Addis Ababa

በምዕራብ ወለጋ ዞን የኖሌ ካባ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2019 ዓ.ም የበጀት ዘመን የጽሕፈት መሣሪያዎች፣ የጽዳት መሣሪያዎች፣ ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች፤ ቋሚ የኤሌክትሮኒክስ መሣሪያዎች፣ ፈርኒቸሮች ፣ የሕንጻ ግንባታ መሣሪያዎች፣ የመንግሥት ሠራተኞች የደንብ ልብስ፣ ፍራሾች፣ ብርድ ልብስ፣ አንሶላ እና ትራስ፣ ሞተር ሳይክል፣ ጀኔሬተር፣ ፎቶ ኮፒ፣ ሞንታርቦ፣ ዲጅታል ቪድዮ ካሜራ እና የውሃ ግንባታ መሣሪያዎች

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

በምዕራብ ወለጋ ዞን የኖሌ ካባ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2019 ዓ.ም የበጀት ዘመን የጽሕፈት መሣሪያዎች፣ የጽዳት መሣሪያዎች፤ ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች፤ ቋሚ የኤሌክትሮንክሰ መሣሪያዎች፣ ፈርኒቸሮች፣ የሕንጻ ግንባታ መሣሪያዎች፣ የመንግሥት ሠራተኞች የደንብ ልብስ፣ ፍራሾች፣ ብርድ ልብስ፣ አንሶላ እና ትራስ፣ ሞተር ሳይክል፣ ጀኔሬተር፣ ፎቶ ኮፒ፣ ሞንታርቦ፤ ዲጅታል ቪድዮ ካሜራ እና የውሃ ግንባታ መሣሪያዎች በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

መስፈርት

1. ሕጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የ2018 ዓ.ም የንግድ ፍቃዳቸው ማደሳቸውን ከሚመለከተው መ/ቤት የተመዘገቡበት የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል እንዲሁም ተጨማሪ ዕሴት ታክሰ ( VAT ) ተመዝጋቢ መሆናቸውን ሕጋዊ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ

2. ያሸነፈበትን ዕቃ በተፈለገበት ጊዜ እስከ ኖሌ ካባ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ድረስ በራሱ ትራንስፖርት አምጥቶ ማስረከብ የሚችል

3. ተጫራቾች የተወዳደሩባቸው ዕቃዎች ሁሉ ጥራቱ የተጠበቀ መሆን አለበት ጥራቱን ያልጠበቀ ዕቃ ካቀረቡ መልሰው መቀየር አለባቸው አለበለዚያ ተቀባይነት አይኖረውም።

4. በወረዳው የገንዘብ ጽ/ቤት የገበያ ጥናት ተመጣጣኝ ዋጋ ለማቅረብ ፍቃደኛ መሆን የሚችል።

5. ተወዳዳሪው ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ CPO ወይም 20,000 (ሃያ ሺህ ) ብር በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ የሚችል።

6. ተጫራቾች የተጠየቁትን ዕቃ ሁሉ ዋጋ ሞልተው ማቅረብ አለባቸው። አለበለዚያ ከውድድሩ ውጪ “ይሆናሉ።

7. አሸናፊው ያሸነፈበትን ዕቃ ሁሉ በአንድ ላይ ውል በፈረመበት ጊዜ ውስጥ ማቅረብ አለበት። በተናጠል ካቀረበ ( አጠቃሎ ሳይጨርስ) ገንዘቡ አይሰጠውም

8. በአቅራቢዎች ምዝገባ የተመዘገበበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።

የአቅራቢው ግዴታ

1. የጨረታ ማስታወቂያ ሠነድ የማይመለስ ለአንዱ ሰነድ ግዥ 100 ብር (አንድ መቶ ብር ) በመክፈል በኖሌ ካባ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 2 መግዛት የሚችል።

2. የጨረታ ሠነድ (የዕቃው ዝርዝር) ፋይናንስ ኦሪጅናልና ኮፒውን በተለያየ ፖስታ በማሸግ ሁለቱንም በአንድ ፖስታ በሰም በማሸግ የራሱን ፊርማና የድርጅቱን ማኅተም አድርጎበት በታሸገ ፖስታ የሚያቀርብ

3. የጨረታ ሠነድ ቴክኒክ ኦርጅናልና ኮፒውን በተለያዩ ፖስታ በማሸግ ሁለቱንም በአንድ ፖስታ በማሸግ የራሱን ፊርማና የድርጅቱን ማህተም አድርጎበት በታሸገ ፖስታ የሚያቀርብ

4. አሸናፈው የውል ስምምነት ማስከበሪያ በመመሪያ መሠረት አሸናፊ ከሆኑ ቀን ጀምሮ በ15 (አስራ አምስት) ቀናት ውስጥ ከጠቅላላው ግዥ 10% ጥሬ ገንዘብ በባንክ በተረጋገጠ ቼከ/ማስያዝ የሚችል።

5. ተጫራቾች /ተወዳዳሪው/ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት የዕቃውን ናሙና ማቅረብ አለበት።

6. የጨረታ አሸናፊ በተጫራቾች መመሪያ በተጠቀሰው መሠረት የጨረታው አሸናፊነቱ በጽሑፍ እንደ ተገለጸ እስከ 15 ቀን ውስጥ በኖሌ ካባ ገንዘብ ጽ/ቤት መጥተው ውል መፈረም አለበት ይህ ባይፈጸም የጨረታ አሸናፊነቱን በመሰረዝ ለጨረታው ማሰከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለመንግሥት ገቢ ይሆናል።

7. የጨረታ አሸናፊ ባሸነፈበት ዕቃ ሁሉ የሁለት ወር ዋስትና መሰጠት የሚችል።

የጽ/ቤቱ መብት

  • ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብት አለው።

ጨረታው የሚጠናቀቅበትና የሚከፈትበት ቀን

  • ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21/ሃያ አንድ/ የሥራ ቀናት ብቻ ይቆያል።
  • ጨረታው በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 የሥራ ቀናት በኖሌ ካባ ገንዘብ ጽ/ቤት በመቅረብ የዕቃው ዝርዝር ሰነድ መግዛት የሚችሉና ተወዳዳሪዎች ( ወኪሎቻቸው) በተገኙበት ቦታ በ22ኛ ቀን በ4፡00 ሰዓት ላይ ይከፈታል ሆኖም ቀኑ በዓል የእረፍት/ቀን ላይ ከዋለ በቀጣይ የሥራ ቀን ይከፈታል።
  • ለተጨማሪ መረጃ በሚከተሉት የስልክ ቁጥሮች ሊጠይቁ ይችላሉ።

09 17 35 44 11 / 09 79 57 92 90

በምዕራብ ወለጋ ዞን የኖሌ ካባ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-25
  • Bid closing time: 17:30
  • Bid closing (note): ጨረታው በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 የሥራ ቀናት
  • Bid opening: 2026-08-26 10:00
  • Bid opening (note): ጨረታው በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 የሥራ ቀናት ቆይቶ ቀጥሎ ባለው በ22ኛ ቀን በ4፡00 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Nole Kaba Woreda Finance & Economic Development Office
  • Bid bond: 20,000.00 ብር
  • Bid document price: 100.00 ብር ለአንዱ ሰነድ
  • Published on: Addis Zemen (Aug 02, 2026)
  • Posted at: 2026-08-03T13:19:23.000Z
← Back to all tenders