Earthworks and site preparation
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ለግንባታ መሳሪያዎች (ብሎኬት ማምረቻ) የመትከያ ቦታ ዝግጅት እና ተያያዥ ስራዎች ዲዛይን እና ግንባታ (Site Preparation, Design & Construction of Facilities for HCB Machines at hearby Bishoftu city/Resettlement site on Turkey basis) ብቁ የሆኑ ደረጃ 1 የመንገድ/ ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ ድርጅቶችን
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር:-SSNT-T632
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በቢሾፍቱ ከተማ በሚያስገነባው አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የመልሶ ማቋቋሚያ ቦታ ላይ ለግንባታ መሳሪያዎች (ብሎኬት ማምረቻ) የመትከያ ቦታ ዝግጅት እና ተያያዥ ስራዎች ዲዛይን እና ግንባታ (Site Preparation, Design & Construction of Facilities for HCB Machines at nearby Bishoftu city/Resettlement site on Turkey basis) ብቁ የሆኑ ደረጃ 1 የመንገድ/ ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ ድርጅቶችን በጨረታ አወዳድሮ በሶስት ምድብ ለማሰራት ይፈልጋል።
ምድብ 1 ቢሾፍቱ ከተማ፤ ዱከም ክፍለ ከተማ፣ የአቡሴራ ወረዳ ምድብ 2; ቢሾፍቱ ከተማ፣ዱከም ክፍለ ከተማ፣ አዳ ነዴ ወረዳ ምድብ 3 ዲባዩ ከተማ፣ ድሬ ወረዳ አንድ ተጫራች ለአንድ፣ ለሁለት ወይም ለሦስቱም ምደቦች ጨረታ ማቅረብ ይችላል። ነገር ግን ከአንድ (1) ምድብ በላይ ለያሸንፍ አይችልም።
ስለሆነም ለስራው ብቁ የሆኑ ተጫራቾች ፣ የዘመኑን የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የታደሰ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ከተፈቀደለት አካል በምድብ GC/RC-1 ማቅረብ የሚችል፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ ከመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ (PPPAA) የአቅራቢነት የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ ፣ በመንግስት ጨረታዎች ለመሳተፍ ጊዜው ያላለፈበት ፈቃድ ያላቸው እና ከግብር እዳ ነጻ ስለመሆናቸው ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡ ፕሮጀክቱ በ9o ተከታታይ ቀናት ውስጥ መጠናቀቅ አለበት።
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት የስራ ቀናት በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የማይመለስ 200.00 ብር (ሁለት መቶ ብር) በሂሳብ ቁጥር 1000006958277(E- 99) ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጨረታ ቁጥር SSNT-T632 በሚል ገቢ በማድረግና የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ ቅጅ (Deposit Slip Copy) ከታች በተጠቀሰው የኢሜይል አድራሻ በመላክ የጨረታ ሰነዱን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂከ ሶርሲንግ ክፍል በኢሜይል ማግኘት ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 500,000.00 / አምስት መቶ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ወይም ለ150 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ምንም አይነት ቅድመ ሁኔታ የሌለው የባንክ ዋስትና ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ከማንኛውም ኢንሹራንስ የሚቀርብ ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም። አሸናፊው ከተለየ በኋላ በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ወዲያውኑ ተመላሽ ይሆናል፡፡
ተጫራቾች በጨረታው ደንብ መሠረት የመጫረቻ ሠነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል ነሓሴ 28, 2018 ዓ.ም እስከ ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቦሌ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና መሥሪያ ቤት የጨረታ መክፈቻ አዳራሽ ውስጥ በተመሳሳይ ቀን ከቀኑ በ 9:30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ
ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ
ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል
ስልክ ቁጥር 011-517- 8024
ኢ-ሜይል: [email protected]
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ ወይም የማሻሻል መብቱ የተጠበቀ ነው።
Ethiopian
የኢትዮጵያ
Tender details
- Deadline: 2026-09-03
- Bid closing time: 15:00
- Bid opening: 2026-09-03 15:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Ethiopian Airlines Group (ETG)
- Buyer TIN: 0000028498
- Bid bond: 500,000.00 ብር
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Aug 08, 2026)
- Posted at: 2026-08-08T08:15:49.000Z