Fresh produce, meat and dairy
የመከላከያ ሠራዊት መኮንኖች ክበብ ደረጃውን የጠበቀ የጤፍ ዱቄት፣ አትክልትና ፍራፍሬ፣ የስጋ አቅርቦት፣ የምግብ ቅቤ እና የማር፣ የዶሮ እና የእንቁላል አቅርቦ፣ የባልትናና የጥራጥሬ አቅርቦት ወይም የታሸጉ የምግብ ሸቀጦች እና ዓሳ አቅርቦት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ ለመፈፀምናስራውን ለማሠራት ይፈልጋል
Description
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የመከላከያ ሠራዊት መኮንኖች ክበብ ከዚህ በታች በዝርዝር የተጠቀሱት የተለያዩ አቅርቦቶች ስራዎች በመስኩ ከተሠማሩ ድርጅቶች ጋር ውል በማሰር በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ ለመፈፀምናስራውን ለማሠራት ይፈልጋል።
- ደረጃውን የጠበቀ የጤፍ ዱቄት፣
- አትክልትና ፍራፍሬ
- የስጋ አቅርቦት
- የምግብ ቅቤ እና የማር
- የዶሮ እና የእንቁላል አቅርቦ
- የባልትናና የጥራጥሬ አቅርቦት ወይም የታሸጉ የምግብ ሸቀጦች
- ዓሳ አቅርቦት
በዚህ መሠረት ማንኛውም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟላ አካል በጨረታው መሳተፍ ይችላል።
- በመስኩ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፤
- የ2018 ዓ.ም ግብር የከፈሉ፤
- በተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ፣
- የግብር መለያ ቁጥር /ቲን ነምበር/ ያላቸው ሆነው የምስክር ወረቀት የተሰጣቸውና ማቅረብ የሚችሉ፤
- የጨረታ ሰነዱን በመከላከያ ሠራዊት መኮንኖች ክበብ ገንዘብ ያዥ ድረስ በማቅረብ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የስራ ቀናት ቅዳሜን ጨምሮ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት እስከ ምሽት 11:00 ሰዓት ከላይ የተዘረዘሩትን መረጃዎች ዋናውንና አንድ ኮፒ በመያዝ የማይመለስ 500.00 (አምስት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል የጨረታ ሠነዱን መውሰድ ትችላላችሁ፤
- ማንኛውም ተጫራች በጨረታ መክፈቻ ቀን ለእያንዳንዱ ሰነድ 10,000.00 (አስር ሺህ ብር በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርበታል፤
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በክበቡ ግዥ ክፍል ለዚህ ተግባር በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ዕለት ጀምሮ ባሉት 15 ቀናት ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- የጨረታ ሠነዱ ስርዝ ድልዝ ቢኖረው፣ ባይፈረምና በፍሉድ ቢጠፋ ከሆነ ከጨረታው ይሰረዛል፤
- የጨረታ ሰነድ ለማስገባት ስትመጡ ቴክኒካል ኮፒ እና ፋይናንሻል ኮፒ መኖሩን ያረጋግጡ፤
ማሳሰቢያ፡- ክበቡ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- የመከላከያ ሠራዊት መኮንኖች ክበብ ጦር ሃይሎች አካባቢ
ስልክ ቁጥር፡-011 371 7317
የመከላከያ ሠራዊት መኮንኖች ክበብ
Tender details
- Deadline: 2026-08-17
- Bid closing time: 17:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የስራ ቀናት ቅዳሜን ጨምሮ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት እስከ ምሽት 11:00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-08-17 17:00
- Bid opening (note): የጨረታ መክፈቻ ቀንና ሰዓት አልተገለጸም
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Defense Force Mekonnenoch Club
- Buyer address: መከላከያ ሠራዊት መኮንኖች ክበብ ጦር ሃይሎች አካባቢ
- Bid bond: 10,000.00 ብር በእያንዳንዱን ሎት
- Bid document price: 500.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Aug 02, 2026)
- Posted at: 2026-08-03T10:49:52.000Z