Addis Ababa

በየካ ክ/ከተማ አስተዳደር ወረዳ 04 ፋይናንስ ጽ/ቤት በበጀት ዓመቱ የተለያዩ አገልግሎቶች እና ዕቃዎችን መግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 001/2019 ዓ.ም

በየካ ክ/ከተማ አስተዳደር ወረዳ 04 ፋይናንስ ጽ/ቤት በበጀት ዓመቱ

  • የተለያዩ የደንብ ልብስ፣
  • ልዩ ልዩ መሣሪያዎች፣
  • መጻሕፍት፣
  • አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፣
  • ሌሎች አላቂ ዕቃዎች፣
  • ቋሚ ዕቃዎች፣
  • የመኪና ዕቃዎች፣
  • ህትመት፣ ሞንታርቦ፣
  • ዲኮር፣ ድንኳን፣
  • የጭነት፣ አይሱዙ፣
  • መስተንግዶ፣ ትራንስፖርት፣ የከተማ ግብርና ዘር አገልግሎቶች እና ዕቃዎችን መግዛት ይፈልጋል። በተጨማሪም በወረዳው ውስጥ የሠራተኛ ካፌ አገልግሎት በጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል።

1. ተጫራቾች በጨረታ ለመካፈል በዘርፉ ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው የዘመኑን ንግድ ፈቃድ ያደሱና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን አለባቸው::

2. ተጫራቾች ቫት ተመዝጋቢና በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የተጫራች መረጃ ያላቸው መሆን አለበት፡፡

3. ተጫራቾች ተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ መሆናቸውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ መረጃ ማቅረብ የሚችሉ::

4. ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታውን ሰነድ መውሰድ ይችላል፡፡

5. ተጫራች ጨረታውን ከመከፈቱ በፊት የጽሕፈት መሣሪያ፣ የጽዳት ዕቃዎች ሌሎችም በሎት የተዘረዘሩት ናሙና የሚያስፈልጋቸውን በዝርዝር ንብረት ክፍል ገቢ ማድረግ አለበት፡፡ ናሙና ያላቀረበ ተጫራች ከጨረታው ውጪ ይሆናል፡፡

6. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ) ዲሁም ከጨረታ እራሳቸውን ማግለል እንደማይችሉ ማወቅ አለባቸው::

7. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ዋና እና ኮፒ በማዘጋጀት በታሸገ ኤንቨሎፕ በአንድ ወይም በሁለት ወጥ ፖስታዎች /ቴክኒክ/ የሚወዳደሩበትን ዓይነት በፖስታው ላይ በመለየት በጋዜጣ ከወጣበት 28/11/2018 ዓ.ም ጀምሮ ለ10 የሥራ ቀናት በወረዳው ፋ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 6 ሰነድ በመውሰድ ለዚህ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

8. ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ12/12/2018 ዓ.ም በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ወጣት ማዕከል አዳራሽ በ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጨረታ ኮሚቴዎች ይከፈታል።

9. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ከሚያቀርቡት ዋጋ ብር ሎት 1/ 31,000.00 ፣ሎት 2/ 28,000.00 ሎት 3/ 33,000.00 ሎት 4/ 13,000.00 ሎት 5/ 6250.00 ሎት 6/ 10,000.00 ሎት 7/ 5,000,00  8/4000.00 በባንክ የክፍያ መያዣ ሰነድ (CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

10. የጨረታው አሸናፊ ለአሸነፉት ዕቃ ዋስትና እና ውል ማስከበሪያ 10% በማስያዝ ውል ስምምነት መፈፀም ይኖርበታል፡፡ የፕሪንተርና የፎቶ ኮፒ ቀለሞች ኦርጂናል ስለመሆኑ ዋስትና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

11. ተጫራቾች የሚያቀርቡት መወዳደሪያ ሰነድ ላይ ፊርማቸውንና አድራሻቸውን በማህተም የተደገፈ መሆን አለበት፡፡

12. ከላይ የተጠቀሱት መስፈርቶች ሳያሟላ በጨረታ ላይ ለመሳተፍ መሞከርና ጨረታውን ከማሳሳትና ለማጭበርበር የሚሞክር ተጫራች ከጨረታ ይሰረዛል፡፡

13. መ/ቤቱ አሸናፊውን ተጫራች በሚመርጥበት ጊዜ የሚገዛውን ዕቃ ወይም አገልግሎት ብዛት (መጠን) እንደአስፈላጊነቱ 20% መቀነስ ወይም የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው::

14. በጥቃቅን የተደራጁ ተጫራቾች ካደራጃቸው አካል ኦርጅናል አምራች መሆናቸው የሚገልፅ ደብዳቤ ማምጣት ይኖርባቸዋል፡፡

15. ተጫራቾች የዕቃ ዝርዝር ዋጋ ስታቀርቡ ከነቫቱ መሆኑን እያሳወቅን ከቫት ውጪ ያቀረበ ከውድድር ውጪ እንደሚሆን እናሳውቃለን፡፡

16. ለሠራተኛ ካፌ የምትወዳደሩ ማቅረብ የሚገባችሁ በካፌ አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎችን በሙሉ ማቅረብ እና በሥራ ላይ የሠሩ መሆናቸውን የሚገልፅ መረጃ ማቅረብ ግዴታ ይኖርባቸኋል፡፡ በመ/ቤቱ መብራት፣ ውሃ፣ ቤት ኪራይ ነፃ ድጋፍ ይደረግላቸዋል፡፡

17. ጨረታው ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ 6ዐ ቀናቶች ይሆናሉ፡፡

18. መ/ቤታችን አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊልም የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

ማሳሰቢያ፡- ከሎት 1 እስከ ሎት 8 ቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው:: ከሎት 9 እስከ ሎት 16 ቲ.ኦ.ቲ/ቫት ተመዝጋቢ መሆን ይኖርባቸዋል።

አድራሻ፡- ሚኒሊክ ሪፈራል ሆስፒታል ሬሳ በር 200 ሜትር ገባ ብሎ

ስልክ ቁጥር፡- 011-126-10-63/011-112-10-50

በየካ ክ/ከተማ አስተዳደር ወረዳ 04 ፋይናንስ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-18
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-08-18 10:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Yeka sub City Administration woreda 04 finance office
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 200.00 ብር ለእያንዳንዱ ሎት
  • Published on: Addis Zemen (Aug 04, 2026)
  • Posted at: 2026-08-04T08:22:45.000Z
← Back to all tenders