Vehicle rental

የኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ አስተዳደር የተለያዩ እቃዎችን አወዳድሮ አገልግሎት ለመፈጸም ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 01/2019

የኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ አስተዳደር ከዚህ በታች የተጠቀሰው የአገልግሎት ግዥ ለ2019 በጀት ዓመት አወዳድሮ አገልግሎት ለመፈጸም ይፈልጋል።

  • ሎት 1. የመኪና ኪራይ
  • ሎት 2. የህትመት ሥራ አገልግሎት
  • ሎት 3. ዲኮር መድረክ እና ድንኳን ኪራይ
  • ሎት 4. የኤሌክትሮኒክስ ጥገና
  • ሎት 5.የኬተሪንግ አገልግሎት
  • ሎት 6. የመኪና ጥገና

ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶችና ግለሰቦች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋበዛሉ።

በዚህም መሰረት ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ሁኔታዎች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።

7. አግባብነት ያለው የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ የቫት ተመዝጋቢዎች የሆኑ።

8. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ ፑል አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት ግዥ ቡድን በመገኘት የማይመለስ ብር 400.00 (አራት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል የጨረታዉን ሰነድ መግዛት ይችላሉ።

9. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚጫረቱበት የጨረታ ሎት ዓይነት ህትመት 20,000 (ሀያ ሺህ ብር) መኪና ኪራይ 50,000 (ሀምሳ ሺህ ብር) ዲኮር መድረክ እና ድንኳን ኪራይ 30,000 (ሰላሳ ሺህ ብር) ኤሌክትሮኒክስ ጥገና 10,000 (አስር ሺህ ብር) የኬተሪንግ አገልግሎት 50,000 (ሀምሳ ሺህ ብር) የመኪና ጥገና 50,000 (ሀምሳ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ (CPO) ከዋጋ ማቅረቢያ ጋር በታሸገ ኤንቨሎፕ በተዘጋጀው ሣጥን ማስገባት አለባቸው።

10. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ሰነድ የስራውን ዝርዝር የሚገልጽ ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ሰነድ ለየብቻ ዋናውን (ኦርጅናል) እና የማይከፈት ኮፒ በታሸገ ፖስታ የድርጅቱን ስምና አድራሻ በመጥቀስ የድርጅቱ ማህተም ያረፈበትን ፖስታ ከላይ በተጠቀሰው ቢሮ ለዚህ አገልግሎት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዛው ቀን 4፡30 ላይ ይከፈታል የጨረታው መክፈቻ ቀን በዓል ከሆነ በማግስቱ ባለው የስራ ቀን 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ 4፡30 ይከፈታል።

ተጫራቾች የሚያቀርቡበት የነጠላ ዋጋ በሰነዱ ላይ በመግለጽ ሙሉ አድራሻና ማህተም መጠቀም አለባቸው።

የተሻለ አማራጭ ዘዴ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ማሳሰቢያ፡-ሙሉ ኦርጅናል የጨረታ ሰነድ ዋጋ ተሞልቶበት ህጋዊ ማህተም እና በየገፁ ፊርማ ተደርጐበት መመለስ አለበት ካልተመለሰ ከጨረታ የሚሰረዝ መሆኑን እንገልጻለን።

2. ለህትመት ስራ ሳምፕል መቅረብ አለበት

አድራሻ፡- ቤተል ከጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን አጠገብ ያለው ህንጻ ላይ ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር

ዋና ስራ አስፈጻሚ ፑል የአስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ግዥ ቡድን 8ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 02

ስልክ ቁጥር 011 834-0979

የኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ የዋና ሥራ አስፈጻሚ ፑል

የአስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-17
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-08-17 10:30
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Kolfe Keranio Sub City Administration Pool Management Finance Office
  • Buyer address: ቤተል ከጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን አጠገብ ያለው ህንጻ ላይ ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የዋና ስራ አስፈጻሚ ፑል የአስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት የመንግስት ግዥ አስተዳደር ቡድን 6ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 605
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 400.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Aug 05, 2026)
  • Posted at: 2026-08-05T07:30:07.000Z
← Back to all tenders