Vehicle rental

በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ የወረዳ 02 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት የተለያዩ አገልግሎቶችን በግልጽ ጨረታ በኮንትራት፣ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር 001/2019

በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ የወረዳ 02 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ሎቶች የአገልግሎት ጨረታ በግልጽ ጨረታ በኮንትራት፣ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል።

  • ሎት 1 የሕዝብ ቅጥቅጥ መኪና ኪራይ/6252/
  • ሎት 2 የጭነት መኪና ኪራይ /6252/
  • ሎት 3 የዲኮር እና ድንኳን ኪራይ/6252/
  • ሎት 4 የሕትመት ሥራ/6213/
  • ሎት 5 መስተንግዶ/6233/
  • ሎት 6 ፈርኒቸር ጥገና/6244/
  • ሎት 7 የኤሌክትሮኒክስ ጥገና /6243/
  • ሎት 8 የሕንፃ ጥገና ዕቃ አቅርቦት/6244/

በዚሁም መሰረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርት የምታሟሉ ተጫራቾች መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

1. ተጫራቾች ከሥራው ዘርፍ ጋር አግባብነት ያለው የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ሥራ ፍቃድ ያለው የዘመኑ ግብር መክፈላቸውን የሚገልፅ ማስረጃ (Tax clearance) ማቅረብ የሚችል።

2. ተጫራቾች የቫት ተመዝጋቢ የሆኑበትንና Tin number ማስረጃ ኮፒውን አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር 400 (አራት መቶ) ብር በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።

4. ተጫራቾች ለሚጫረቱባቸው ሎቶች የጨረታ ማስከበሪያን በተመለከተ ለሎት 1፡- 3,000.00 ብር፣ ለሎት 2 ፡3,000.00 ብር፤ ለሎት 3፡- 2,500.00 ብር፣ ለሎት 4፡-2,500.00 ብር፣ ለሎት5፡ 3,500.00 ብር፣ ለሎት 6፡ 2,500.00 ብር፣ ለሎት 7፡- 2,500.00 ብር፣ ለሎት 8፡ 3,000.00 ብር፣ በተቋሙ ስም የተዘጋጀ ሲፒኦ ከኦርጅናል ሰነዳችሁ ጋር ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

5. በጥቃቅን አነስተኛ ተቋማት የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በጨረታ ማስከበሪያ በውል ማስከበሪያ እና በቅድሚያ ከፍያ ዋስትና ምትክ ተቋሙ ካደራጃቸው አካል የሚሰጥ የዋስትና ደብዳቤ በጽ/ቤቱ ኃላፊ የተፈረመ ደብዳቤ እና የስም ቲተር እና የስራ ድርሻ እንዲሁም ክብ ማህተም ያሟላ ደብዳቤ ተቀባይነት ይኖረዋል።

6. የጨረታ ሰነዱ የሚገኝበት ቦታ በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 ፋይናንስ ጽ/ቤት 4ኛ ፎቅ ካሸሪ ከፍል ይገኛል።

7. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ሎት ከላይ የተዘረዘሩ የሰነድ ማስረጃዎች በማካተት ኦርጅናልና ኮፒውን በተለያየ ፖስታ በማሸግ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት ተከታታይ አስር የሥራ ቀናት ውስጥ በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 አስተዳደር በናሙና ከፍል በተዘጋጀው የአገልግሎት ጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

8. ማንኛውም ተጫራች የሚጫረቱበትን የእቃ ናሙና በተመረጡ ሎት እና ሌሎች ናሙና ማቅረቢያ ዘዴ የጨረታ ሣጥኑ ከመታሸጉ በፊት በማዳበሪያ ናሙና ሲረከብ ለተመደበው አካል ማስረከብ ና ማስፈረም እንዲሁም በእያንዳንዱ ዕቃ ላይ ማህተም መደረግ ይኖርባቸኋል፡፡ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት በአየር ላይ ቆይቶ በ11ኛው ቀን ጠዋት በ3፡30 ሰዓት ታሽጎ በ4፡00 ሰአት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት በወረዳው ናሙና ክፍል ይከፈታል።

9. ተጫራቾች ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ወይም የበአል ቀን የሚውል ከሆነ ቀኑን አሳልፈን የሚከፈት መሆኑን ማወቅ አለባቸው።

10. የአገልግሎት እቃ አቅርቦት ላይ መ/ቤቱ ከአሸናፊው ተጫራች ጋር ውል ከመፈራረሙ በፊት በጨረታ ሰነዱ ከተገለጸው የአቅርቦት መጠን ላይ መጨመር ወይም መቀነስ አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው በአሸናፊው ተጫራች የቀረበው ከውድድሩ የተገኘው ዋጋ ሳይቀየር እስከ 20% /ሃያ በመቶ/ መጨመር ወይም መቀነስ ይችላል።

መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- ካራ ቆሬ 36 ቁ. አውቶቡስ ማዞሪያ

ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 011-318-55-10

የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-15
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ጠዋት በ3፡30 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-08-15 12:00
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ጠዋት በ4፡00 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Kolfe Keranio Sub City Woreda 2 FEDB
  • Buyer address: ካራ ቆሬ 36 ቁ. አውቶብስ ማዞሪያ
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: ለእያንዳንዱ ሎት 400 (አራት መቶ) ብር
  • Published on: Addis Zemen (Aug 04, 2026)
  • Posted at: 2026-08-04T08:55:03.000Z
← Back to all tenders