Medical consumables and disposables

በጉ/ክ/ከተማ አዲስ ሕይወት ጤና ጣቢያ ለ2019 ዓ.ም. የበጀት ዓመት የአንደኛ ዙር የተለያዩ ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

ማስታወቂያ

የጨረታ መለያ ቁጥር 001/2019 ዓ/ም የአንደኛ ዙር ዕቃ ግዥ ግልፅ ጨረታ በጉ/ክ/ከተማ አዲስ ሕይወት ጤና ጣቢያ ለ2019 ዓ.ም የበጀት ዓመት የአንደኛ ዙር

  • የተለያዩ የደንብ ልብስ፣
  • የጽሕፈት መሣሪያ፣
  • ህትመት፣
  • የፅዳት ዕቃዎች፣
  • አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፣
  • የውስጥ ፓርትሽን ለሕንፃ ቁሳቁስና ለተገጣጣሚዎች እደሳና ጥገና፣
  • የሠራተኛ ካፍቴሪያ፣
  • የጭነት አገልግሎት፣
  • ፕላንትና ማሽነሪ ለመሣሪያ ጥገና፣
  • ፕላንትና ማሽነሪ ለመሣሪያ ግዥ ቋሚ የቢሮ እቃዎች ለመድኃኒት እና ላቦራቶሪ ሪኤጀንት እና ቋሚ የሕክምና በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህም:-

1. ማንኛውም ሕጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለው የቫት ተመዝጋቢ የሆነ የዘመኑን ግብር የከፈለና በአቅራቢዎች ሊስት የተመዘገበ በራሱ ትራንስፖርት ጤና ጣቢያው ንብረት ክፍል ድረስ ማቅረብ የሚችል።

2. ማንኛውም ሕጋዊ ተጫራቾች ከሚጫረቱበት ጠቅላላ የዕቃውን ዋጋ የጨረታ ማስከበሪያ

  • ሎት 1 የደንብ ልብስ እና ስፌት 7,000
  • ሎት 2 የጽሕፈት መሣሪያ 6,884፣
  • ሎት 3 ህትመት 2,500
  • ሎት 4 የፅዳት እቃ 9,242
  • ሎት 5 አላቂ የቢሮ ዕቃዎች 6,160
  • ሎት 6 የውስጥ ፓርትሽን ለሕንፃ ቁሳቁስና ለተገጣጣሚዎች እደሳና ጥገና 10,000
  • ሎት 7 የሠራተኛ ካፍቴሪያ 10,560
  • ሎት 8 ጭነት አገልግሎት 800
  • ሎት 9 ፕላንት ማሽነሪ ለመሣሪያዎች ጥገና 4,000
  • ሎት 10 ፕላንት ማሽነሪ ለመሣሪያዎች ግዥ 25,322 ለመድኃኒት እና ላቦራቶሪ ሪኤጀንት እናቋሚ የሕክምና 10,000 እቃ በጤና ጣቢያው ስም በየሎት የተገለፀውን CPO (ሲፒኦ) ማቅረብ አለባቸው። ተደምሮ የሚመጣው CPO (ሲፒኦ) ተቀባይነት የለውም።

3. አሸናፊ ተጫራቾች ለውል ማስከበሪያ የሚውል የጠቅላላ ዋጋ 10% ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

4. ማንኛውም ተጫራች የዕቃዎቹን ዝርዝር የያዘውን ሰነድ የማይመለስ ብር 200 ብር በመክፈል ጤና ጣቢያው ድረስ በመምጣት አራተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 406 ግዥ ከፍል ሰነዱን መግዛት ይችላል። ሆኖም ግን በጥቃቅን እና አነስተኛ የተደራጁ በዋስትና ደብዳቤ ሰነዱን በነፃ መውሰድ የሚችሉ ይሆንና ነገር ግን ድርጅታቸው በማያመርቱባቸው እቃዎች ሎቶች ላይ የጨረታ ሰነድ የሚገዙ እና የጨረታ ማስከበሪያ CPO (ሲፒኦ) ማቅረብ አለባቸው።

5. የጨረታ ሰነዱን የሚወዳደሩበትን ሎት ዋጋ በመሙላት ኦርጅናል እና ኮፒ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በየሎቱ ታሽጎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጋዜጣው ከወጣበት ቀን እስከ 10ኛው ቀን 11፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

6. ጨረታው በ10ኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከቀኑ በ11፡00 ሰዓት ታሽጎ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ይከፈታል። 11ኛው ቀን የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።

7. የጨረታ ሠነዱን ዋጋ ሞልተው ለማስገባት ሲመጡ በቅድሚያ ናሙና ማቅረብ ባለባቸው እቃዎች ላይ ናሙና ማቅረብ አለባቸው።

8. ማንኛውም ተጫራች የሚጫረቱበትን እቃ መ/ቤቱ አስፈላጊ ሆኖ ካገኘው ዓመቱን ሙሉ ማቅረብ የሚችል።

9. ጤና ጣቢያው የዕቃውን ብዛት እንደአስፈላጊነቱ ከውል በፊትም 20% እና ከውል በኋላ 25% የመጨመር ወይም የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው።

10. መሥሪያ ቤቱ ዕቃውን አስፈላጊ ሆኖ ካገኝው እስከ 6 ወር ድረስ የእቃውን 25% በተናጥል ዋጋ ተጨማሪ ግዥ ትዕዛዝ ሰጥቶ ግዥ መፈፀም ይችላል።

11. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- ሽሮሜዳ ሥላሴ ቤ/ክርስቲያን ሳይደርሱ በስተግራ በሚያስገባው አስፓልት 500 ሜትር ገባ ብሎ በቀድሞው ቀበሌ 23/18 ባሁኑ ወረዳ 6 አጠገብ

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 09 13 65 61 17/ 09 11 89 96 32/ ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በሸገር ከተማ አስተዳደር የገላን ክ/ከተማ/ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-18
  • Bid closing time: 17:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ጨረታው በ10ኛው ቀን በ11፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-08-19 12:00
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Gulele Sub City Addis Hiwot Health Center
  • Buyer address: ሽሮሜዳ ሥላሴ ቤ/ክርስቲያን ሳይደርሱ በስተግራ በሚያስገባው አስፓልት 500 ሜትር ገባ ብሎ በቀድሞው ቀበሌ 23/18 በአሁኑ ወረዳ 6 አጠገብ
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Aug 09, 2026)
  • Posted at: 2026-08-10T08:52:26.000Z
← Back to all tenders