Fresh produce, meat and dairy
በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ዱራሜ ካምፓስ ለአንድ ዓመት የሚቆይ የተለያዩ ግዥ በሀገር አቀፍ ጨረታ ህጋዊ ከሆኑ ነጋዴዎች ግዥ መፈጸም ይፈልጋል
Description
ሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ዋ/ዩ/ዱ/ካ/012345/2019
በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ዱራሜ ካምፓስ ለአንድ ዓመት የሚቆይ ሎት-1፡-የምግብ ጥሬ ዕቃ ግዥ (ጥቅል ጎመን፣ቀይ ሽንኩርት፣ ሩዝ፣ አተር ክክ፣ምስር ከከ፣የተፈጨ በርበሬ፣ የበሬ ሥጋ፣ነጭ ሽንኩርት፣ ድንች፣ ዕርድ፣ የሻይ ቅጠል እና ጨው) ሎት-2፡ የተማሪዎች ቁርስ ዳቦ ግዥ ሎት-3፡-የማገዶ እንጨት ግዥ ሎት-4፡-የጤፍ ግዥ እና ሎት-5፡ - የትራንስፖርት አገ/ት የሚሰጥ 63 ሰው የመጫን አቅም ያለው 2012 ሞዴል ደረጃ የሆነ 02 አውቶብስ መኪና፣ ለስራ ክፍል ኃላፊዎች የትራንስፖርት አገ/ት የሚሰጥ 15 ሰው የመጫን አቅም ያለው 2014 ሞዴል ደረጃ-1 የሆነ 01 ሀይሩፍ መኪና እና ለካምፓሱ የጭነት አገት የሚሰጥ አይሱዙ የጭነት መኪና ሞዴሉ 2012 እና ከዛ በላይ የሆነ 01 መኪና ኪራይ ግዥ በሀገር አቀፍ ጨረታ ህጋዊ ከሆኑ ነጋዴዎች ግዥ መፈጸም ይፈልጋል።
በመሆኑም በጨረታው መወዳደር የምትፈልጉ ተጫረቾች፡-
ከሎት-1 እስከ 4 የሚወዳደሩ ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች፡-
- በዘርፉ አግባብነት ያለው እና በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፊቃድ ያለው(ያላት)
- የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር /TN No/ ያለው(ያላት)
- በአቅረቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችል/ትችል፤
- የቫት ተመዝጋቢነት ማስረጃ ማቅረብ የሚችል/ትችል፤
- ከዚህ በፊት በዘርፉ ያገለገሉበት የመልካም ስራ አፈጻጸም ምስክር ወረቀት ያለው/ያላት/
- ለዳቦ የሚወዳደር አቅራቢ በማሽን የተጋገረ ዳቦ የሚያቀርብ የዳቦ መጋገሪያ ትልቅ ማሽን አና መብራት ቢጠፋ እንኳን አገ/ት እንዳይቋረጥ ማሽኑን የሚያንቀሳቅስ ጄኔሬቴር ያለው መሆን አለበት።
ሎት-5 የሚወዳደሩ ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች፡-
- በዘርፉ አግበብነት ያለው ህጋዊ የታደሰ ንግድ ስራ ፈቃድ ያለው(ያላት)
- የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር /TIN No/ያለው(ያላት)
- የቫት ተመዝጋቢ የሆነ/የሆነች
- በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችል/ትችል፤
- የመኪናው ባለቤትነት ሊብሬ ወይም ህጋዊ ውክልና ማቅረብ የሚችል(ትችል)
- የተሽከርካሪው ወቅታዊ ብቃት ማረጋገጫ ማስረጃ ያለው(ላት)
- ለተሽከርካሪው የሦስተኛ ወገንና ሙሉ ኢንሹራንስ ያለው (ላት)
- የተሽከርካሪው ወቅታዊ የቴከኒክ ምርመራ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል(ትችል)
- መኪናው ደረጃ-1 የሆነ
- ከላይ የተዘረዘሩ መስፈርቶችን የምታሟሉ ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ጨረታ በሀገር አቀፍ አዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከታወጀበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ከዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ዱራሜ ካምፓስ ከግዥ ቡድን መሪ ቢሮ በአካል በመቅረብ የማይመለስ 200 /ሁለት መቶ/ ብር ብቻ በመክፈል መግዛት ትችላላችሁ።
- ከተሰጠው መስፈርት ወይም የቴከኒክ ፍላጎት መግለጫ ውጪ የሚሳተፉ ተጫራቾች ከውድድር ውድቅ ይደረጋሉ።
- ተጫራቾች እኩል ዋጋ ቢያቀርቡ አሸናፊው በዕጣ የሚለይ ይሆናል።
- ተጫራቾች የጨረታውን ነጣላ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ ሞልተው ማቅረብ አለባቸው።
