Pharmaceuticals and medicines

የይ/ዓለም ሆስፒታል ህክምና ኮሌጅ የተለያዩ ዕቃዎችን መግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 01/2019

የይ/ዓለም ሆስፒታል ህክምና ኮሌጅ ተኝተውና ተመላልሰው ለሚታከሙ ህሙማን የሚውሉ

  • መድኃኒቶች፣ የህክምና መገልገያዎችንና የላቦራቶሪ ሪኤጀንቶች፣
  • አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎች፣ አላቂ የፅዳት ዕቃዎችን፣
  • ለሠራተኞች ደንብ ልብስ፣
  • ለተኝቶ ታካሚዎችና ለህክምና ተማሪዎች ለምግብ አገልግሎት የሚሆኑ ጥራጥሬዎች፣ አትክልት፣ ዳቦ፣ እንጀራ ፣
  • የህንፃ ጥገና ቁሳቁሶች፣ ቢሮ መገልገያ ዕቃዎች ፈርኒቸር/፣
  • የመኪና መለዋወጫ ዕቃዎች፣
  • የተለያዩ ህትመቶች፣
  • የመኪና መለዋወጫ ዕቃዎች እና
  • የመኪናዎች ጥገና ስራ በግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ ለማስጠገን ይፈልጋል።

1. ህጋዊና የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ፣የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና በተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡ።

2. የጨረታ ማስከበሪያ ብር 30,000.00 /ሰላሳ ሺህ ብር/ CPO ማስያዝ የሚችሉ።

3. በጨረታ ላይ ለመወዳደር የሚያስችል ማስረጃ ከገቢዎች ቢሮ የተሰጣቸውንና የታደሰ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ።

4. ተጫራቾች ህጋዊ ንግድ ፈቃዳቸውን ተ.እ.ታ. የተመዘገቡበትን ሰርትፍኬት በማቅረብ የጨረታ ዶክሜንቱን ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 ስራ ቀናት ውስጥ ይ ዓለም ሆስፒታል ህክምና ኮሌጅ ግዥ ን/አስ/ዳይሬክቶሬት ግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር 5 በመቅረብ የማይመለስ ብር 400/አራት መቶ/ በመክፈል የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ።

5. የጨረታ ሰነድ አንድ ቴክኒካል ኦርጂናል እና ሁለት ቴክኒካል ኮፒ እና አንድ ፋይናሻል ኦርጂናል ሁለት ፋይናሻል ኮፒ ሰነድ እያንዳንዱን ፖስታዎች የድርጅቱን ማህተም ተደርጎና በሰም በማሸግ በአንድ ፖስታ በማድረግ ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።

6. የጨረታ ሰነድ በተጫራች መመሪያ መሠረት ተሞልቶ እና ቁልቁል ተደምሮ ህጋዊ የሆነ የድርጅቱን ማህተም በማሳረፍ በ16ኛ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ጀምሮ እስከ 6፡00 ሰዓት ድረስ ይ/ዓለም ሆስፒታል ህክምና ኮሌጅ ግዥ ን/አስ/ዳይሬክቶሬት ግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር 5 ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

7. ጨረታው በ16ኛው ቀን ከቀኑ 6፡00 /ስድስት ሰዓት ላይ ተዘግቶ ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በተጠቀሰው ቀንና ቦታ ከቀኑ 8፡00 /ስምንት ሰዓት/ ላይ በግልፅ ይከፈታል።

8. የወቅቱ የገበያ ዋጋ ያላገናዘበ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም ከቀረበው የዋጋ ትን መያዝ አለበት።

9. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ማሳሰቢያ፡-

  • ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል።
  • ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር 09 09 49 54 15 እና 09 11 70 83 66 ይደውሉ

በሲ/ብ/ክ/መ/ጤና ቢሮ የይ/ዓለም

ሆስፒታል ህክምና ኮሌጅ


Tender details

  • Deadline: 2026-08-22
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከቀኑ 6፡00 /ስድስት ሰዓት/
  • Bid opening: 2026-08-22 14:00
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 /ስምንት ሰዓት/
  • Region: Sidama
  • Publishing entity: Yirgalem Hospital Medical College
  • Bid bond: 30,000.00 ብር
  • Bid document price: 400.00 /አራት መቶ ብር/
  • Published on: Addis Zemen (Aug 05, 2026)
  • Posted at: 2026-08-05T08:54:40.000Z
← Back to all tenders