Vehicle rental

የድሬዳዋ አስተዳደር ገቢዎች ባለስልጣን የፋይናንስ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት 2019 በጀት ዓመት ተሽከርካሪ መኪና በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመከራየት ይፈልጋል

Description

ተሸከርካሪ መኪና ኪራይ  የጨረታ ማስታወቂያ

የጨ/መ/ቁ ገቢ 004/2019

የድሬዳዋ አስተዳደር ገቢዎች ባለስልጣን የፋይናንስ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት 2019 በጀት ዓመት ከመንግስት በተመደበለት በጀት የባለስልጣኑ ተሸከርካሪ መኪና ኪራይ አገልግሎት ሥራዎች የሚያከናዉኑ ባለንብረቶች ለአንድ ዓመት በሚቆይ ዉል በአካባቢያዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመከራየት ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም፡-

  1. ተጫራቾች በዘርፉ ስራ የተሠማሩና ሕጋዊ የንግድ ፍቃድና በመንግስት የእቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ተመዝግበው የምስክር ወረቀት ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል
  2. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
  3. የዘመኑን ግብር የከፈሉና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው
  4. ተጫራቾች ለተወዳደሩበት ጨረታ አግባብነት ያለው የተሟላ ማስረጃና ሠነድ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፣
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የስራ ቀናት ድረስ የጨረታ ሠነዱን ከፋይናንስ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 26 ቀርበው የማይመለስ ብር 200 በመክፈል መግዛት ይችላሉ ፤ አስፈላጊውን ዋጋ በግልጽ ቫትን ያካተተ መሆን አለመሆኑን በመግለጽ ሞልተው ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዋናውና ኮፒውን በአግባቡ አሽገው ማስገባት ይችላሉ፡፡
  6.  የጨረታ ሳጥኑ በ16ኛ ቀን ጠዋት ልክ 4፡00 ሠዓት ላይ ታሽጎ በዚሁ ዕለት ልክ 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪላቸው በተገኙበት በሥራ ሂደቱ ቢሮ በግልጽ ይከፈታል፡፡
  7. ተጫራቾች ለተሸከርካሪ መኪና ኪራይ ብር 5,ዐዐዐ ብር የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ቼክ፤በጥሬ ገንዘብ፤በባንክ ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት እንዲሁም ከዳራጁት የመንግስት ተቋም በደብዳቤ በሚሰጥ ዋስትና ከነዚህ አማራጮች በአንዱ በመጠቀም ከጨረታ ሠነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  8. መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  9. ተጨማሪ ማብራሪያና መረጃ ቢያስፈልግ በሚከተለው አድራሻ መጠቀም ይችላሉ፡-

የድሬዳዋ አስተዳደር ገቢዎች ባለስልጣን

የግዥ ፋይናንስ ንበረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት

ሞባይል፡- 0915034952/0913398382


Tender details

  • Deadline: 2026-08-15
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ዕለት ጀምሮ በ16ኛ ቀን ጠዋት ልክ 4፡00 ሠዓት
  • Bid opening: 2026-08-15 10:30
  • Bid opening (note): የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ዕለት ጀምሮ በ16ኛ ቀን ጠዋት ልክ 4፡30 ሠዓት
  • Region: Dire Dawa
  • Publishing entity: Dire Dawa Administration Revenue Authority
  • Bid bond: 5000.00 ብር
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published on: Melekite Dire (Jul 29, 2026)
  • Posted at: 2026-08-04T07:15:04.000Z
← Back to all tenders