Medical consumables and disposables
የሰሜን ሸዋ ዞን ኩዩ አጠቃላይ ሆስፒታል ለ2019 የበጀት ዓመት ለኩዩ አጠቃላይ ሆስፒታል የተለያዩ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛትና ለማስራት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የሰሜን ሸዋ ዞን ኩዩ አጠቃላይ ሆስፒታል ለ2019 የበጀት ዓመት ለኩዩ አጠቃላይ ሆስፒታል አላቂ እቃዎች የጽህፈት መሳሪያዎች የፅዳት እቃዎች፤ ቋሚ የቢሮ እቃዎች ግዥና ጥገና፤ የኤሌክትሮንክስ እቃዎች፤ የኤሌክትሪክ እቃዎች፤ መዲካል እቃዎች፤ የደንብ ልብስ፤ የመኪና ጎማ፤ የህትመት ስራና የህክምና እቃዎች፣ ኮምፒውተርና ፕሪንተር ማስጠገን፣ የመኪኖች ማስጠገንና ተለዋዋጭ እቃዎች ግዥ፣ የኮምፒውተር ቀለም ሙሌት ስራ፣ መዳኒትን ለመጫን ኦክስጅን ሲሊንደር እና የተለያዩ እቃዎችን ለማስጫን, የተለያዩ ፎርማቶችን ለማሳተም፣ ኮምፒዩተርን እና የተለያዩ እቃዎችን ለማስጠገን የቤት ኮርኒስን ለማስጠገን፣ያረጁ የሆስፒታል ህንፃዎችን ማሳድስ እና ሆስፒታል ውስጥ የሚገኝ ካፍቴሪያ መከራየት ሰለምፈልግ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛትና ለማስራት የተዘጋጀ የጨረታ ሰነድ።
ሀ. የተወዳዳሪዎች መመሪያ
ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ እና 2018/2019 የታደሰ ንግድ ፍቃድ ማስረጃ የገንዘብ እና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር የእቃ አቅራቢነት የተመዘገበ ንግድ ፍቃድ ማስረጃ እና 100000(አንድ መቶ ሺ) ብር በላይ ገቢ ግዥ የሚወዳደሩ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገበ የምስክር ወረቀት ማስረጃ ከመወዳደሪያ ሀሳብ ሰነድ ጋር በማያያዝ ማቅረብ አለባቸው።
1. ተጫራቾች ከማንኛውም ሙስና የብክነት ድርጊቶች ነፃ ለመሆን በፈደራል እና በክልል የወጡትን የግዥ ደንቦችን የሚያከብር ስለመሆኑ ሰነድ ውስጥ የቀረቡትን ግዴታዎች አምኖበት መፈጸም ይኖርባቸዋል።
2. ማንኛውም ተጫራቾች ጨረታውን በህገ ወጥ መንገድ ማቅረብ የሞከረ ከጨረታ ውጭ ከመሆኑ በላይ ለወደፊቱ በሚካሄዱት ጨረታዎች እንዳይሳተፍ ተደረጎ ያስያዘው የጨረታ ማስከብሪያ ቤቱ ገቢ ይሆናል።
3. ተጫራቾች በፈለጉት ዕቃ እና ማቅረብ በሚችሉት ዕቃዎች ላይ ብቻ መወዳደር ይችላሉ ሆኖም ለአንድ አይነት እቃ ከተጠየቀው ብዛት አሳንሶ መቅረብ አይቻልም።
4. ተጫራቾች ወደ ጨረታው ለመቅረብ ግዴታቸውን የተወጡ እና የተጠየቀውን ስፔስፊኬሽን በሟሟላት የወቅቱን የገበያ ሁኔታ ያገናዘበ ዋጋ መስጠት የሚችሉ መሆን አለባቸው።
5. አንድ ተጫራች በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት ይኖርበታል።
6. የተጫራቾች የወዳደሪያ ሀሳብ ሰነድ ሲቀርብ የእቃው ስፔስፍከሽን የእቃው አይነት መጠን የአምራቹ ስም የተመረተበት አገር እና የእቃውን መለያ ሞዴል መግለጽ እና ሰነድ ስርዝ ድልዝ የሌለው ሆኖ በግልጽ የተጻፈ መሆን አለበት።
7. የእዕቃው ናሙና ወይም ስዕል ማሳየት አስፈላጊ በሆነበት ጊዜ ማቅረብ የሚችል ከሰነድ ጋር ያቀርባል።
