Telecommunication equipment and services

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የGPS-Fleet Management System supply and installation and other related items (ጂፒኤስ ፍሊት ማኔጅመንት ሲስተም አቅርቦትና ገጠማ እና ሌሎች ተያያዥ ዕቃዎች አቅርቦት) ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ፣ ፍቃድ ካላቸው ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥውን መፈፀም ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ ጨረታ

ቁጥር EEP/NP/NCB/01/2019

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የGPS-Fleet Management System supply and installation and other related items (ጂፒኤስ ፍሊት ማኔጅመንት ሲስተም አቅርቦትና ገጠማ እና ሌሎች ተያያዥ ዕቃዎች አቅርቦት) ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ፣ ፍቃድ ካላቸው ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥውን መፈፀም ይፈልጋል።

ስለሆነም ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር ይችላሉ።

1. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩና አግባብነት ያለው የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፍኬት(TIN) ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ በግዥ ኤጀንሲ የአቅራቢዎች ዝርዝር ድረ-ገፅ (e-GP) ላይ የተመዘገቡ፣የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ መሆን አለባቸው።

2. በዚህ ጨረታ ለመሳተፍ ከላይ የተዘረዘሩትን ማስረጃዎች በማያያዝ መወዳደር የሚችሉ ሲሆን ዝርዝር ሁኔታው በጨረታ ሰነዱ ውስጥ ይገኛል።

3. ተጫራቾች ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ቀንና ሰዓት ኮተቤ ብረታ ብረት ፊት ለፊት በሚገኘው ዋናው መ/ቤት ህንፃ ቁጥር-11 1ኛ ፎቅ በሚገኘው ገንዘብ ተቀባይ ቢሮ የማይመለስ ብር 1,000.00 (አንድ ሺህ ብር) የጨረታ ሰነዱን በሚገዛው ድርጅት ስም ወደ EEP transmission Construction A/C No.00002526655203 Commercial Bank of Ethiopian (CBE) ትራንስፈር በማድረግ በመክፈል እና የጨረታ ሰነዱን ህንፃ ቁጥር ብሎክ-9 1ኛ ፎቅ ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 201 በመምጣት መውሰድ ይችላሉ።

4. ተጫራቾች የGPS-Fleet Management System supply and installation and other related items (ጂፒኤስ ፍሊት ማኔጅመንት ሲስተም አቅርቦትና ገጠማ እና ሌሎች ተያያዥ ዕቃዎች አቅርቦት) ግዥ የቴክኒካል እና ፋይናንሻል ሰነዳቸውን ለየብቻው በሰም በታሸገ ሁለት ኤንቨሎፕ የጨረታ ቁጥር EP/NP/NCB/01/2019 የቴክኒካል እና ፋይናንሻል ሰነድ የሚል ምልክት በማድረግ ከታች በተቀመጠው ሰንጠረዥ መሠረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

NO

የግዥው አይነት/ Description

የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ

የጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት

የጨረታው መክፈቻ ቀንና ሰዓት

1

PGPS-Fleet Management System supply and installation and other related items (ጂፒኤስ) ፍሊት ማኔጅመንት ሲስተም አቅርቦትና ገጠማ እና ሌሎች  ተያያዥ ዕቃዎች አቅርቦት)

500,000.00 (አምስት መቶ ሺህ ብር)

 

ነሐሴ 22 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት

 

ነሐሴ 22 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት

 

5. ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 011-558-06-27 መደወል ይችላሉ።

6. ገዥው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ  ኃይል


Tender details

  • Deadline: 2026-08-28
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid opening: 2026-08-28 14:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Ethiopian Electric Power
  • Bid bond: 500,000.00 (አምስት መቶ ሺህ ብር)
  • Bid document price: 1000.00 /አንድ ሺህ ብር/
  • Published on: Addis Zemen (Aug 07, 2026)
  • Posted at: 2026-08-07T07:51:29.000Z
← Back to all tenders