Hotel Service Provision
የሀዋሳ ከተማ ስፖርት ክለብ በ2019 ዓ/ም ለክለቡ ስፖርተኞች በአንድ ሆቴል ውስጥ የሆነ የአልጋ ኪራይ እና የምግብ መስተንግዶ በጨረታ ማወዳደር ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የሀዋሳ ከተማ ስፖርት ክለብ በ2019 ዓ/ም ለክለቡ ስፖርተኞች በአንድ ሆቴል ውስጥ የሆነ የአልጋ ኪራይ እና የምግብ መስተንግዶ በጨረታ ማወዳደር ይፈልጋል።
በዚህ መሠረት፤-
ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ አቅራቢዎች መወዳደር ይችላሉ፡፡
1.በሥራ መስኩ ሕጋዊ የታደሠ ንግድ ፍቃድ፣የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
2.የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆነ
3.የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
4.ተጫራቾች ለተመዘገቡ ጨረታዎች የጨረታ ማስከበሪያ 50,000.00 /ሃምሳ ሺህ /ብር በባንክ የተረጋገጠ (የምስክር) ሲፒኦ (CPO) ወይም ቢድ ቦንድ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
5.የጨረታ ሰነዱን ከሀዋሳ ከተማ ስፖርት ክለብ ቢሮ በመቅረብ ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 /ለአስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናትን በመጠቀም ብር 3,000.00 /ሶስት ሺህ/ በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
6.የተወዳዳሪ ሆቴል ደረጃ በባሕልና ቱሪዝም ሰርተፍኬት የተሰጠው ከባለ 3 ኮኮብ በላይ የሆነ መሆን አለበት ማስረጃውንም አያይዞ ኮፒ ማቅረብ አለበት፡፡
7.የጨረታ ሠነዱ በሰም ለየብቻቸው በታሸገ ኤንቨሎፕ አንድ ኦርጅናልና ሁለት ኮፒ ፋይናንሻል በማያያዝ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተከታታይ ቀናትን በመጠቀም በሀዋሳ ከተማ ስፖርት ክለብ ፋይናንስ ቢሮ አርተፍሻል ሜዳ ቢሮ ቁጥር 1 ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
8. ጨረታው በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበትም ሆነ ባልተገኙበት 4፡00 ሰዓት በቢሮ ቁጥር 1 ይከፈታል፡፡ ይህ ቀን ቅዳሜ /እሁድ/ ከሆነ እንዲሁም የበዓላት ቀን ከሆነ በተመሣሣይ ሰዓት በሚቀጥለው የሥራ ቀን ጨረታው ይከፈታል፡፡
9. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ ተጠበቀ ነው።
ስልክ ቁጥር፡- 046-212-4176
የሀዋሳ ከተማ ስፖርት ክለብ
Tender details
- Deadline: 2026-08-25
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ጨረታው በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት
- Bid opening: 2026-08-25 12:00
- Bid opening (note): ጨረታው በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
- Region: Sidama
- Publishing entity: Hawassa City Sport Club
- Bid bond: 50,000.00 ብር
- Bid document price: 3,000.00 /ሶስት ሺህ/
- Published on: Addis Zemen (Aug 10, 2026)
- Posted at: 2026-08-11T08:30:59.000Z