Addis Ababa
በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 13 አስተዳደር እና ፋይናንስ ጽ/ቤት የ2019 በጀት ዓመት የተለያዩ ዕቃዎችን በ1ኛው ዙር ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 13 አስተዳደር እና ፋይናንስ ጽ/ቤት የ2019 በጀት ዓመት የ1ኛ ዙር ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም ከታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች እንድትወዳደሩ እያሳወቅን።
|
ተ.ቁ |
የእቃው አይነት |
የሎት አይነት |
የጨረታ ማስከበሪያ ብር መጠን |
|
1 |
ስቴሽነሪ እና ቶነሮች መሳሪያዎች |
ሎት 1 |
30,206.96 ብር |
|
2 |
የፅዳት እቃዎች |
ሎት 2 |
59,825.088 ብር |
|
3 |
የደንብ ልብስ |
ሎት 3 |
36,521.56 ብር |
|
4 |
ልዩ ልዩ የቢሮ መገልገያ ዕቃዎች |
ሎት 4 |
6000 ብር |
|
5 |
ፈርኒቸር እቃዎች |
ሎት 5 |
20,000 ብር |
|
6 |
የመስተንግዶ አቅርቦት |
ሎት 6 |
8,000 ብር |
|
7 |
የትራንስፖርት አገልግሎት |
ሎት 7 |
15,000 ብር |
|
8 |
የህትመት አገልግሎት |
ሎት 8 |
13,000 ብር |
|
9 |
የኤሌክትሮኒክስ ጥገና አገልግሎት |
ሎት 9 |
4,000 ብር |
|
10 |
የመድረክ እቃዎች ኪራይ አገልግሎት |
ሎት 10 |
5,000ብር |
1. በጨረታ ለመወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች በዘመኑ ህጋዊ የሆነ የታደሰ የንግድ ፍቃድ፣ ቲን ነምበር ያለው እና የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለበት።
2. በጨረታው የሚወዳደሩ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ብቻ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።
3. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችል በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ ለመሆኑ ማስረጃ ከሰነዱ ጋር ማቅረብ የሚችል።
4. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት እቃ ናሙና ማቅረብ አለባቸው።
5. ተጫራቾች ዋጋ ሲሞሉ ስርዝ ድልዝ ቢፈጠር ከፊት ለፊቱ ፊርማ ሊኖረው ይገባል። አለበለዚያ የተሞላው ዋጋ ተቀባይነት የለውም።
6. የጨረታ ሰነዱ አንዱ የጨረታ መመሪያ መሆኑን ተጫራቾች ሊረዱት የሚገባ ሲሆን በጨረታ ሰነዱ ላይ ያልተካተቱ ችግሮች ቢያጋጥሙን በግዥ መመሪያው መሰረት የሚዳኝ ይሆናል።
7. ጨረታውን ለማወዳደር የእቃ ጥራት የዋጋ ዝቅተኝነት ወ.ዘ.ተ ግምት ውስጥ የምናስገባ ይሆናል።
8. ጨረታውን ለማዛባት ወይም እንቅፋት ለመፍጠር የሚሞክሩ ተጫራቾች ከጨረታ ውጪ የሚሆኑ ሲሆን ወደፊትም በመንግስት ግዥ መመሪያ መሰረት በህግ እንዲከሰሱ ይደረጋል።
9. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ዋጋ ለውጥ ማሻሻያ ማድረግና ራሳቸውን ማግለል አይችሉም። እንዲሁም ከስፔስፊኬሽን ወይም ካቀረቡት ናሙና ውጭ ማቅረብ አይችሉም።
10. ጨረታው በሁለት ኢንቨሎፕ የሚቀርብ ሆኖ ኦርጂናል እና ኮፒ የጨረታ ሰነድ የሚል ጽሁፍ እንዲሁም ሙሉ የጨረታ ሰነዱ ኮፒ ተደርጎ በአቅራቢው ድርጅት ማህተም ተረጋግጦ ተመላሽ መሆን ይገባል።
11. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ክፍት ሆኖ የሚቆይ ይሆናል።
12. ተጫራቾች መጫረቻ ስነዶችን ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ 10ኛው ቀን ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በ10ኛው ቀን 11፡00 የሚታሸግ ሲሆን ቀጣዩ ቀን የስራ ቀን ከሆነ ጠዋት 3፡30 ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም የሚከፈትና የሚለይ ይሆናል።
13. የመወዳደሪያ ሰነዱን ቦ/ክ/ከ/ወ/13/ አስተዳድር እና ፋይናንስ 4ኛ ፎቅ በመቅረብ አንድ ሎት ዋጋ የማይመለስ 200 (ሁለት መቶ) ብር በመክፈል መግዛት ይችላሉ።
14. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ውል መያዝ አለባቸው። በተጨማሪም ውሉን ከተዋዋሉ በኃላ እቃውን በ10 ቀናት ውስጥ በአስተዳድሩ ግቢ ውስጥ ባለው ንብረት ክፍል አጠናቀው ማስገባት ይኖርባቸዋል።
15. ጽ/ቤቱ 20 % መጨመር ወይም 20% መቀነስ መብቱ የተጠበቀነ ነው።
ማሳሰቢያ - የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ፡- ገርጂ ታክሲ ተራ ወረዳ 13 አስተዳድርና ፋይናንስ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 41 በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር፡- 011 893 1655 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
የቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 13 አስተዳደር እና ፋይናንስ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-08-12
- Bid closing time: 17:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው ቀን 11፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-08-13 09:30
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ቆይቶ በቀጣዩ የስራ ቀን ጠዋት 3፡30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Bole Sub City Woreda 13 FEDB
- Buyer address: ርጂ ታክሲ ተራ ወረዳ 13 ፋይናንስ ጽ/ቤት 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 41
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 200.00 ብር በየሎቱ
- Published on: Addis Zemen (Aug 02, 2026)
- Posted at: 2026-08-03T13:08:21.000Z