Pharmaceuticals and medicines

በልደታ ክ/ከተማ ጤና ጽ/ቤት የአብነት ጤና ጣቢያ በ2019 በጀት ዓመት የህክምና መድሀኒት እና የላብራቶሪ ሪኤጀንት ብቃት ያላቸውንና በመስኩ የተሰማሩ ተጫራቾች አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል

Description

ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

የግዥ መለያ ቁጥር፡ 01/2019

በልደታ ክ/ከተማ ጤና ጽ/ቤት የአብነት ጤና ጣቢያ በ2019 በጀት ዓመት ከዚህ በታች በተገለፁት መሠረት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ስለሚፈልግ፡-

  • ሎት 01 የህክምና መድሀኒት እና የላብራቶሪ ሪኤጀንት ብቃት ያላቸውንና በመስኩ የተሰማሩ ተጫራቾች አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል።

በዚህም መሰረት፡-

1. በጨረታው ለመወዳደር ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ በመንግስት ግ/ን/አስ/ኤጀንሲ ድረ ገጽ ላይ በአቅራቢዎች ምዝገባ ዝርዝር የተመዘገቡ፣ የቲን/TIN/ ተመዝጋቢ የሆኑና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።

2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 30,000 (ሰላሳ ሺህ) ብር በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ/CPO/ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።

3. አሸናፊ ተጫራቾች ውሉን ሲፈርሙ የውል ማስከበሪያ ከአሸነፉት ጠቅላላ ዋጋ 10% ማስያዝ አለባቸው::

4. ተጫራቾች ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት እለት አንስቶ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ) ብር በመክፈል በአብነት ጤና ጣቢያ 1ኛፎቅ የግዥ ክፍል በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።

5. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስታወቂያው ከወጣበት እለት ጀምሮ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት በአብነት ጤና ጣቢያ 1ኛፎቅ የግዥ ከፍል ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።

6. ጨረታው በአስረኛው ቀን በ11፡30 ሰዓት ታሸጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአስራ አንደኛው ቀን 3፡00 ሰዓት በአብነት ጤና ጣቢያ አዳራሽ ይከፈታል። የመክፈቻ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ ይከፈታል።

7. ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን የህክምና መድሀኒት/ሪኤጀንት ጠቅላላ ዋጋ ማስቀመጥ ይጠበቅባቸዋል።

8. የዘገየ ጨረታና በጨረታ መክፈቻ ላይ ያልተነበበ ጨረታ ተቀባይነት የለውም።

9. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ጤና ጣቢያው ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

10. መ/ቤቱ ለጨረታ ካቀረባቸው እቃዎች ውስጥ እስከ 20% ድረስ ጨምሮ ወይም ቀንሶ የመግዛት መብቱ የተጠበቀ ነው።

11. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ ማብራሪያ እና ጥያቄ

  • በስልክ ቁጥር፡- 011-273-43-49 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
  • አድራሻ፡- ልደታ ክ/ከተማ አብነት ጤና ጣቢያ ከአብነት አደባባይ ፊት ለፊት ግቤ ህንፃ ጎን 100 ሜትር ገባ ብሎ

በልደታ ክ/ከተማ ጤና ጽ/ቤት የአብነት ጤና ጣቢያ


Tender details

  • Deadline: 2026-08-19
  • Bid closing time: 17:30
  • Bid closing (note): ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት እለት አንስቶ በአስረኛው ቀን በ11፡30 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-08-20 12:00
  • Bid opening (note): ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት እለት አንስቶ በአስራ አንደኛው ቀን 3፡00 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Lideta Sub City Health Bureau Abent Health Post
  • Buyer address: አብነት አደባባይ ጊቤ ሕንፃ አጠገብ 100 ሜትር ገባ ብሎ
  • Bid bond: 30,000.00 ብር
  • Bid document price: 300.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Aug 08, 2026)
  • Posted at: 2026-08-08T08:14:05.000Z
← Back to all tenders