Addis Ababa

በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ወረዳ 11 ፋይናንስ ፅ/ቤት የተለያዩ ዕቃዎችንና አገልግሎቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ዙር የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 001

በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ወረዳ 11 ፋይናንስ ፅ/ቤት ከዚህ በታች በሎት የተደራጁ እቃዎችንና አገልግሎቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ሎት 1

የጽህፈት መሳሪያ እቃዎች እና ሌሎች

ሎት 2

ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች

ሎት 3

የደንብ ልብሶች የጽዳት እቃዎች ስፖርት መገልገያ እቃዎች የመኪና ጎማዎችና የዲኮር እቃዎች

ሎት 4

መድሀኒቶች የእንስሳ ህክምና መሳሪያዎችና የተለያዩ ዘሮች ዶሮዎች የዶሮ ኬጂ

ሎት 5

የትራንስፖርት እና የጭነት አገልግሎት

ሎት 6

የመስተንግዶ አገልግሎት

ሎት 7

ህትመትና የህትመት ውጤቶች

ሎት 8

የጉልበት አገልግሎት ዲኮር መኪና እጥበት

ሎት 9

ቋሚና እቃዎች

ሎት 10

የኤሌክትሮኒክስና ፈርኒቸር ጥገናዎች አገልግሎት

በመሆኑም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 400 (አራት መቶ ብር) በመክፈል በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 አስተዳደር ፋይናንስ ፅ/ቤት ካራ ቆሬ ወታደር ሰፈር የሚገኘው ህንፃ ቀርበው መውሰድ እንደሚችሉ እናሳውቃለን።

ተጫራቾች ማሟላት የሚኖርባቸው፡-

  • የዘመኑን የታደሰ የንግድ ፈቃድና የንግድ ምዝገባ ሰርተፊኬት ማቅረብ አለባቸው።
  • የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን ናምበር/ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  • ተጫራቾች የጨረታ ማስረከብያ (ለሎት1፣ 2፣ 3፣ 4 ላሉት ብር 20000/ሀያ ሺህ) (ለሎት 5፣ 6፣ 7፣ 8 እና 10 ላሉት ብር 10000/አስር ሺህ) እንዲሁም (ለሎት 9 20000 /ሃያ ሺህ) በባንክ በተረጋጠ በሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው።
  • ተጫራቾች በጥቃቅንና አነስተኛ ከተደራጁ ሲፒዮ ማስያዝ አይጠበቅባቸዉም በምትኩ በኃላፊ የተፈረመ የዋስትና ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸዉ።
  • የሚቀርበው የዋጋ ሰነድ ለቫት ተጠቃሚዎች ቫትን ያካተተ መሆን አለበት።
  • ማንኛውም ተጫራች የታሸገ ፖስታ ላይ የድርጅቱ ማህተም ስልክ እና ፊርማ መኖር አለበት።
  • ማንኛውም ተጫራች የሚያቀርበው ሰነድ ኮፒ እና ዋናውን በተለያየ ፖስታ በየሎቱ ለይቶ ማቅረብ ይኖርበታል።
  • ለሎት 5፣ 6 እና 8 ብቻ ማሟላት የሚገባውን ሰነድ ተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ ከሆኑ የሚበረታታ ሲሆን ይህን ማቅረብ ካልተቻለ በምትኩ በቁርጥ ዋጋ የሚጫረቱ ይሆናል።
  • አሸናፊ ተጫራች በሰነድ ዉስጥ በተመለከተዉ የጊዜ ገደብ ዉስጥ ቀርቦ ዉል መዋዋል አለባቸዉ..
  • የእቃ ማስረከቢያ ቦታ ኮልፌ ቀራኒዮ ወረዳ 11 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ይሆናል።
  • ተጫራቾች ለሚያቀርቡት ለተወዳደሩበት እቃ ናሙና ማቅረብ አለባቸው። ናሙና ያላቀረበ ድርጅት ከውድድር ውጪ ይሆናል። እቃው በናሙናው ላይ ያለውን የጥራት ደረጃ ይዞ ካልተገኘ ተመላሽ ይደረጋል።
  • ለቋሚ እቃዎች ሳምፕል ሙሉ ዝርዝር የሚገልፅ በፎቶ ማቅረብ ይችላሉ።
  • ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ከላይ የተጠቀሱትን መረጃዎች በማቅረብ ለጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ መውሰድ ይችላሉ።
  • ተጫራቾች ተወዳድረው ያሸነፉባቸውን እቃዎች በወቅቱ ማቅረብ ካልቻሉ ያስያዙት ሲፒኦ ይወረሳል።
  • ተጫራቾች በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ከሆነ በግዥ መመሪያ መሰረት በህግ አግባብ የሚጠየቁ ይሆናል ።
  • አሸናፊ ድርጅት ያሸነፉበትን እቃ 10% በባንክ በተረጋጠ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  • አሸናፊ ድርጅት ውል ከገባበት ቀን ጀምሮ በ10 (አስር ) ቀን ውስጥ እቃውን ማቅረብ ይኖርበታል።
  • አንድ ተጫራች በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይችልም።
  • የጨረታው ሳጥን አስር (10) ተከታታይ የስራ ቀናት አየር ላይ ውሎ በአስራ አንደኛው ቀን (11) በ 13/12/2018 ዓ.ም በ4፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 አስተዳደር የስብሰባ አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል።
  • ተጫራቾች ተወዳድረው ያሸነፉባቸውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት እና ጉልበት ጫኝና አውራጅ በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 ግምጃ ቤት ት ማቅረብ አለባቸው።
  • ተጫራቾች (በጨረታው) የተሸነፉ ድርጅቶች የጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ሲፒኦ ተመላሽ ይሆናል። በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 ጽ/ቤት ሌላ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ መስሪያ ቤቱ የሚገኝበት ልዩ ቦታ ካራቆሬ ወታደር ሰፈር ወረዳ 11 ፋይናንስ ጽ/ቤት መሆኑን እንገልጻለን።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 011 369 5372 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ።

በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ወረዳ 11 ፋይናንስ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-19
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-08-19 10:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Kolefe Keranio Sub City Woreda 11 FEDB
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 400.00 ብር ለእያንዳንዱ ሎት
  • Published on: Addis Zemen (Aug 05, 2026)
  • Posted at: 2026-08-05T10:12:08.000Z
← Back to all tenders