ICT
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በ2019 በጀት ዓመት የዲጂታል ትራንስፖርት አገልግሎት (በጥሪ ማዕከል የተደገፈ) በግልጽ ጨረታ የግዥ ዘዴ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
የብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር፡-ኢፕድ 001/2019
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በ2019 በጀት ዓመት የዲጂታል ትራንስፖርት አገልግሎት (በጥሪ ማዕከል የተደገፈ) በግልጽ ጨረታ የግዥ ዘዴ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም፡-ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በውድድሩ መሳተፍ ይችላሉ፡፡
1. በሥራ ዘርፉ ሕጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢነት ምስክር ወረቀት፣ በጨረታ ለመሳተፍ የሚያገለግል ታክስ ክሊራንስና በመንግሥት ግዢ በአቅራቢነት የተመዘገቡ መሆን አለባቸው፡፡
2. ዕጩ ተወዳዳሪዎች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ግዥውን አስመልክቶ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት አቅርቦት መምሪያ ግዥ ቡድን በአካል በመምጣት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከሚወጣበት ቀን ጀምሮ ለ16 ተከታታይ ቀናት በመውሰድ የሚወዳደሩበትን ዝርዝር ዋጋ ከቫት ጋር በመሙላት የጨረታ ሰነዱን ቴክኒክና ፋይናንሽያል በ4 በታሸገ ኢንቨሎፕ ኦሪጅናሉንና ኮፒዎቻቸውን ለየብቻ በማቅረብ ጉዳዩን አስመልክቶ በተዘጋጀው በአቅርቦት መምሪያ ግዥ ቡድን በሚገኘዉ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
3. ዕጩ ተወዳዳሪዎች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚውል ብር 260,000.00 (ሁለት መቶ ስልሳ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ/ቢድቦንድ ማስያዝ አለባቸው፡፡
4. ጨረታው ዕጩ ተወዳዳሪዎች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው የሥራ ቀን የጨረታ ሳጥኑ በአቅርቦት መምሪያ ከረፋዱ 4፡00 ሠዓት ታሽጎ በዕለቱ ከረፋዱ 4፡30 ይከፈታል፡፡ ሆኖም ግን የመክፈቻ ቀኑ እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ ቀጣይ ባለው የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል
5. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ፡ኢ፡ሜይል [email protected]
አድራሻ ፡አራት ኪሎ ከብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ፊት ለፊት
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት
Tender details
- Deadline: 2026-08-27
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው የሥራ ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሠዓት
- Bid opening: 2026-08-27 12:00
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው የሥራ ቀን ከረፋዱ 4፡30 ሠዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Ethiopian Press Agency
- Buyer address: አራት ኪሎ ከብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት ፊት ለፊት
- Bid bond: 260,000.00 (ሁለት መቶ ስልሳ ሺህ ብር)
- Bid document price: 100 (አንድ መቶ ብር)
- Published on: Addis Zemen (Aug 12, 2026)
- Posted at: 2026-08-12T07:38:57.000Z