Disposal, scrap and surplus sales

በአዊ/ብሔ/አስ/ዞን/ አካባቢ ጥበቃ ተጠሪ ጽ/ቤት የአን/ጓ/ወ/ አካባቢ ጥበቃ ተጠሪ ጽ/ቤት እና የአን ጓ/ወ/ ስፖርት ጽ/ቤት ለሽያጭ የሚውሉ ባህር ዛፍ እና ዲክራሲ ግራር መሸጥ ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በአዊ/ብሔ/አስ/ዞን/ አካባቢ ጥበቃ ተጠሪ ጽ/ቤት የአን/ጓ/ወ/ አካባቢ ጥበቃ ተጠሪ ጽ/ቤት እና የአን ጓ/ወ/ ስፖርት ጽ/ቤት ለሽያጭ የሚያውለው ባህር ዛፍ እና ዲክራሲ ግራር ሽያጭ

  • ሎት 1. በአን/ጓ/ወረዳ በካፍታ ቀበሌ በበካፍታ ዮሐንስ ጎጥ ልዩ ስሙ ገፊ ላይ የሚገኘውን የማህበረሰብ ባህር ዛፍና ዲከርንስ ግራር ደን የጨረታ ማስከበሪያ ብር 12,797 (አስራ ሁለት ሽህ ሰባት መቶ ዘጠና ሰባት ብር) ፣
  • ሎት 2. በአዊ ብሄ//ዞን በአገው ግ/ቤት ክ/ከተማ በወረዳው ሁለገብ የስፖርት ማዘውተሪያ ሜዳ ላይ ያለ ባህር ዛፍ 2 ቃዳ መሬት ላይ የሚገኝ ባህር ዛፍ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 80,000 (ሰማኒያ ሽህ ብር) ብቻ በማስያዝ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ 