- በጨረታ ሰነዱ ላይ በዝርዝር የተገለጹ ዕቃዎች/አገ/ት የማቅረቢያ ጊዜ በውል ስምምነት የሚገለጽ ሆኖ አሸናፊ ተጫራች ያሸነፈውን ዕቃ/አገ/ት በራሱ ትራንስፖርት እስከ ዋቸሞ ዩኒቨርሲት ዱራሜ ካምፓስ ግቢ ድረስ ያቀርባል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በሎት፡-1 በእያንዳንዱ የምግብ ጥሬ ዕቃ ዓይነት ብር 30,000.00(ሰላሳ ሺህ ብር) ብቻ፣ በሎት፡-2 30,000.00(ሰላሳ ሺህ ብር) ብቻ፣ በሎት፡-3 30,000.00(ሰላሳ ሺህ ብር) ብቻ፣ በሎት፡ -4 200,000(ሁለት መቶ ሺህ ብር) ብቻ፣ ሎት፡-5 ለአውቶብስ መኪና ለእያዳንዱ ብር 50,000(ሃምሳ ሺህ ብር) ብቻ በድምሩ ብር 100,000(አንድ መቶ ሺህ ብር)ብቻ ፣ለሀይሩፍ መኪና ብር 30,000(ሰላሳ ሺህ ብር)ብቻ እና ለአይሱዙ መኪና ብር 30,000(ሰላሳ ሺህ ብር) ብቻ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም ባንክ ጋራንቲ ሌተር/ደብዳቤ/ በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ በዱራሜ ካምፓስ ስም አዘጋጅተው ለብቻው በፖስታ በማሸግ ከኦርጅናል ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች የዕቃ/የአገልግሎት ዝርዝር ነጠላ እና ጠቅላላ ዋጋ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አባሪ ተደርጎ በተሰጠው ዕቃ/አገ/ት ግዥ ዝርዝር ገጽ ወይም በራሳችሁ ዋጋ ማቅረቢያ ላይ ቅደም-ተከተሉን ሳያዛቡ በመሙላት የድርጅታቸውን ማህተምና ፊርማ በሁሉም ገጾች ላይ በማሳረፍ 1/አንድ/ ኦርጅናል እና 2 (ሁለት) ፎቶ ኮፒ በተለያየ ፖስታ በማድረግ ጨረታው ከታወጀበት ቀን ጀምሮ እስከ 11ኛው ቀን ከቀኑ እስከ 8፡15 ድረስ ፖስታውን በማሸግ በዋቸሞ/ዩ/ዱ/ካ ግዥ ቡድን መሪ ቢሮ ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል። ጨረታው በ11ኛው ቀን ከቀኑ 8፡15 ላይ ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚያው ቀን ከቀኑ 8፡30 ይከፈታል። ይሁን እንጂ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በራሳቸው ፍላጎት አለመገኘት ጨረታውን ከመክፈት አያስተጓጉልም። ነገር ግን 11ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል። ጨረታው የታወጀበት ቀን 01/12/2018 ዓ/ም ጨረታው የሚከፈትበት ቀን 11/12/2018 ዓ/ም ይሆናል።
- የጨረታው ውጤት ጨረታው ተገምግሞ እንዳለቀ በደብዳቤ /በፋክስ/ በስልክ እና በውስጥ ማስታወቂያ የሚገለጽ ይሆናል።
- ተጫራቾች አሸናፊ ከሆኑ ላሸነፉበት ጠቅላላ ዋጋ 10% የመልካም ሥራ አፈጻጸም ዋስትና (ውል ማስከበሪያ) በቅድሚያ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
- ማንኛውም ተጫራች በውል ውስጥ የተካተቱትን ህጎች የማክበር ግዴታ አለበት።
- ተጫራቾች በሚወዳደሩበት ሎቶች ዋጋቸውን ሲሞሉ ከቫት ጋር ወይም ያለቫት ብለው መግለጽ አለባቸው። ካልሆነ ግን የተሞላው ዋጋ ቫት 15% እንዳለ ተደርጎ ይወሰዳል።
- በዋጋ ማቅረቢያው ላይ የሚጻፈው ጽሁፍ በግልጽ የሚነበብ መሆን አለበት። ድልዝ ስርዝ ቢኖር እንኳን ማስተካከያ በተደረገው ቦታ ላይ የድርጅቱ ህጋዊ ፊርማ መፈረም አለበት
- በተጨማሪ የእያንዳንዱ ዕቃ አገልግሎት ዝርዝር መረጃ በጨረታ ሰነዱ ላይ ተገልጾአል።
- ካምፓሱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ተጨማሪ መረጃ፡- ቢያስፈልግ በስልክ ቁጥር 09 16 72 60 33 ደውሎ ማግኘት ይቻላል።
በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የዱራሜ ካምፓስ
Tender details
- Deadline: 2026-08-17
- Bid closing time: 14:15
- Bid opening: 2026-08-17 14:30
- Region: Central Ethiopia
- Publishing entity: Wachemo University Durame Campus
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Aug 07, 2026)
- Posted at: 2026-08-07T08:31:55.000Z