Equipment
የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ለሠራተኞች አገልግሎት የሚውሉ የደህንነት መጠበቂያ ዕቃዎች፣ የደንብ ልብስ፣ የደህንነት እና የሥራ ጫማዎች መግዛት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
ፌቤኮ/ብግጨ/ዕግ/22/11/18
1. የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ለሠራተኞች አገልግሎት የሚውሉ የደህንነት መጠበቂያ ዕቃዎች የደንብ ልብስ እና የደህንነት እና የሥራ ጫማዎች ግዥ በጨረታ መለያ ቁጥር ፌቤኮ ብግጨ/ዕግ/22/11/18 በ 3(ሦስት) ሎት ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
2. ኮርፖሬሽኑ ለሚያከናውነው ከዚህ በታች ለተዘረዘሩት ዕቃዎች ግዥ ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውንና የዕቃውን ዋጋ በአንድ የታሸገ ኢንቨሎፕ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ተጫራቾች በሚወዳደሩባቸው ለእያንዳንዱ የእቃ አይነት ናሙና ከጨረታ መክፈቻ ቀን 3 (ሶስት) ቀን አስቀድሞ ማቅረብ አለባቸው፡፡
|
ሎት |
የዕቃ ዝርዝር |
የጨረታ ማስከበሪያ |
|
1 |
የደህንነት መጠበቂያ ዕቃዎች (ሄልሜት አንፀባራቂ፣መነፅር እና ተዛማጅ እቃዎች |
30,000.00 |
|
2 |
የደንብ ልብስ (ሙሉ ልብስ፣ ሸሚዝ ቱታ፤ጋወን እና ተዛማጅ እቃዎች) |
50,000.00 |
|
3 |
የደህንነት እና የሥራ ጫማዎች |
30,000.00 |
3. ጨረታው የሚከናወነው በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ሥነ-ሥርዓትና ይህንኑ አስመልክቶ ከኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ በመንግሥት የልማት ድርጅቶች የግዥ አፈፃጸም መመሪያ 1070/2017 መሠረት ሲሆን ተጫራቾች ከሚፈለገው አገልግሎት ጋር የተዛመደ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የግብር ከፋይ ማስረጃ የሚያቀርቡ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
4. የተሟላ የጨረታ ሰነዶችን ማንኛውም ፍላጎት ያለው ተጫራች ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ21 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ለገሀር በሚገኘው የኮርፓሬሽኑ ዋና መ/ቤት ሕንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 201 በኮርፖሬሽኑ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በአካል በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶቻቸውን በኮርፖሬሽኑ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 201 ለዚሁ አገልግሎት ታሽጎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 21ኛው ቀን ወይም ነሐሴ 26 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ እንዲያቀርቡ ሆኖ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ በባንክ በተመሰከረለት የባንክ ዋስትና ወይም ሲ.ፒ.ኦ በፌዴራል ቤቶች ኮፖሬሽን ስም ከጨረታ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡ ከጨረታው መክፈቻ ዕለትና ሰዓት ዘግይቶ የቀረበ የጨረታ ሰነድ ውድቅ ይደረጋል፤ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ነሐሴ 26 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡15 ሰዓት በኮርፖሬሽኑ 1ኛ ፎቅ በሚገኘው የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
6. ኮርፖሬሽኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ ዌብሳይትwebsite www.fhc.gov.et የፖሣ.ቁ. Po. Box 299
የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን
Tender details
- Deadline: 2026-09-01
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-09-01 10:15
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Federal Housing Corporation
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
- Published on: Addis Zemen (Aug 10, 2026)
- Posted at: 2026-08-11T08:14:03.000Z
- Buyer website: https://www.fhc.gov.et