House and Building Sale
የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ አ.ማ. የንብረቶች ሐራጅ ማስታወቂያ አውጥቷል
Description
ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የሐራጅ ማስታወቂያ
የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ አ.ማ. ከዚህ በታች ስሙ ለተገለጸው ተበዳሪ የበደረውን ገንዘብ በብድር ውሉ መሠረት ስላልከፈሉ ባንኩ በተሽሻለው አዋጅ ቁጥር 97/90 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ለብድር መክፈል ዋስትና እንዲሆን ሥልጣን ባለው አካል የተመዘገበውንና ያሳገደውን ንብረት በግልጽ ጫረታ አወዳድር በመሸጥ ገንዘቡን ወደ ተበዳሪ የብድር ዕዳ ገቢ ለማድረግ ይፈልጋል። በመሆኑም ማንኛውም ተጫረች ሐራጁ በሚካሄድበት ዕለት ለቅይጥ አገልግሎት የሚውል ለመኖሪያ እና ንግድ ቤት) መግዛት የሚፈልግ ተጫራቾች በዕለቱ በጫረታ ቦታ በመቅረብ በጫረታ ላይ እንዲወዳደሩ ተጋብዟል።
|
ተቁ
|
የተበዳሪው ስም
|
የንብረት አስያዥ ስም
|
የንብረቱ ዓይነት
|
አበዳሪ ቅርንጫፍ
|
ለጨረታ የቀረበው ንብረት አድራሻና ዝርዝር ሁኔታ |
ቦታ ስፋት በካ.ሜ
|
የጨረታ መነሻ ዋጋ
|
ጨረታው የሚካሄድበት ቀን፣ ሰዓትና ቦታ |
|||
|
ዞን |
ክ/ከተማ |
ወረዳ |
የካርታ ቁጥር |
||||||||
|
1 |
ገለታ ቦጆ ሶሪ
|
ገለታ ቦጆ ሶሪ
|
ቅይጥ አገልግሎት (ለመኖሪያ ቤትና ለንግድ አገልግሎት የሚውል)
|
አስኮ
|
ኦሮሚያ (ሸገር ከተማ)
|
ገፈርሳ
|
ቡረዩ
|
BU/Q/dur/ 3004/2001
|
864
|
41,659,129.93
|
ጫረታው ጳጉሜ 3 ቀን 2018 ዓ.ም ጠዋት ከ4፡00-6፡00 ስዓት በቂርቆስ ክ/ከ/ወረዳ 09 የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጽ/ቤት ፊት ለፊት በሚገኘው ጌት ሀውስ ሕንጻ የኦሮሚያ ሕብረት ሥራ ባንክ አማ ፊንፊኔ ቅርንጫፍ በሚገኝበት ሕንፃ 3ኛ ፎቅ የስብሰበ አደራሽ ውስጥ ይካሄዳል።
|
ተጫራቾች ለጫረታ ከመቅረባቸው በፊት የሚከተሉትን ደንቦች በመገንዘብ ማክበር ይኖርባቸዋል።
1. ተጫራቾች ጫረታው በሚካሄድበት ዕለት የጫረታውን መነሻ ዋጋ 1/4 (25%) የጫረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ በባንክ ክፍያ ማዘዣ CPO በኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ አማ ስም አስርተው ይዘው በመቅረብ በጫረታው ዕለት ቀርበው በመመዝገብ በጫረታው ለመሳተፍ ይችላሉ። ጫረታውን በድርጅት ስም የምጫረት ተጫራች በዘመኑ የታደሰ የንግድ ምዝገበ ወረቀት፣ የንግድ ፈቃድና ከድርጅቱ የተሰጠዉ ውክልና እንዲሁም ማንነቱን የሚገልጽ መታወቂያ ማቅረብ አለበት።
2. ጨረታው ከላይ ቦታ፣ቀንና ሰዓቱ በተገለፀው መሠረት ባለዕዳዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይካሄዳል። ባለዕዳዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ሳይገኙ ቢቀሩ ሐራጁ በሌሉበት ይካሄዳል።
3. ንብረቱን በሥራ ሰዓት መጎብኘት ለሚፈልጉ ተጫራቾች በቡረዩ ገፈርሳ ክ/ከተማ ቡረዩ ወረዳ የሚገኝ መኖሪያ ቤት አስኮ ቅርንጫፍ በስልክ ቁጥር 09 10-07-49-47 ወይም 09 11-54-35-22 በመደወል መኖሪያ ቤቱ (ንብረቱ) በሚገኝበት ቦታ በመገኘት ከሰኞ እስከ ዓርብ በሥራ ሰዓት መጎብኛት ይችላሉ።
4. የጫረታው አሸናፊ የአሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ15 ቀናት ውስጥ አጠቃሎ የመክፈል ግዴታ አለበት። የጫረታው አሸናፊ የሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ15 ቀናት ውስጥ ካልከፈለ ያስያዘው CPO ለባንኩ ገቢ ሆኖ ጫረታው ተሰርዞ አዲስ የሐራጅ ማስታወቂያ ወጥቶ የሚካሄድ ይሆናል። በጫረታው ለተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት CPO ወዲያውኑ ተመላሽ ይደረጋል።
5 የጨረታው አሸናፊ በሕጉ መሠረት ለመንግስት የሚከፈለውን ማንኛውንም የቫትና ታክስ ክፍያ፣ የስም ማዛወሪያ እና ሌሎች ወጪዎችን ከፍሎ ስሙ ወደ እራሱ እንዲዛወር ያደርገል\።
6. ባንኩ የተሸለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ አ.ማ
Tender details
- Deadline: 2026-09-08
- Bid closing time: 12:00
- Bid opening: 2026-09-08 12:00
- Region: Oromia
- Publishing entity: Oromia Cooperative Bank S.C.
- Bid bond: 25%
- Published on: Reporter (Aug 09, 2026)
- Posted at: 2026-08-10T13:38:10.000Z