Vehicle rental
በሸገር ከተማ አስተዳደር የሲዳ አዋሽ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 የበጀት ዓመት ለወረዳው አገልግሎት የሚውሉ ፒካአፕ (pickup) እና ኮሮላ (Corolla)መኪና መከራየት ይፈልጋል
Description
ማስታወቂያ
በሸገር ከተማ አስተዳደር የሲዳ አዋሽ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 የበጀት ዓመት ለወረዳው አገልግሎት የሚውሉ ፒካአፕ(pickup) እና ኮሮላ(Corolla) መኪና መከራየት ይፈልጋል።
በዚህም መሰረት ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶችን በማሟላት በጨረታው እንዲሳተፍ ይጋብዛል።
1. በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የዘኑ ግብር የከፈሉ።
2. በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡና የተጨማሪ እሴት ታክስ(VAT),TIN ተመዝጋቢ የሆኑና የምስክር ወረቀት ያላቸው
3. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣ ቀን ጀምሮ ባሉት 15(አስራ አምስት) ተከታታይ የሥራ ቀናት ለአንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 1000(አንድ ሺህ ብር) በሲዳ አዋሽ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት በመክፈል ሰነዱን ከሲዳ አዋሽ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት መውሰድ ይችላሉ።
4. ተጫራቾች የሚያቀርቡበትን የዋጋ ማቅረቢያ ዝርዝር ሰነድ ዋና እና ኮፒ ለየብቻ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ /ፖስታ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15(አስራ አምስት) ተከታታይ የሥራ ቀናት ድረስ በሲዳ አዋሽ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
5. በ16ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ(ተዘግቶ) ልክ በዚሁ ቀን ከረፋዱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወክሎቻቸው በተገኙበት በሲዳ አዋሽ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት ይከፈታል። ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል። ነገር ግን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወክሎቻቸው የማይገኙ ከሆነ ጨረታውን ከመክፈት አይግደውም።
6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 20,000 (ሃያ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ/ CPO/ ብቻ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
7. ተጫራቾች የጨረታ አሸናፍነታቸው ከተገለፀላቸው በኃላ የውል ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ 10% በማስያዝ ውል መዋዋል ይጠበቅባቸዋል።
8. ተጫራቾች የጨረታ አሸናፍነታቸው ከተገለፀላቸው በኃላ በተገለፀላቸው ቀን ቀርቦው ውል ካልፈፀሙና የውል ማስከበርያ ካልስያዙ የጨረታ ማስከበሪያው ለንግስት ገቢ ይሆናል።
9. ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኃላ በጨረታው ሰነድ ላይ የተገለጹትን ማንኛውንም ሁኔታዎች መለወጥ ወይም ማሻሻል ወይም ጨረታውን ትቻለው ማለት አይችልም።
10. የመወዳደሪያ በጨረታ ሰነዱ በተዘረዘረው መሠረት ተሞልቶ መቅረብ ይኖርበታል።
11. የመንግስት ፋይናንስ ህግ እና መመሪያን የሚጥስ ማንኛውም ነገር ተቀባይነት የለውም።
12. መ/ቤቱ የተሸለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
13. ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 09 41 34 05 08/ 09 12 04 75 66 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ።
አድራሻ በሸገር ከተማ ገላን ክ/ከ ሲዳ አዋሽ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
በሸገር ከተማ አስተዳደር የሲዳ አዋሽ ወረዳ
ገንዘብ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-08-22
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-08-22 10:30
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን 4፡30 ሰዓት
- Region: Oromia
- Publishing entity: የሲዳ አዋሽ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
- Bid bond: 20,000 (ሀያ ሺህ ብር)
- Bid document price: 1000 (አንድ ሺህ ብር)
- Published on: Addis Zemen (Aug 05, 2026)
- Posted at: 2026-08-05T07:22:02.000Z