8. ተጫራቾች ያሸነፉበትን እቃ በሰሜን ሸዋ ዞን ኩዩ አጠቃላይ ሆስፒታል እቃ ግምጃ ቤት ገቢ ማድርግ ይኖርባቸዋል።
9. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሀሳብ ሰነድላይ ስም ፊርማ እና አድረሻ ማስፈር ይኖርባቸዋል።
10. መ/ቤቱ በአቀረበው ጨረታ ላይ 20 % የመጨመር ወይም የመቀነስ መብት አለው።
11. አሸናፊ ተጫራች ከተገለጸበት ከ 3-5 ቀን ቀርቦው ውል ካለ ፈጽሙ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ ይወረሳል።
12. የጨረታው የመወዳደሪያ ሀሳብ ኦሪጅናል እና አንድ ፎቶ ኮፒ በሰም በታሸገ ኢንቭሎፕ ይቀርባል።
13, የሚቀረበው ሰነድ በሚመለከተው ባለስልጣን የተፈረመበት እና በማህተም የተረጋገጠ መሆን አለበት።
14. የጨረታው ሳጥን ሰሜን ሸዋ ዞን ኩዩ አጠቃላይ ሆስፒታል ቢሮ ቁጥር 1 ይገኛል።
15. ተወዳዳሪዎች የጨረታውን መወዳደሪያ ሰነድ በታሸገ ፖስታ በ 27/11/ 2018 እስከ 25/12/2018 ዓ.ም ድረስ ማንኛውም ቀን የስራ ቀን ማቅረብ የሚችሉ።
16. የጨረታ ሳጥን በ25/12/2018 ልክ በ 07፡30 ይዘጋል።
17. ጨረታው በ25/12/2018 ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
18. አሸናፊ ተጫራቾች የውል ማስከበሪያ የጨረታ ውጤት ከተነገረበት ከሶስት እስከ አምስት ቀናት ውስጥ ከግዥ ዋጋ ላይ 10% በስፒኦ ወይም በባንክ በተመሰከረ ቼክ በማቅረብ የግዥውን ውል መፈርም ይኖርበታል።
19. የመጨረሻ ክፍያ አጠቃላይ የጨረታው እቃ አሸናፊ ተጫራቾች በሞደል 19 ገቢ መሆኑን ከተረጋገጠ በኋላ ይከፈላል።
20, ተጫራቾች በገቢዎች ባለስልጣን ተፈቅዶ የታተመ በደረሰኝ ማቅረብ ይገባቸዋል።
21. የሚቀርበው ዋጋ ከታክስ ውጭ ወይም ከታከሲ ጭምር መሆኑን መገለጽ አለበት። ካልተገለፀ የቀረበው ዋጋ ከታክስ ጭምር እንደ ቀረበ ተደረጎ ይወሰዳል።
22. ይህ ጨረታ ተወዳዳሪ በሰዓቱ ባይገኝም በሰዓቱ ይከፈታል።
23. ተጫራቾች እያንዳንዱን ዕቃ የሚሸጡበትን ዋጋ የያዘ ዝርዝር የዋጋ ሰነድ በፖስታ በማሸግ በ25/12/2018 ዓ.ም እስከ 07፡30 ሰዓት ብቻ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 20,000 ብር ጋር በማስያዝ ከላይ በተጠቀሰው መ/ቤት ያስገባል።
24. የጨረታው ሰነድ 27/11/2018 እስከ 25/12/2018 ድረስ ከኩዩ አጠቃላይ ሆስፒታል ፋይናንስና ግዥ ቁ.1 ተገኝቶ በ 500 ብር የማይመለስ መግዛት ይቻላል።
መ/ቤቱ ስም እና አድራሻ
ስልክ ቁጥር :- 011 131 0361 / 09 19 41 41 26
በሰሜን ሸዋ ዞን ኩዩ አጠቃላይ ሆስፒታል
Tender details
- Deadline: 2026-08-31
- Bid closing time: 13:30
- Bid opening: 2026-08-31 14:00
- Region: Oromia
- Publishing entity: Kuyu General Hospital
- Bid bond: 20,000.00 ብር
- Bid document price: 500.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Aug 02, 2026)
- Posted at: 2026-08-03T12:57:59.000Z