Addis Ababa

ሁንዴ ኦሮሞ ግራስሩትስ ዴቬሎፕመንት ኢኒሼቲቭ ሆለታ ቅርንጫፍ ግቢ የሚገኙትን የተለያዩ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈለጋል

Description

ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን በጨረታ ለመሸጥ የወጣ ማስታወቂያ

ሁንዴ ኦሮሞ ግራስሩትስ ዴቬሎፕመንት ኢኒሼቲቭ ሆለታ ቅርንጫፍ ግቢ የሚገኙትን የተለያዩ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን፣ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈለጋል።

ስለሆነም

1. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናቶች ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 10፡00 ሰዓት ከአዲስ አበባ ዋና ቢሮ ሁንዴ ኦሮሞ ግራስሩትስ ዴቬሎፕመንት ኢኒሼቲቭ በመገኘት የጨረታውን ሠነድ የማይመለስ ብር 1,000.00 (አንድ ሺህ ብር) ብቻ በመከፈል መግዛት ይኖርባቸዋል። በመቀጠልም ወደ ሆለታ ቅርንጫፍ ግቢ በመሄድ መኪናውን በአካል ከጎበኙ በኋላ ሰነዱን ሞልተው ተመላሽ ያድርጋሉ። አንዲዚሁም የመኪናው ዓይነት በሰነዱ ላይ በዝርዝር ያገኙታል።

2. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ተሽከርካሪ ወይም በጥቅል የሚወዳደሩ ከሆነ የጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ (10%) በሁንዴ ኦሮሞ ግራስሩትስ ዴቬሎፕመንት ኢኒሼቲቭ ስም የጨረታ ማስከበሪያው በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ተሞልቶ ከጨረታ ሠነዱ ጋር በማያያዝ በጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

3. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናቶች የሚሸጡ ተሽከርካሪዎችን ለማየት ኮፈን ተከፍቶ ስለሚቆይ ዘወትር በስራ ሠዓት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 10፡00 ሠዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን ሆለታ በሚገኘው ድርጅታቸን ከምችት ገቢ በስፍራው ተገኝተው መመልከት ይቻላል።

4. ተጫራቾች ከጨረታ ሠነድ ጋር በተያያዘው የዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ ብቻ ተጫራቾች የሚገዙበትን ዋጋ፣ ስማቸውን፣ክፍለከተማ፣ወረዳ፣ የቤት ቁጥርና ስልክ ቁጥራቸውን በግልፅ በመፈረም ማቅረብ አለባቸው።

5. ከጨረታው መዝጊያ ሰዓት በኋላ የሚደርሱ የጨረታ ሠነዶች ተቀባይነት የላቸውም።

6. ጨረታው ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት አየር ላይ ከቆየ በኋላ በመጨረሻው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአዲስ አበባ ዋና ቢሮ የሚከፈት ይሆናል

7. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ገንዘብ አጠቃለው ከከፈሉ በኋላ ንብረቶቹን በ20 የስራ ቀናት ውስጥ የማንሳት ግዴታ አለባቸው።

8. ለተሽከርካሪዎች የስም ማዞሪያ ወጭዎች ለማንሳት የሚያስፈልግ ማንኛውም ወጭ ሙሉ በሙሉ በገዥዎች ይሸፈናል።

10. ድርጀቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ፡- ሁንዴ ኦሮሞ ግራስሩትስ ዴቬሎፕመንት ኢኒሼቲቭ ከመስቀል ፍላወር አደባባይ ወደ ቅዱስ ያሬድ ቤ/ክ በሚያስገባ ኮቢል ስቶን ዜማ ያሬድ መኪና መሸጫ አጠገብ ወይም በስልክ ቁጥር 09 13 39 98 17 መደወል ይቻላል።

ሁንዴ ኦሮሞ ግራስሩተስ ዴቬሎፕመንት ኢኒሼቲቭ


Tender details

  • Deadline: 2026-08-12
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ጨረታው ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት አየር ላይ ከቆየ በኋላ በመጨረሻው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-08-12 10:30
  • Bid opening (note): ጨረታው ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት አየር ላይ ከቆየ በኋላ በመጨረሻው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Hundee-Oromo Grassroots Development Initiative
  • Buyer address: አዲስ አበባ፣ መስቀል ፍላወር አካባቢ፣ ያሬድ ቤተክርስቲያን ጀርባ፣ በቪላ ቨርዴ ሆቴል ገባ ብሎ
  • Bid bond: 10%
  • Bid document price: 1000
  • Published on: Reporter (Aug 02, 2026)
  • Posted at: 2026-08-03T11:35:20.000Z
← Back to all tenders