Personal care and hygiene products
ጮራ ለሕፃናትና ቤተሰብ ልማት የተለያዩ ግብአቶችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
ጮራ ለሕፃናትና ቤተሰብ ልማት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጉለሌ ክ/ከተማ የሕፃናትና የወጣቶች እንዲሁም የማህበረሰብ ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየሰራ የሚገኝ ሀገር በቀል ድርጅት ነው።
ድርጅቱ ለ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት ለልጃገረድ ሴቶችና ለአካል ጉዳተኛ ሕፃናት አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ግብአቶችን ማለትም 7,200 ሮዝ ሞዴስ 3,900 250 ግራም እስካይ ሳሙና እንዲሁም ከ114 እሽግ (ብዛቱ 28) 5 ቁጥር ABC ዳይፐር በተጨማሪም 396 የተማሪ ቦርሳ 121 የመዋለ ሕፃናት እንዲሁም 275 ከ1ኛ እስከ 8ኛ ክፍል አገልግሎት የሚውል በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። ቦርሳ ለሚያቀርቡ ተጫራቾች ድርጅቱ የሚያቀርበውን ቦርሳ ናሙና (ሳምፕል) ፅህፈት ቤቱ ድረስ በመምጣት በመመልከት ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ ፈቃደኛ የሆኑ ከዚህ በታች ያሉትን መስፈርቶች እና አስፈላጊ ሰነዶችን የሚያሟሉ ከታች በተገለፀው አድራሻ የጨረታ ሰነድን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ7 (ሰባት) ተከታታይ የሥራ ቀናት ማስገባት ይኖርባቸዋል።
መስፈርቶች/ሰነዶች፡-
1. በጨረታው ለመወዳደር የሚያበቃቸው የታደሰ የዘመኑ ንግድ ሥራ የምዝገባ ፈቃድ
2. የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ምዝገባ የምስክር ወረቀት
3. አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት
4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ 2% በባንክ የክፍያ ትእዛዝ CPO ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
5. ጨረታውን አሸናፊ ድርጅት የተጠየቁትን ግብአቶች (ሞዴስ ሳሙናና ዳይፐር) ቦርሳ ውል ከተፈራረመበት እለት ጀምሮ በ3 ቀን ውስጥ ማስረከብ የሚችል መሆን ይገባዋል። እንዲሁም በራሱ ትራንስፖርት ማስተባበሪያ ጽ/ቤታችን ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል።
ጨረታው በ7ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ተዘግቶ ጨረታው በተዘጋበት እለት 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
ማሳሰቢያ፡- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 011-157-5125
CPO የሚሰራበት Chora for Children and Family Development
አድራሻ፡- ሰሜን መዘጋጃ ከፍ ብሎ ድልበር ት/ቤት አጠገብ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና ጽ/ቤት
ጮራ ለሕፃናትና ቤተሰብ ልማት
Tender details
- Deadline: 2026-08-08
- Bid closing time: 09:30
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ7ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት
- Bid opening: 2026-08-10 10:00
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ7ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Chora for Child and Family Development
- Bid bond: 2%
- Published on: Addis Zemen (Aug 02, 2026)
- Posted at: 2026-08-03T09:36:50.000Z