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

  1. በአጣና ግንዲላ ወይም በጣዉላ ንግድ የተሰማሩ ተጫራቾች የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና በዘመኑ ግብር ከፍለዉ ያጠናቀቁ ስለመሆናቸዉ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. ተጫራቾች የደን ዉጤቱን የሚገዙበት ክልል መነሻ በማድረግ በመመሪያዉ መሰረት የሚከፈሉባቸዉ የደን አይነቶች የዋጋ መጠን ግልጽ በሆነ ጽሁፍ በትክክል ሞልተዉ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሣተፍ ከላይ ከተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና ማስረጃዎችን ማለትም የታደሰ ንግድ ፈቃድ ቲን ሰርተፊኬት የማይመለስ ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ፖስታ ውስጥ በማስገባት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  5. የጨረታዉ አሸናፊ ያሸነፉበትን ዋጋ 13 በመቶ የሮያሊቲ ክፍያ ቅድሚያ መክፈል ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ለጨረታ የሚቀርበዉ ዋጋ መግለጫ ስርዝ ድልዝ የሌለበት ሁኖ በተጫራቹ በራሱ ወይም በህጋዊ ወኪል አማካኝነት ተሞልቶ ተፈርሞ ማህተም ካለዉ ተደርጎበት መቅረብ ይኖርበታል፡፡ ስርዝ ድልዝ ካለም ዋጋዉን በሞላዉ ሰዉ ፓራፍ መደረግ ይኖርበታል፡፡
  7. ተጫራቾች የተወዳደሩበትን ባህር ዛፍና ዲከረንስ ግራር በአን/ጓ/ወ በበካፍታ ቀበሌ በካፍታ ዮሐንስ ጎጥ ልዩ ስሙ ገፊ ደን ድረስ እና አን/ጓ/ወ/ግ/ቤት ከተማ ድረስ በመሄድ ማየት ይችላሉ ፡፡
  8. ለጨረታዉ የሚቀርበዉ ዋጋ እስከ 90 ቀናት ድረስ ፀንቶ ይቆያል ፡፡
  9. በጨረታ ተካፋይ የሆነ ተወዳዳሪ በጨረታ ሳጥን የመወዳደሪያ ዋጋ የማስገቢያ ቀን ከተጠናቀቀ በኋላ ዋጋን መለወጥ ማሻሻል ወይም በጨረታ አልሳተፍም ማለት አይችልም፡፡ አልሳተፍም ብሎ ካወጣም የጨረታ ማስከበሪያ ለመንግስት ገቢ ይደረጋል፡፡
  10.  ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን (በግልፅ ጨረታ) በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 20 ቀናት እስከ 11፡30 ድረስ በስራ ሰዓት የጨረታ ሰነዱን አን/ጓ/ወ/ ገንዘብ ጽ/ቤት ፋይናንስ ቡድን በማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) መግዛት ይችላሉ፡፡
  11. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ ድምር  10 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በወረዳው የገቢ ደረሰኝ ወይም በመሂ-1 ገቢ በማድረግ የደረሰኙን ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማያያዝ አለባቸው፡፡
  12. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በጥንቃቄ በፖስታ በማሸግ አን/ጓ/ወ ገንዘብ /ጽ/ቤት ወይም ቢሮ ቁጥር 09 በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በሥራ ሠዓት ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ21ኛ ቀን እስከ ጠዋቱ 4፡00 ድረስ የጨረታ ሣጥን ከሚታሸግበት የመጨረሻ ሰዓት እና ደቂቃ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  13.  ማንኛዉም ተጫራች በሌሎች ተጫራቾች ዋጋ ተመስርተዉ ዋጋ ማቅረብ አይችሉም፡፡
  14. የጨረታዉ አሸናፊ ከታወቀ በኋላ አሸናፊ ላልሆኑት የጨረታ ማስከበሪያ ወዲያዉኑ ይመለስላቸዋል፡፡
  15. ተጫራቹ አሸናፊ መሆኑ ከተገለፀበት እስከ 15 ቀን ባለዉ ጊዜ ዉስጥ የዋጋዉን 10 በመቶ የስራ ዋስትና በማስያዝ ቀርቦ ዉል ይፈርማል፡፡
  16. የዉል ግዴታዉን ያልተወጣ ተጫራች ያስያዘዉ የጨረታ ማስከበሪያ ይወረስበታል፡፡ ተጨማሪ ጉዳት ካደረሰ በህግ ሊጠየቅ ይችላል፡፡
  17. አሸናፊው ተጫራች ያስያዘዉ የጨረታ ማስከበሪያ የሚመለስልት ዉሉን ከፈፅመ በኋላ ነው፡፡
  18. የመጫረቻ ዋጋ በአሃዝ እና በፊደል በግልፅ መፃፍ ይኖርበታል፡፡ በአሃዝና በፊደል በተሞላዉ ዋጋ መካከል ልዩነት ቢኖር በፊደል የተሞላዉ እና በነጠላ ዋጋ ላይ የተቀመጠው ተቀባይነት ይኖረዋል፡፡
  19. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አን/ጓ/ወ/ገንዘብ /ጽ/ቤት በቢሮ ቁጥር 08 በ21ኛው ቀን የጨረታ ሣጥኑ ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጐ ከጠዋቱ 4፡15 ይከፈታል፤ ተጫራቾች ወይም ወኪሎች ካልተገኙ የጨረታ ሰነዱ እንዲከፈት ተደርጎ ያልተገኙ ተጫራቾች ግን በእለቱ ለሚተላለፈው ውሳኔ ተገዥ ይሆናሉ፡፡
  20. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  21. በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 058 224 0345/058 224 0520//09 18 26 9613/09 19 44 7123 በመደወል ማብራሪያ ማግኘት ይችላሉ፡፡

ማሳሰቢያ፡- 

ተጫራቾች ኮሚቴ የቆጠረዉን ባህር ዛፍና ዲከረንስ ግራር ደን የጨረታ ሰነድ ከመግባቱ በፊት በትክክል ቆጥረዉ መወዳደር ይችላሉ፡፡ አሸናፊዉ፤ ካሸነፈ በኋላ ጉድለት ካለ ኮሚቴዉ አያስተናግድም ቀድመዉ በመቁጠር ይወዳደሩ የቁጥር ስህተት ካለ ቀድመዉ ለኮሚቴዉ ያመልክቱ አሸናፊዉ ድርጅት በጨረታ ጊዜ ባሸነፈዉ ዋጋ መጠን ልክ ርክክብ ስለሚፈፀም በጥንቃቄ መሙላት ያስፈልጋል፡፡

የአን/ጓ/ወ/አካ/ጥ/ ተጠሪ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-24
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): የጨረታ ሰነዱን (በግልፅ ጨረታ) በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ21ኛው ቀን የጨረታ ሣጥኑ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-08-24 12:00
  • Bid opening (note): የጨረታ ሰነዱን (በግልፅ ጨረታ) በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ21ኛው ቀን የጨረታ ሣጥኑ ከጠዋቱ 4፡15 ሰዓት
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: የአን/ጓ/ወ/አካ/ጥ/ ተጠሪ ጽ/ቤት
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published on: Be'kur (Aug 03, 2026)
  • Posted at: 2026-08-04T11:44:32.000Z
← Back to all tenders