Poultry, beekeeping and animal feed
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ቢሮ የተለያዩ አይነት የንብ እርባታ እና የዶሮ እርባታ ቁሳቁሶችን በግልጽ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Description
ድጋሚ የወጣ የንብ እና ዶሮ እርባታ ቁሳቁሶች ግዥ ጨረታ
ማስታወቂያ 15/2019
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ቢሮ በምግብ ሥርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም በጀት ድጋፍ የተለያዩ አይነት የንብ እርባታ እና የዶሮ እርባታ ቁሳቁሶችን በግልጽ ጨረታ ከዚህ በታች በሰንጠረዥ በተዘረዘረው መሰረት በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ |
ሎት |
የዕታው አይነት |
መለኪያ |
ብዛት |
የጨረታ ማስከበሪያ |
ጨረታው የሚዘጋበትና የሚከፈትበት ሰዓት |
ሰነዱ የሚገኝበት ቦታ |
|
1 |
ሎት 1 |
የተለያዩ አይነት የንብ እርባታ ቁሳቁሶች |
በጥቅል
|
1 |
50,000 |
በ31ኛው ቀን በ4፡00 ታሽጎ በዕለቱ 4፡10 ይከፈታል |
ደ/ኢ/ግ/ቢሮ ዲላ መምህራን ኮሌጅ ግቢ |
|
2 |
ሎት 2 |
የተለያዩ አይነት የዶሮ እርባታ ቁሳቁሶች |
በጥቅል |
1 |
50,000 |
በንግድ ስራ ዘርፉ የታደሰ ፍቃድ የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያለው በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ ስለመመዝገባቸውና የቫት ተመዝጋቢነት ማስረጃዎች ያላቸውና የሚያቀርቡ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ለ60 ቀናት የፀና መሆን ይኖርበታል።
- በተጫራቾች የሚቀርቡት የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒ ኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ያስያዙበትን ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች በቢሮ የተዘጋጀውን መደበኛ የጨረታ ሰነድ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ ቀናት እስከ 30ኛ ቀን 11፡30 ድረስ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል በዲላ ከተማ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ግብርና ቢሮ መምህራን ኮሌጅ ግቢ ወስጥ ከሚገኘውየግብርና ቢሮ ግዥ ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ክፍል መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነድ በመሙላት ቴክኒካል ሰነድ አንድ ኦርጂናል እና እንድ ኮፒ እንዲሁም ፋይናንሽያል ሰነድ አንድ ኦርጂናል እና አንድ ኮፒ አዘጋጅቶ በማሸግና ሁሉንም በአንድ እናት ፖስታ ከቶ በማሸግ በ31ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት በቢሮው ግዥ ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ለዚሁ ጨረታ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ። እንዲሁም የጨረታው ሳጥን በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ 4፡10 ተጫራቾች (ተወካዮቻቸው) በተገኙበት በቢሮው የግዥ ንብ አስ/ዳይሬክቶሬት ክፍል ይከፈታል።
- ቢሮው በቀረበው ጨረታ ላይ ካሸናፊው ድርጅት ጋር ውል ከመፈራረሙ በፊት የግዥውን 20% ፐርሰንት መቀነስ ወይም መጨመር ይችላል።
- የጨረታው መክፈቻ ቀን ማለትም 31ኛው ቀን የመንግስት የስራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በቀጣይ ባለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓትና ቦታ የሚከፈት ይሆናል።
- ከአንድ በላይ የሆኑ ተወዳዳሪዎች ያቀረቡት ዋጋ እኩል በሚሆንበት ወቅት በእጣ የሚለይ ይሆናል።
- ቢሮው ለዚሁ ጨረታ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰርዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ፡- 046-131-0134 / 09 16 17 65 73 ይጠቀሙ።
የደቡብ ኢትዮጵያ መንግስት ግብርና ቢሮ
Tender details
- Deadline: 2026-09-05
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ31ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-09-05 10:10
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ31ኛው ቀን 4፡10 ሰዓት
- Region: South Ethiopia Regional State
- Publishing entity: South Ethiopia's Regional State Agriculture Bureau
- Bid bond: 50,000.00 ብር ለእያንዳንዱ
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Aug 06, 2026)
- Posted at: 2026-08-06T07:57:26.000Z