Audio-visual, photography and graphic design

የኢትዮጵያ ልማት ባንከ አዳማ ዲስትሪክት የዶሎማይት ማምረቻ ማሽን እና አንድ ዊል ሎደር በዝግ ጨረታ አወዳድሮ በጥሬ ገንዘብ መሸጥ ወይም የባንኩን መስፈርት ለሚያሟሉ መልሶ ማከራየት ይፈልጋል

Description

የሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ልማት ባንከ አዳማ ዲስትሪክት ከዚህ በታች በሰንጠረዥ ውስጥ ስሙ የተጠቀሰው ተከራይ በካፒታል ዕቃ ዱቤ ግዥ እና ኪራይ ውሉ መሰረት ግዴታውን ባለመወጣቱ ምክንያት ባንኩ በአዋጅ ቁጥር 103/90 እና 807/2005 በተሠጠው ስልጣን መሰረት ከተከራዩ መልሶ የተረከበውን የካፒታል ዕቃዎችን በዝግ ጨረታ አወዳድሮ በጥሬ ገንዘብ መሸጥ ወይም የባንኩን መስፈርት ለሚያሟሉ መልሶ ማከራየት ይፈልጋል።

የካፒታል ዕቃ ተከራይ ስም

የሚሸጠው ንብረት

የጨረታ መነሻ ዋጋ (ብር)

የሚሸጠው ንብረት የሚገኝበት ቦታ

የጨረታ ደረጃ

 

ጨረታ የሚካሄድበት ቦታ፣ ቀን እና ሰዓት

ኤክሶደስ ኬሚካል አስመጪ ኃላ/የተ/የግ/ማህበር

የዶሎማይት ማምረቻ ማሽን እና አንድ ዊል ሎደር

64,093,679.68

 

ቢሾፍቱ ከተማ፣ ዱከም ክ/ከተማ

1ኛ

በኢትዮጵያ ልማት ባንክ አዳማ ዲስትሪክት መ/ቤት ነሐሴ 14 ቀን 2018 ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት

ማሳሰቢያ

1. ተጫራቾች የጨረታውን መነሻ ዋጋ 20% (ሃያ በመቶ) የባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲፒኦ) ብቻ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ።

2. የጨረታ ሰነዱን ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ አዳማ ዲስትሪክት በመውሰድ የሚገዙበትን ዋጋ በመጥቀስ ሌሎች አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎች ጋር በታሸገ ኤንቨሎፕ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ነሐሴ 14 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ድረስ ማስገባት አለባቸው።

3. በጥሬ ገንዘብ አሸናፊ የሆነው ተጫራች ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ 15% የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ጨምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ካልከፈለ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ የሽያጭ ጨረታው ውጤቱ ይሰረዛል።

4. ሕጋዊ ሰውነት ያላቸው ድርጅቶች በመወከል በሽያጭ ጨረታ ላይ የሚሳተፍ ግለሰብ የተረጋገጠ ዋና የውክልና ስልጣን ይዞ መቅረብ ይኖርበታል።

5. ባንኩ ለጥሬ ገንዘብ ተጫራች ቅድሚያ የሚሰጥ ሲሆን፤ ካፒታል ዕቃውን መልሶ መከራየት የሚፈልግ ተጫራች የባንኩን የሊዝ ፋይናንሲንግ መስፈርት ማሟላት ይኖርበታል።

6. አሸናፊው ያስያዘውን ገንዘብ ከግዢው ዋጋ ሲታሰብለት ለተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ሲፒኦ ተመላሽ ይደረጋል።

7. በጥሬ ገንዘብ የጨረታው አሸናፊ የጉምሩክ ቀረጥና ታክስ ነጻ መብት ሊኖረው አሊያም በመንግስት የሚፈለገውን ቀረጥ ለመክፈል ይገደዳል።

8. የጥሬ ገንዘብ ጨረታው አሸናፊ 15% የተጨማሪ እሴት ታክስን ጨምሮ ሌሎች ገዢ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰኑ ክፍያዎችን እንዲሁም የስም ዝውውር ክፍያ ጨምሮ ገዢው ይከፍላል።

9. አሸናፊ ተጫራች ማሽኑን ካለበት ማምረቻ ቦታ መውሰድ አሊያም ከይዞታ ባላቤቱ ጋር መስማማት ይኖርበታል።

10. ዝርዝርና ተጨማሪ መረጃ በተመለከተ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አዳማ ዲስትሪክት መስሪያ ቤት በአካል በመቅረብ ማነጋገር ወይም በስልክ ቁጥር፡- 022-211 66-87 ላይ መደወል ይቻላል። ንብረቱን መጎብኘት የሚፈልግ ተጫራች ከዲስትሪክቱ ጋር አስቀድሞ ቀጠሮ በማስያዝ መጎብኘት ይችላሉ።

11. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አዳማ ዲስትሪክት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-20
  • Bid closing time: 09:00
  • Bid opening: 2026-08-20 10:00
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: Development Bank of Ethiopia
  • Buyer address: DBE Head Office, Property and Facility Management Directorate Procurement Team, Tower II,5th floor,
  • Bid bond: 20%
  • Published on: Addis Zemen (Aug 05, 2026)
  • Posted at: 2026-08-05T08:28:27.000Z
← Back to all tenders