Addis Ababa
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ደቡብ ምዕራብ አዲስ አበባ ዲስትሪክት የእርሻ መሳሪያ ባለበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ደቡብ ምዕራብ አዲስ አበባ ዲስትሪክት በሊዝ ፋይናንሲንግ ሥርዓት መሰረት ገዝቶለት የነበረውን እና ከታች የተዘረዘረው የእርሻ መሳሪያ ግዴታቸውን በመወጣት ባለመቻላቸው ከአቶ አዱኛ ተስፋ መልሶ በመረከብ ባለበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
|
ተ.ቁ |
የተከራይ ስም |
በጨረታ የሚሸጠው/ የሚከራየው ንብረት የሚገኝበት ቦታ |
የንብረቱ ዝርዝርና አይነት |
የጨረታው መነሻ ዋጋ /በብር/ |
የጨረታው አይነትና ደረጃ |
ጨረታው የሚካሄድበት ቀን ሰዓትና ቦታ |
|
1 |
አዱኛ ተስፋ |
ሸገር ከተማ አስተዳደር፣ገላን ክ/ከተማ፣ አትላስሪዞርት ወረድ ብሎ፣የኢትዮጵያ ልማት ባንክ መጋዘን ግቢ ውስጥ፡፡ |
1. Tractor: (Brand: CASE IH-FARMALL110JX; Model: TTF 8045.25D.313T; Engine Type: e37; Origin: Turkey: year 2023; Condition: Good), Needs Repair & Maintenance, ……ብዛት 1 2. Disc Plough (Brand: OTOMA; Model: O/ QD70/E; 4 Discs) ..ብዛት 1 |
5,193,750.00 |
የመጀመሪያ ድርድር ጨረታ
|
ነሐሴ 28 ቀን 2018 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00-6፡00 ቦታ፡- በኢትዮጵያ ልማት ባንክ ደቡብ ምዕራብ አዲስ አበባ ዲስትሪክት ሜክሲኮ አልሳም ጨለለቅ ህንጻ 2ኛ ፎቅ በሚገኘው ቢሮ፤ |
1. ከላይ የተገለፀውን ንብረት መግዛት ወይም መከራየት የሚፈልግ አካል (ግለሰብ፣ ተቋም ወይም አነስተኛና መካከለኛ ማሀበራት) የጨረታውን መነሻ ዋጋ 1/4ኛ (25 በመቶ) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ(CPO) በኢትዮጵያ ልማት ባንክ ስም በማዘገጀት፤በዲስትሪክቱ በተዘጋጀው ሰነድ መሰረት የሚገዙበትን ዋጋ እና የግዢ ሁኔታ በመግለፅ በፖስታ በማሸግ ለዚሁ አላማ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ እስከ ነሐሴ 27 ቀን 2018 ዓ.ም ገቢ መደረግ ያለበት ሲሆን ከላይ በተጠቀሰው ቦታ እና ሰዓት ውድድሩ ይከፈታል።
2. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሀጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ይከፈታል፤
3. ንብረቱን ሙሉ በሙሉ በጥሬ ገንዘብ ለመግዛት ተወዳድሮ ያሸነፈ ተጫራች፡-
3.1. ቀሪውን ገንዘብ ተ.እ.ታን ጨምሮ በ5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ መክፈል ይኖርበታል፡፡ የጨረታ አሸናፊው በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ቀሪውን ገንዘብ አጠቃሎ መክፈል ይኖርበታል፡፡የጨረታ አሸናፊው በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ቀሪውን ገንዘብ አጠቃሎ ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ያስያዘው ገንዘብ በሙሉ ለባንኩ ገቢ ይደረጋል፤
3.2. ንብረቱን ከመረከቡ በፊት በዘርፉ ከቀረጥ ነጻ የመጠቀም መብት ማቅረብ ወይም መንግስት ከንብረቶቹ የሚፈለገውን የጉምሩክ ቀረጥ እና ታክስ መክፈል ግዴታ አለበት፤
4. ንብረቱን በባንኩ ማሽነሪ ዱቤ ግዢ እና ኪራይ መሰረት የመከራየት ዕቅድ ያለው ተጫራች፡-
4.1. የባንኩን የማሽነሪ ኪራይ መስፈርት ስለማሟላቱ በቅድሚያ ማረጋገጥ ይኖርበታል፤ እንዲሁም በባንኩ በፖሊሲ እና መመሪያ መሰረት የሚያከናውነው የፕሮጀክት ጥናት የሚቀመጡ ቅድመ ሁኔታዎችን የማሟላት ግዴታ አለበት፤
4.2. በባንኩ አሰራር መሰረት የሚጠበቅበትን ቅድሚያ ክፍያ በ5 ተከታታይ ቀናት ዉስጥ በመክፈል የባንኩን የማሽነሪ ዱቤ ግዢ እና ኪራይ መስፈርት በማሟላት ውል መፈጸም ይኖርበታል። በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ግዴታውን ካልተወጣ የጨረታ አሸናፊነቱ ተሰርዞ ያስያዘው ገንዘብ በሙሉ ለባንኩ ገቢ ይሆናል፤
5. በጨረታው ለተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ገንዘብ (CPO) በባንኩ ማህተም ተረጋግጦ ይመለስላቸዋል፤
6. ስለ እያንዳንዱ ንብረት ዝርዝርና ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ሜክሲኮ አልሳም ጨለለቅ ህንጻ 2ኛ ወለል ላይ በሚገኘው የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ደቡብ ምዕራብ አዲስ አበባ ዲስትሪክት ማነጋገር ወይም በስልክ ቁጥር +251-11-558-6175 /0911-74-35 02 በስራ ሰዓት ደውሎ ማነጋገር ይቻላል፤
7. ንብረቶቹን ለመጎብኘት የሚፈልግ ከደቡብ ምዕራብ አዲስ አበባ ዲስትሪክት ጋር በመነጋገር አስቀድሞ ቀጠሮ በመያዝ መመልከት ይችላሉ፤
8. የጨረታው አሸናፊ ከታወቀበት ጊዜ ጀምሮ የካፒታል ዕቃውን ለማስተዳደር ማለትም የመጠለያ ኪራይ፣ የጥበቃ ክፍያ እንዲሁም ተያያዥ ወጪዎችን የመሸፈን ግዴታ አለበት፤
9. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ደቡብ ምዕራብ አዲስ አበባ ዲስትሪክት
Tender details
- Deadline: 2026-09-03
- Bid closing time: 12:00
- Bid opening: 2026-09-03 12:00
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: ኢትዮጵያ ልማት ባንክ ደቡብ ምዕራብ አዲስ አበባ ዲስትሪክት
- Bid bond: 25%
- Published on: Addis Zemen (Aug 06, 2026)
- Posted at: 2026-08-06T08:07:03.000Z