Addis Ababa
የኢትዮጵያ ጠለፋ መድን አ.ማ. ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር ኢጠመ/0005/2018
ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን ለመሸጥ የወጣ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
ኩባንያችን የኢትዮጵያ ጠለፋ መድን አ.ማ. በአሁኑ ወቅት በዋና ቢሮ (Head Office) እየተጠቀመባቸው ያሉትን ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
ስለሆነም ፍላጎት ያላችሁ እና ከዚህ በታትች የተዘረዘሩትን መስፈርት የምታሟሉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ተሽከርካሪዎች የተጠቀሱትን መስፈርቶች እና ሰነዶች በማሟላት ለመግዛት እንድትወዳደሩ እንጋብዛለን፡-
|
ተቁ |
የተሽከርካሪዎች አይነት በዝርዝር |
ብዛት
|
የሞተር ቁጥር
|
የሻንሲ ቁጥር
|
ሲሲ
|
የሠሌዳ ቁጥር |
የጫረታ መነሻ ዋጋ |
|
1 |
ሚኒባስ ሃዩንዳይ (MINI BUS H-1) |
1 |
D4BHG009026
|
KMJWA37HAGU835241
|
2476
|
03-አ36111አአ |
2,750,000.00
|
|
2 |
ክሬታ-ሃዩንዳይ
|
1 |
G4FGGU832055
|
MALC381CBGM133356 |
1591 |
03-አ37413አአ |
3,250,000.00 |
|
3 |
ክሬታ-ሃዩንዳይ
|
1 |
G4FGGU847434 |
MALC381CBGM133346 |
1591 |
03-37414አአ |
3,250,000.00 |
|
4 |
ቺቭሮሌት
|
1 |
B12D1386347KD3
|
KL1TJ6CD8GB514647 |
1200 |
03-38578አአ |
1,350,000.00
|
ስለሆነም ፍላጎት ያላችሁ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች እና ሰነዶች በማሟላት እንድትወዳደሩ እንጋብዛለን፡-
1. ተጫራቾች የታደሰ ህጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ፤ የንግድ ምዝገባ ፈቃድ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ምስክር ወረቀት፤ የግብር ከፋይ ምዝገባ ምስክር ወረቀት እና የመሳሰሉትን ሰነዶች በማያያዝ ማቅረብ አለባችሁ።
2. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ቀናት ከጠዋት 2፡00 እስከ 11፡00 ሰዓት ባለዉ ጊዜ ዉስጥ ለሽያጭ የቀረቡትን ተሽከርካሪዎች ልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 09 ጆሳንሰን አካባቢ በሚገኘው የኩባንያዉ ዋና መሥሪያ ቤት ህንፃ 7ኛ ፎቅ በአካል በመምጣት መመልከት ትችላላችሁ።
3. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ንብረት የጫረታ መነሻ ዋጋ ለሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ ) 1/4 (አንድ አራተኛ) በባንክ የተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ በኩባንያችን ስም በማሰራት ከጨረታ ሰነድ ጋር በማያያዝ በታሸገ ኤንቨሎፕ ለዚሁ በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ዉስጥ ጨረታዉ ከመዘጋቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል።
4. የጨረታዉ መገምገሚያ መስፈርት መኪናዉን ለመግዛት የቀረበ ዋጋ፤ የተሟላ ጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ሲ.ፒ.ኦ) እንዲሁም በሰነዱ የተገለጹትን ዶክመንቶች አሟልቶ መገኘት ነዉ።
5. ከላይ በተራ ቁጥር 4 የተገለጸዉን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ያላስያዘ እና የተዘረዘሩትን ሌሎች ነጥቦች ያላሟላ ተጫራች ከጨረታዉ ዉድቅ ይደረጋል።
6. የጨረታ ሳጥኑ ጨረታዉ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ማለትም ከሰኞ ሓምሌ 27 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን በ15ኛዉ ቀን ማለትም አርብ ነሓሴ 15 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በኩባንያዉ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል። ተጫራቹ በራሱ ዉሳኔ ጨረታዉ በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኙ ቢቀር የጨረታዉን መከፈት አያስተጓጉልም።
7. በጨረታዉ አሸናፊ ተጫራቾች ጨረታዉን ማሸነፋቸዉ ከተነገረበት ወይም የስማቸዉ ዝርዝር በማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ ከተለጠፈበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር ከ2 /ሁለት/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ዉስጥ የዉል ማስከበሪያ የዉል ዋጋዉን 10 በመቶ በማቅረብ ኩባንያዉ ጋር ዉል መፈራረምና ያሸነፉበትን ዋጋ ሙሉ መክፈል ይኖርባችዋል። ሆኖም ከላይ በተገለጸዉ መሰረት ዉል ካልፈረሙ ወይም ሙሉ ክፍያዉን በተጠቀሰዉ ጊዜ ገደብ ዉስጥ መክፈል ካልቻሉ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለኩባንያዉ ገቢ ይደረጋል።
8. የጫረታዉ አሸናፊ ከሚገዛዉ ተሽከርካሪ ጋር የተያያዙ ማናቸዉንም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎች፤ ግብር 15% የተጨማሪ እሴት ታክስ፤ የስም ማዘዋወሪያ፤ ተሽከርካሪ የዋጋ ግምት እንዲሁም በመንገድ ትራንስፖርት በኩል ሊፈጠር የሚችለዉን ማናቸዉንም ወጪዎች ይክፍላል።
9. ተጫራቾች ያሸነፉትን ተሽከርካሪዎች በ5 /አምስት/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ዉስጥ መዉሰዳቸዉ ሲረጋገጥ ያስያዙት የዉል ማስከበሪያ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
10. ኩባንያዉ ባወጣዉ ጨረታ በንግድ ስሙ ያልተወዳደረ ማንኛዉም ተጫራች ከተገኘ ከዉድድር ዉድቅ ይደረጋል።
11. ተጫራቾች የፋይናንስ ዋጋ ግምገማ (Financial Proposal) ሰነድ በታሸገ ፖስታ በሚከተለው አድራሻ ከላይ በተጠቀሰው የጨረታ ማስታወቂያ ጊዜ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
የኢትዮጵያ ጠለፋ መድን አ.ማ
የሰው ሃብትና ተቋም አገልግሎት ልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 09፤ ጆሳንሰን አካባቢ ከኖቢ ኮምፕሌክ ህንጻ አጠገብ በሚገኘው የኩባንያዉ ዋና መሥሪያ ቤት ህንፃ 7ኛ ፎቅ
ስልክ፡ +251-11 557 5757
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
12. የኢትዮጵያ ጠለፋ መድን ኢማ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
13. ስለ ጫረታዉ አፈጻጸም ዝርዝር ማብራሪያ የሚፈልጉ ተጫራቾች ጫረታዉ ከመዘጋቱ ቀን በፊት በስልክ ቁጥር 011 557 5757 በመደወል መጠየቅ ይቻላል።
የኢትዮጵያ ጠለፋ መድን አ.ማ.
Tender details
- Deadline: 2026-08-21
- Bid closing time: 14:00
- Bid opening: 2026-08-21 14:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Ethiopian Reinsurance Share Company
- Buyer address: አፍሪካ ጉዳና ቢትወደድ ባህሩ አብርሃም ህንፃ 6ኛ ፎቅ በመቅረብ
- Bid bond: 25%
- Published on: Reporter (Aug 02, 2026)
- Posted at: 2026-08-03T11:54:49.000Z