Building Construction

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የደህንነት ስፍራ ዲዛይን እና ግንባታ (Design Build of Emergency Access Roads on Both Sides of Runways 07L/25R and 07R/25L, Including Runway 07L/25R RESA at AABIA) ለማሰራት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር: SSNT-T635

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ብቁ የሆኑ ደረጃ 1 የመንገድ /ጠቅላላ ሥራ ተቋራጮችን (Category 1 Road/ General Construction) በጨረታ አወዳድሮ በ አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ለሁለቱም መንደርደሪያ ሜዳዎች የአደጋ ጊዜ መዳረሻ መንገዶችን እና ለ 07L/25R የመንደርደሪያ ሜዳ ጫፍ የደህንነት ስፍራ ዲዛይን እና ግንባታ (Design Build of Emergency Access Roads on Both Sides of Runways 07L/25R and 07R/25L, Including Runway 07L/25R RESA at AABIA) ለማሰራት ይፈልጋል:: ስለሆነም ለስራው ብቁ የሆኑ ተጫራቾች ፣ የዘመኑን የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የታደሰ የምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ ከተፈቀደለት አካል በምድብ R/GC 1 ማቅረብ የሚችሉ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VA) ተመዝጋቢ የሆኑ ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ ከመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ (PPPAA) የአቅራቢነት የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ ፣ በመንግስት ጨረታዎች ለመሳተፍ ጊዜው ያላለፈበት ፈቃድ ያላቸው እና ከግብር እዳ ነጻ ስለመሆናቸው ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡ የፕሮጀክቱ ማጠናቀቂያ ጊዜ በ180 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ይሆናል።

ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጳጉሜ 3፣ 2018 ዓ.ም ባሉት የስራ ቀናት በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የማይመለስ ሁለት መቶ ብር (200.00 ብር) በሂሳብ ቁጥር 1000006958277(E-99) ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጨረታ ቁጥር SSNT-T635 በሚል ገቢ በማድረግና የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ ኮፒ (Deposit Slip Copy) ስካን በማድረግ ከታች በተጠቀሰው የኢሜይል አድራሻ በመላክ የጨረታ ሰነዱን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ግዢ ከፍል በኢሜይል ማግኘት ይችላሉ።

በጨረታው የሚካፈል ማንኛውም ተጫራች ለሚጫረትበት ሁለት መቶ ሺህ ብር (200,000.00ብር) የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Bond) የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) በኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስም ማስያዝ አለባቸው። ከማንኛውም ኢንሹራንስ እና ቅድመ ሁኔታ ያለው የባንክ ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም፡፡ጨረታው ከተዘጋበት ቀን ጀምሮ ለ መቶ ሃምሳ ቀናት (150) ቀናት የሚቆይ ይሆናል። አየር መንገዱ ጨረታው የሚቆይበትን ጊዜ እንዲራዘምለት ተጫራቾችን የመጠየቅ መብት አለው።

ተጫራቾች በጨረታው ደንብ መሠረት የመጫረቻ ሠነዳቸውን (ቴክኒካልና ፋይናንሻል) ዋናውን እና ኮፒውን እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያ በተለያየ ኤንቨሎፕ አሽገው ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ከፍል ጳጉሜ 3፣ 2018 ዓ.ም እስከ ጠዋቱ 5፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዲስ አበባ ቦሌ በሚገኘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና መስሪያ ቤት የጨረታ መክፈቻ አዳራሽ ውስጥ በተመሳሳይ ቀን ከጠዋቱ 5:30 ሰዓት ይከፈታል።

ለተጨማሪ ማብራሪያ:-

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ

ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ

ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል

ስልክ ቁጥር Tel: +251 115 17 4028/8025

ኢ-ሜይል: [email protected] 

አየር መንገዱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

Ethiopian

የኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ


Tender details

  • Deadline: 2026-09-08
  • Bid closing time: 11:00
  • Bid opening: 2026-09-08 11:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Ethiopian Airlines Group (ETG)
  • Buyer TIN: 0000028498
  • Bid bond: 200,000.00 ብር
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Aug 10, 2026)
  • Posted at: 2026-08-11T08:46:23.000Z
← Back to all tenders