዳደር ፋ/ጽ/ቤት ጥራታቸውን የጠበቁ አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎች፣ ልዩ ልዩ መሳሪያዎች፣ የጽዳት እቃዎች፣ የደንብ ልብሶች፣ የመኪና ጎማ፣ የጭነት አገልግሎት እና የትራንስፖርት አገልግሎት፣ መስተንግዶ፣ ህትመት፣ ዲኮር ኪራይና ድንኳን ኪራይ፣ የኤሌክትሮኒክስ ጥገና እና የቢሮ ፈርኒቸር ጥገና አገልግሎት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት እና ማሰ
Description
ግልጽ የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር 001/2019
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቦሌ ክ/ከተማ የወረዳ 11 አስተዳደር ፋ/ጽ/ቤት ጥራታቸውን የጠበቁ አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎች ልዩ ልዩ መሳሪያዎች፣ የጽዳት እቃዎች፣ የደንብ ልብሶች፣ የመኪና ጎማ የጭነት አገልግሎት እና የትራንስፖርት አገልግሎት፣ መስተንግዶ፣ ህትመት፣ ዲኮር ኪራይና ድንኳን ኪራይ፣ የኤሌክትሮኒክስ ጥገና እና የቢሮ ፈርኒቸር ጥገና አገልግሎት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት እና ማሰራት ይፈልጋል።
በዚህ መሰረት በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ህጋዊ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ መሆን አለባቸው።
1. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበትን ህጋዊ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ለመክፈላቸው ማስረጃ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ።
2. በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር በአቅራቢነት የተመዘገቡና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
3. የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያለው።
4. ተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል።
5. ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሰውን የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ CPO ቦ/ከ/ወ/u/ ፋ/ጽ/ቤት ስም ማቅረብ አለባቸው።/
6. ህጋዊ መንጃ ፍቃድ ያላቸው /ለጭነትና ለትራንስፖርት/።
7. የባለቤትነት መታወቂያ ድብተር/ሊብሬ ያለው /ለጭነትና ለትራንስፖርት/።
8. ሶስተኛ ወገን /ኢንሹራንስ⁄ ያለው ለጭነትና ለትራንስፖርት/።
|
ሎት ቁጥር |
ሎት ዝርዝር |
የተጠየቀው የጨረታ ማስረከቢያ በኢትዮ.ብር |
|
ሎት 1 |
የደንብ ልብስ |
5000.00/አምስት ሺህ ብር/ |
|
ሎት 2 |
አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎች እና ልዩ ልዩ መሳሪያዎች |
10,000 /አስር ሺህ ብር/ |
|
ሎት 3 |
አላቂ የጽዳት እቃዎች |
5000.00/ አምስት ሺህ ብር/ |
|
ሎት 4 |
የመስተንግዶ አገልግሎት |
5000.00/ አምስት ሺህ ብር/ |
|
ሎት 5 |
የህትመት አገልግሎት |
5000.00 /አምስት ሺህ ብር/ |
|
ሎት 6 |
የዲኮርና ድንኳን ኪራይ አገልግሎት |
8000.00/ ስምንት ሺህ ብር/ |
|
ሎት 7 |
ኤሌክትሮኒክስ ጥገና |
2500.00 /ሁለት ሺህ አምስት መቶ ብር/ |
|
ሎት 8 |
ፈርኒቸር ጥገና አገልግሎት |
2500.00 /ሁለት ሺህ አምስት መቶ ብር/ |
|
ሎት 9 |
የመኪና ጎማ |
10,500/አስር ሺህ አምስት መቶ ብር/ |
|
ሎት 10 |
የትራንስፖርት አገልግሎት |
5000.00 /አምስት ሺህ ብር |
|
ሎት 11 |
የጭነት አገልግሎት |
5000.00 /አምስት ሺህ ብር |
|
ሎት 12 |
የልብስ ስፌት |
2500.00 /ሁለት ሺህ አምስት መቶ ብር/ |
1. የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በየሎቱ የማይመለስ ብር 300.00 ብር (ሦስት መቶ ብር) በመክፈል የተዘጋጀውን ሰነድ ከተቋሙ ቢሮ ቁጥር 004 እየቀረቡ መግዛት ይችላሉ።
2. ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን የእቃ ዓይነቶች ውል ከፈረሙበት ጊዜ ጀምሮ በ15 ቀን ውስጥ አጠናቀው ገቢ ማድረግ አለባቸው። በተቀመጠው ቀነገደብ ያላስገቡ ተጫራቾች በህግ የሚጠየቁ መሆኑን ማወቅ ይኖርባቸዋል።
3. ተጫራቾች ጨረታ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት ወረዳ 11 ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 011 ድረስ በመምጣት ዋጋው የተሞላበትን የጨረታ ሰነዱን ዋናውን እና ፎቶ ኮፒውን ለየብቻው በማሸግ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
4. ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተሰጠው ተመሳሳይ ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋው ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
5. ተጫራቾች ያሸነፉበትን ዋናውን የውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ አለባቸው።
6. ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ለሚወዳደሩበት ናሙና ለሚቀርብባቸው እቃዎች ናሙና ማቅረብ አለባቸው። ናሙና የማይቀርብባቸው ቋሚ እቃዎች መስሪያ ቤቱ ባቀረበው ስፔስፊኬሽን መሰረት ማቅረብ አለባቸው።
7. የጨረታ አሸናፊ ድርጅት ያሸነፉትን እቃ በራሱ ትራንስፖርት ቦሌ ወረዳ 11 ፋይናንስ ጽ/ቤት ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል።
8. መ/ቤቱ ለጨረታ ከቀረበው እቃ 20% የመቀነስም ሆነ የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው።
9. የጥቃቅን አነስተኛ ተጫራቾች ባመረቱት ምርት ብቻ መወዳደር ይችላሉ። ነገር ግን ባላመረቱት ምርት ከሆነ እንደማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነድ ገዝተው እንዲሁም ሲፒኦ አስይዘው መወዳደር ይችላሉ።
10. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- ሰሚት ኮንዶሚኒየም 3ኛ በር አደባባዩን ወረድ ብሎ ቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 11 ፋ/ጽ/ቤት
ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 09 18 30 37 97/ 09 12 12 82 06
በቦሌ ክ/ከተማ የወረዳ 11 አስተዳደር ፋ/ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-08-12
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00
- Bid opening: 2026-08-12 10:30
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Bole Sub City Woreda 11 Administration Finance Office
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 300.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Aug 02, 2026)
- Posted at: 2026-08-03T09:33:44.000Z