Construction Machinery and Equipment

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በምዕራብ ሐረርጌ ዞን ሚኤሶ ወረዳ የገንዘብ ጽ/ቤት 2019 ዓ.ም ለወረዳ ለተለያዩ ቤቶች የሚውሉ አላቂ እና ቋሚ የግንባታ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በምዕራብ ሐረርጌ ዞን ሚኤሶ ወረዳ የገንዘብ ጽ/ቤት 2019 ዓ.ም ለወረዳ ለተለያዩ ቤቶች የሚውሉ አላቂ እና ቋሚ የግንባታ ኢቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ የሚከተለውን መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል።

1. ማንኛውም ተጫራች ዕቃውን በጥራት ለማቅረብ የሚያስችል ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸውንና 2018 ዓ.ም ግብር የከፈሉ 2019 ያደሰ።

2.ተጫራቾች የእቃ አቅራቢያዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።

3. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ የሆኑና ለዚሁ ማስረጃ የሚያቀርቡ መሆን አለባቸው።

4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 10000 (አስር ሺህ ብር) በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንከ የተረጋገጠ (CPO) ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500 በመክፈል ከላይ በተገለጸው ጽ/ቤት አድራሻ ቢሮ ቁጥር አንድ (1) በመቅረብ ይህ ማሰታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በመንግስት መ/ቤት የስራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ።

6. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 28/12/18 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ለተጫራቾች ከፍት ይሆናል።

7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የሚጫረቱበትን መወዳደሪያ የአንዱን ዋጋ በመጥቀስ ዋና እና ኮፒውን ለየብቻ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ ውስጥ አድርገው በ28/12/18 ዓ.ም ከቀኑ 7፡30 አስከ 8፡00 ድረስ ቢሮ ቁጥር አንድ (1) ገቢ ማድረግ አለባቸው። ጨረታው በዚው ዕለት ከቀኑ 8፡00 ተዘግቶ ከቀኑ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ጨረታው ይከፈታል።

8. አሸናፊ ድርጅት ተጫራቾች ያሸነፉበትን ዕቃዎች በራሱ ትራንስፖርት አስከ ሚኤሶ ወረዳ የገንዘብ ጽ/ቤት ቅጥር ግቢ የሚገኝ መጋዘን ማቅረብ ይኖርባቸዋል።ተጫራቾች የተፈለገውን ዕቃ ብዛትና ጥራት አሟልቶ ግዴታ ማቅረብ አለባቸው።

9.ለሽያጭ የቀረበውን ዕቃ ጥራቱን ያልጠበቀ ከሆነ አሸናፊው ድርጅት በራሱ ወጪ ዕቃውን የመለወጥ ገንዘቡን የመመለስ ግዴታ አለበት።

10.የማስጫኛና የማስወረጃ ወጪ በተጫራቹ ይሸፈናል።

11. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ የተሞላው ላይ ስረዝ ድልዝ ወይም ለማንበብ አስቸጋሪ ከሆነ ተቀባይነት አይኖረውም።

12. ተጫራቾች የሚሞሉት ሰነድ ላይ የድረጅታቸውን መሐተም እና ፊርማ በያንዳዱ ገጽ ላይ መኖር አለበት።

13. ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆኖ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

14. ተወዳዳሪዎች ጨረታው ከተከፈተበት ጊዜ ጀምሮ ውሉን ከተፈራረሙ በኋላ ዋጋው የፀና ይሆናል።

አድራሻ በምዕራብ ሐረርጌ ዞን ሚኤሶ ወረዳ የገንዘብ/ጽ/ቤት

ሚኤሶ

ስልክ ቁጥር 0967758707

የምዕራብ ሐረርጌ ዞን ሚኤሶ ወረዳ የገንዘብ/ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-03
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid opening: 2026-09-03 14:30
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: Meisso Wereda FEDB
  • Bid bond: 10,000.00 (አስር ሺ ብር)
  • Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Aug 12, 2026)
  • Posted at: 2026-08-12T07:59:07.000Z
← Back to all tenders