Books, manuals and publications

የሀድያ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ለዞኑ ትምህርት መምሪያ የመጀመሪያ ደረጃና የ7ኛ እና የ8ኛ ክፍል የመማሪያ መጽሐፍት ህትመት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሳተም ይፈልጋል

Description

ለሶስተኛ ዙር የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

የሀድያ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ለዞኑ ትምህርት መምሪያ የመጀመሪያ ደረጃና የ7ኛ እና የ8ኛ ክፍል የመማሪያ መጽሐፍት ህትመት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሳተም ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሠረት ተጫራቾች፡-

1ኛ. በመስኩ የታደሰ ንግድ ፈቃድ

2ኛ. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር

3ኛ. የቫት ተመዝጋቢነት ሠርተፍኬት

4ኛ, የዕቃና አገልግሎት አቅራቢነት ሰርተፍኬት ያላቸው ድርጅቶች፡

በሀድያ ዞን ፋ/መምሪያ ቢሮ ቁጥር 17 በአካል በመቅረብ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ብር 100/አንድ መቶ ብር/ በመክፈል እንድትገዙና ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 100,000/አንድ መቶ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ (CPO) ማስያዝ የሚጠበቅባቸው ሲሆን የጨረታ መወዳደሪያ መምሪያው ባዘጋጀው ፎርማት ላይ ብቻ በመሙላት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት የመወዳደሪያ ፖስታዎችን ኦርጅናልና ኮፒ በማሸግ ቢሮ ቁጥር 17 ላይ በሚገኘው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እንድታስገቡና ጨረታውም በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ የጨረታ ሳጥን ታሽጎ በ4፡30 ላይ የሚከፈት ሲሆን ቀኑ የእረፍት ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ ቀን በተመሳሳይ ቦታና ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡

መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 0461784281 /0465552337 ደውሎ መጠየቅ የሚቻል መሆኑን እንገልጻለን፡፡

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት

የሀድያ ዞን ፋይናንስ መምሪያ


Tender details

  • Deadline: 2026-08-24
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-08-24 10:30
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
  • Region: Central Ethiopia
  • Publishing entity: Hadiya Zone Finance Bureau
  • Bid bond: 100,000.00 ብር
  • Bid document price: 100.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Aug 09, 2026)
  • Posted at: 2026-08-10T08:06:01.000Z
← Back to all tenders