Well drilling and boreholes
ሲዳማ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ለገመጦ ጥልቅ ውሃ ጉድጓድ ቁፋሮ ፕሮጀክት ጉድጓድ የማበልጸግ /ፓምፕ ቴስት/ ስራ በጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
ሀገር አቀፍ ግልፅ ጨረታ ቁጥር 05/2018
ሲዳማ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ለገመጦ ጥልቅ ውሃ ጉድጓድ ቁፋሮ ፕሮጀክት ጉድጓድ የማበልጸግ /ፓምፕ ቴስት/ ስራ በጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚችሉ ተጫራቾች
1. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ፍቃድ ያላቸው
2. ቫት የተመዘገቡ
3. በጨረታ ለመሣተፍ ከገቢዎች ፍቃድ ያላቸው
4. የመልካም ሥራ አፈፃፀም ማስረጃ ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል
የጨረታ ሰነድ የሚሸጥበት ጊዜና ቦታ፦
1. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15 ተከታታይ ቀናት ድረስ የማይመለስ ብር 300.00/ሶስት መቶ ብር/ በሲዳማ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን የሂሳብ ቁጥር 1000604259658 በኢትዮጲያ ንግድ ባንክ ገቢ በማድረግ የንግድ ፍቃዳቸውን ፎቶ ኮፒ ይዘው በመቅረብ ሲዳማ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን ሀዋሳ ከአዲሱ ገበያ ከፍ ብሎ ጊዮርጊስ ቤ/ክ አጠገብ ከሚገኘው ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ የጨረታ ሰነድ መግዛት ይቻላሉ፡፡
ጨረታው የሚከፈትበት እና ሰነዱ የሚቀርብበት ጊዜ፦
1. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከቀኑ ከ8:30 እስከ 11፡00 ሰዓት በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ያስገባሉ ::
2. በማግስቱ በ12ኛው ቀን ከጠዋቱ በ3:30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
3. ዕለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለዉ የስራ ቀን ይከፈታል ::
የጨረታ ዋስትና ፦
1. ማንኛውም ተጫራች 2% በባንክ የተረጋገጠ CPO ወይም ከስድስት ወር ያላነሰ ጊዜ ያለው በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ቢድቦንድ ዋስትና ከዋጋ ማቅረቢያ ጋር አያይዞ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
የጨረታ ሠነድ አስተሻሸግ ሁኔታ ፦
1. የዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ማስረጃ ፣ የልዩ እሴት ታክስ ተመዝጋቢነትና የታክስ ክፍያ ማረጋገጫ ሰነዶች ፣ በጨረታው ለመሳተፍ ከገቢዎች የተሰጠ ማስረጃ እና የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተደገፈ CPO/ ከኦርጂናል የዋጋ ማቅረቢያ ጋር በአንድ ላይ በሰም ታሽገው መቅረብ አለባቸው፡፡ ፋይናንሻል ዶክመንት ኦርጅናልና ኮፒ ለየብቻ በሰም ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል፡፡
2. ቴክኒካል ዶክመንት ኦርጅናልና ኮፒ ለየብቻ በሰም ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል፡፡
ይህንን አስተሻሸግ ዘዴ ያልተጠቀመ ተጫራች ከጨረታው ይሠረዛል፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0916 071 539 / 0911 806 709 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
ኮርፖሬሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ሲዳማ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን(ሲኮስኮ)
Tender details
- Deadline: 2026-08-13
- Bid closing time: 17:00
- Bid closing (note): ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከቀኑ ከ8:30 እስከ 11፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-08-14 09:30
- Bid opening (note): ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ12ኛው ቀን ከጠዋቱ በ3:30 ሰዓት
- Region: Sidama
- Publishing entity: Sidama Construction Works Corporation
- Bid bond: 2%
- Bid document price: 300.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Aug 03, 2026)
- Posted at: 2026-08-04T10:29:28.000Z