Poultry, beekeeping and animal feed
የቦንጋ ዶሮ ዕርባታ ማዕከል በመራባት ላይ ላሉ ዶሮ መኖነት የሚውል የጥሬ ግብዓት ጥራቱን የጠበቀ ምርት በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Description
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የቦንጋ ዶሮ ዕርባታ ማዕከል በመራባት ላይ ላሉ ዶሮ መኖነት የሚውል የጥሬ ግብዓት ጥራቱን የጠበቀ ምርት ማለትም፡-
1ኛ ፉርሽካ
2ኛ አኩሪ አተር ፋጉሎ
3ኛ የኑግ ፋጉሎ
4ኛ ልዮር ቫይታሚን ፕሪሚክስ 0.25% ወይም 0.5%
5ኛ እስታርተር ቫይታሚን ፕሪሚክስ 0.25% ወይም 0.5%
6ኛ ሚትዮኒን
7ኛ ላዮሲን
8ኛ የተፈጨ ሥጋና አጥንት
9ኛ አንደኛ ደረጃ በቆሎ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
ስለዚህ በዘርፉ የተሰማራችሁ ነጋዴዎች
1ኛ. ሕጋዊ ንግድ ፍቃድ ያለው እና ማዕከሉ በምፈልገው መጠን እና ጥራት ማቅረብ የሚችል
2ኛ. ተጫራቾች አግባብነት ያለው የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፣ የጨረታ እሴት ታክሰ ምዝገባ ሠርተፍኬት ያላቸው፣ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው እና ካሁን ቀደም በተመሳሳይ ሥራ የተሻለ አፈፃፅም ያለው፤ ከላይ የተጠቀሱትን ማስረጃ ፎቶ ኮፒ እና ኦሪጂናል በማቅረብ አመሳክሮ ሰነዱን መግዛት ይችላል፡፡
3ኛ. ተጫራቾች የተሟላ ሠነድ ለየብቻ 1/አንድ/ኢሪጂናል 2/ሁለት/ፎቶ ኮፒ ይዘው መቅረብ አለባቸው፡፡
4ኛ. ተጫራቾች በኦሪጂናል 150,000/ አንድ መቶ ሃምሳ ሺ ብር /C P O/ የተያዘበት ሠነድ ገብቶ መታሽግ አለበት፡፡
5ኛ. ተጫራቾች የጨረታ ሠነዳቸውን በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ ማስገባት አለባቸው።
6ኛ. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር ሠነድ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግሥት ቦንጋ ዶሮ ዕርባታ በኩል የማይመለሰ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር /በመክፍል ከቦንጋ ዶሮ ዕርባታ ማዕከል መግዛት ይችላሉ፡፡
7ኛ. የጨረታው አሸናፊ የጨረታው ውጤት ሲታወቅ የውል ማስከበሪያ ከጠቅላላ የጨረታ ዋጋ 10% ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
8ኛ. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን በ11፡30 ሰዓት ላይ ታሽጎ በ16ኛው ቀን 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቦንጋ ዶሮ ዕርባታ ማዕከል በኩል ይከፈታል፡፡
9ኛ. የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቅዳሜ እና እሁድ ወይም በዓላት ቀን ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተገለፀው ቦታና ሰዓት የመዝጊያና መክፈቻ ቀን ይሆናል፡፡
10ኛ. የተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው አለመገኝት የጨረታውን ሂደት አያስተጓጉልም።
11ኛ. ተጫራቾች በሚያቀርቡት ማንኛውም ኦሪጂናል መረጃ ፊረማና ማህተም ሊኖረው ይገባል፡፡
12ኛ. የጨረታው አሽናፊ በ7 ቀናት ውስጥ ውል ገብቶ ሥራውን መጀመር ይኖርበታል፡፡
13ኛ ማዕከሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ፡-0934 449 883 / 0910 409 901 ላይ ደውለው ይጠይቁ፡፡
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ የቦንጋ ዶሮ ዕርባታ ማዕከል
Tender details
- Deadline: 2026-08-22
- Bid closing time: 17:30
- Bid closing (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን በ11፡30 ሰዓት
- Bid opening: 2026-08-24 12:00
- Bid opening (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን 4፡30 ሰዓት
- Region: South West Ethiopia Region
- Publishing entity: Bonga Poultry Center
- Bid bond: 150,000.00 ብር
- Bid document price: 500.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Aug 08, 2026)
- Posted at: 2026-08-08T08:07:02.000Z