Office Machines and Computers
በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ወረዳ 03 ፋይናንስ ፅ/ቤት የኤሌክትሮኒክስ ጥገና፣ ፈርኒቸር ጥገና እና መስተንግዶ አገልግሎት እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Office Machines and ComputersMaintenance and RepairFurniture
Addis Ababa
More tags
Catering and Cafeteria ServicesWood and Wood WorkingEquipment and AccessoriesElectrical, Electromechanical and ElectronicsInstallation, Maintenance and Other Engineering ServicesComputer and AccessoriesIT and TelecomOffice Machines and AccessoriesOffice Supplies and ServicesAmharic2merkatoKolfe Keranio Sub City Woreda 3 FEDB
Description
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ 2ኛ ዙር
ቁጥር 002
በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ወረዳ 03 ፋይናንስ ፅ/ቤት ከዚህ በታች በሎት የተደራጁ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
- ሎት 1 .የኤሌክትሮኒክስ ጥገና
- ሎት 2. ፈርኒቸር ጥገና
- ሎት 3. መስተንግዶ አገልግሎት
በመሆኑም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 200(ሁለት መቶ ብር) በመክፈል በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 አስተዳደር ፋይናንስ ፅ/ቤት ካራ ቆሬ የሚገኘው ህንፃ ቀርበው መውሰድ እንደሚችሉ እናሳውቃለን።
ተጫራቾች ማሟላት የሚኖርባቸው ፡ -
- የዘመኑን የታደሰ የንግድ ፈቃድና የንግድ ምዝገባ ሰርተፊኬት ማቅረብ አለባቸው።
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን ናምበር/ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስረከቢያ የአስገቡት ዋጋ ለሁሉም ሎት 1.5 % በሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው።
- ተጫራቾች በጥቃቅንና አነስተኛ ከተደራጁ ሲፒዮ ማስያዝ አይጠበቅባቸውም በምትኩ የዋስትና ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው የሚቀርበው ደብዳቤ በኃላፊ መፈረም አለበት።
- የቫት ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባቸው የሚቀርበው የዋጋ ሰነድ ለቫት ተጠቃሚዎች ቫትን ያካተተ መሆን አለበት።
- ማንኛውም ተጫራች የታሸገ ፖስታ ላይ የድርጅቱ ማህተም መኖር አለበት።
- ማንኛውም ተጫራች የሚያቀርበው ሰነድ ኮፒና ዋና ማቅረብ ይኖርበታል።
- አሸናፊ ተጫራች በሰነድ ውስጥ በተመለከተው የጊዜ ገደብ ውስጥ ቀርቦ ውል መዋዋል አለባቸው።
- ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ከላይ የተጠቀሱትን መረጃዎች በማቅረብ ለጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ መውሰድ ይችላሉ።
- አንድ ተጫራች በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይችልም።
- የጨረታው ሳጥን ጨረታው አየር ላይ ከዋለ ከ10 የስራ ቀን በኋላ በአስራ አንደኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በወረዳው አስተዳደር ፋይናንስ ፅ/ቤት ውስጥ ይከፈታል።
- ተጫራቾች (በጨረታው) የተሸነፉ ድርጅቶች የጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ሲፒኦ ተመላሽ ይሆናል፡፡ ጽ/ቤቱ ሌላ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ
መስሪያ ቤቱ የሚገኝበት ልዩ ቦታ ካራ ቆሬ ሩታ ከግራር 200 ሜትር ገባ ብሎ ወረዳ 03 ፋይናንስ ጽ/ቤት መሆኑን እንገልጻለን።
በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ወረዳ 03 ፋይናንስ ፅ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-08-24
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ጨረታው አየር ላይ ከዋለ ከ10 የስራ ቀን በኋላ በአስራ አንደኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-08-24 10:30
- Bid opening (note): ጨረታው አየር ላይ ከዋለ ከ10 የስራ ቀን በኋላ በአስራ አንደኛው ቀን በ4፡30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Kolfe Keranio Sub City Woreda 3 FEDB
- Bid bond: ለሁሉም ሎት 1.5 %
- Bid document price: 200.00 ብር ለእያንዳንዱ ሎት
- Published on: Addis Zemen (Aug 12, 2026)
- Posted at: 2026-08-12T11:06:46.000Z