Vehicle

የድሬዳዋ ከተማ ጽዳት ውበት እና አረንጓዴ ልማት ኤጀንሲ በከተማው ውስጥ በሚሰጠው ስምሪት መሰረት በጽዳት ማህበራት ከቤት ለቤት የሚሰበሰበውን ደረቅ ቆሻሻ በተሽከርካሪ በመቀበል እስከ ቆሻሻ ማስወገጂያ ቦታ በማጓጓዝ የማስወገድ አገልግሎት መስጠት የሚፈልጉ ድርጅቶችን/ማህበራቶችን በጨረታ አወዳድሮ በኮንትራት ውል ለማሠራት ይፈልጋል

Description

የድሬዳዋ ከተማ ጽዳት ውበት እና አረንጓዴ ልማት ኤጀንሲ

ደረቅ ቆሻሻን በተሸከርካሪ በማጓጓዝ የማስወገድ አገልግሎት መስጠት ለሚችሉ

በጽዳት አገልግሎት ዘርፍ ፈቃድ ላላቸው ተጫራች ማሕበራት/ድርጅት የወጣ ለ2ኛ ጊዜ ጨረታ ማስታወቂያ

የድሬዳዋ ከተማ ጽዳት ውበት እና አረንጓዴ ልማት ኤጀንሲ በከተማው ውስጥ በሚሰጠው ስምሪት መሰረት በጽዳት ማህበራት ከቤት ለቤት የሚሰበሰበውን ደረቅ ቆሻሻ በተሸከርካሪ በመቀበል እስከ ቆሻሻ ማስወገጂያ ቦታ በማጓጓዝ የማስወገድ አገልግሎት መስጠት የሚፈልጉ ድርጅቶችን/ማህበራቶችን በጨረታ አወዳድሮ በኮንትራት ውል ለማሠራት በመፈለጉ ይህንን የጨረታ ማስታወቂያ አውጥቶአል።

በዚሁ መሰረት በከተማ ጽዳትና ውበት አገልግሎት ዘርፍ የተሰማሩ ማሕበራት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶችን በማሟላት የጨረታ ሰነዱን በመግዛት በጨረታው ላይ መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እናስታውቃለን።

የተጫራቾች መመሪያ

  • ተጫራቾች በከተማ ጽዳት እና ውበት ዘርፍ በማሕበር የተደራጁና ህጋዊ የታደለ የስራ ፈቃድ ያላቸው የግብር ከፋይ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችልየዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
  • የቫት ከፋይ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ የሚያቀርቡ
  • ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ የተቀመጡ መመሪያዎች የመገምገሚያና ቴከኒካል መስፈርቶቹ የሚጠይቁትን ተዛማጅ ጉዳዮች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።
  • ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በድሬ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰአት ከከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ፋ/ግ/ንብ/አስተዳደር ክፍል በመቅረብ የማይመለስ 300 ብር በመክፈል መግዛት ይችላሉ።
  • ተጫራቾች የገዙትን የጨረታ ሰነድ በሚገባ አንብበውና ተረድተው በመሙላት አንድ ኦሪጂናልና ሁለት ኮፒ የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን ይህ ማስታወቂያ በድሬ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት እስከ 21ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 3 ሰአት ድረስ የጨረታ ሰነዱን ከገዙበት ከከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ፋ/ግ/ንብ/አስተዳደር ክፍል ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  • ተጫራቾች የሚመለስ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000 /አስር ሺህ ብር/ በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተመሰከረ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  • የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ሳጥኑ ይህ ማስታወቂያ በድሬ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት እስከ 22ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡ዐዐ ሰአት ድረስ ከፍት ሆኖ ከቆየ በሁዋላ 4፡00 በዛኑ ቀንና ሰአት ተዘግቶ ወዲያውኑ 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
  • ተጫራቾች የበለጠ መረጃዎችን ከሚገዙት የጨረታ ሰነድ ላይ መመልከት ይኖርባቸዋል
  • አስፈላጊ የሆኑ ማብራሪያዎችን ከጽደትና ውበት ኤጀንሲ ቢሮ ወይም ከከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ፋ/ግ/ንብ/አስተዳደር ከፍል በመጠየቅ ማግኘት ይቻላል።
  • መ/ቤቱ የተሸለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ ለሙሉ የመሰረዝ መብት አለው
  • ማሣሰቢያ፡-መ/ቤቱ በጨረታው የተሸለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  • ለበለጠ መረጃ የስ/ቁ 09 15 75 53 24/09 15 00 17 11
  • አድራሻ፡- ድሬደዋ ከተማ ሥራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ቢሮ (ቴሌ ትራፊክ መብራት ከፍ ብሎ)

Tender details

  • Deadline: 2026-08-29
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በድሬ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት እስከ 22ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰአት
  • Bid opening: 2026-08-29 12:00
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በድሬ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት እስከ 22ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰአት
  • Region: Dire Dawa
  • Publishing entity: የድሬዳዋ ከተማ ጽዳት ውበት እና አረንጓዴ ልማት ኤጀንሲ
  • Bid bond: 10,000.00 (አስር ሺ ብር)
  • Bid document price: 300.00 ብር
  • Published on: Melekite Dire (Aug 05, 2026)
  • Posted at: 2026-08-12T13:15:15.000Z
← Back to all tenders