Billboards and Digital Advertising

የመንግስት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር የህንፃ ላይ ስም ጽሁፍ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የመንግስት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር በፌዴደራል መንግስት የግዥ አፈጻጸም ሥርዓትን ለመወሰን ባወጣው መመሪያ ቁጥር 1073/17 መሰረት የህንፃ ላይ ስም ጽሁፍ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በዚሁ መሠረት፡-

  • ሎት 1. የህንፃ ላይ ስም ጽሁፍ

1.ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የምዝገባ ምስከር ወረቀት፣ የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልፅ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤ እንዲሁም በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ማስረጃ (ክሊራንስ) ጊዜው ያላለፈበት ከገቢዎች ሚኒስቴር የሚያቀርቡ መሆን አለባቸው፡፡

2.ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ቀን ድረስ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ከአራት ኪሎ ወደ መገናኛ በሚወስደው መንገድ ህጻናት እና ወጣቶች ቴአትር ፊት ለፊት የመንግስት ሠራተኞች ማኀበራዊ ዋስትና አስተዳደር ከግዥ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 313 መግዛት የሚችሉ ሲሆን የሚጫረቱበትን ዋጋ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተያይዞ በሚገኘው የዋጋ ማቅረቢያ ሠንጠረዥ ላይ በመሙላት የቴክኒካልእና የፋይናንሽያል ሰነድ በኮፒ እና ኦርጅናል ለየብቻ በማድረግ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ አሽገው ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ የመንግስት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር የግዥ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 313 ማስገባት አለባቸው፡፡

3.ተጫራቾች ለተፈላጊ አቅርቦቶች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000.00 (አስር ሺህ ብር) ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ የጨረታ ሳጥኑ ከመከፈቱ በፊት ማስያዝ አለባቸው::

4.ጨረታው አየር ላይ በዋለበት በ11ኛው ቀን ከሰአት 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ የሚከፈተውም በዚሁ ዕለት ተጫራቾች ወደም ህጋዊ ወኪሎቻቻው በተገኙበት ከሰአት 8፡30 የመንግስት ሠራተኞች ማኀበራዊ ዋስትና አስተዳደር ግዥ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 313 ነው። 11ኛው ቀን የእረፍት ወይም የበዓል ቀን ከሆነ ጨረታው ከላይ በተገለጸው ሰዓት በቀጣዩ የሥራ ቀን ይከፈታል።

5.አስተዳደሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ስልክ ቁጥር-0111-2326 99

የመንግስት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር


Tender details

  • Deadline: 2026-08-25
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid closing (note): የጨረታውን ሰነድ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከሰአት 8፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-08-25 14:30
  • Bid opening (note): የጨረታውን ሰነድ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከሰአት 8፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Public Servants Social Security Administration
  • Bid bond: 10,000.00 (አስር ሺ ብር)
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Aug 14, 2026)
  • Posted at: 2026-08-14T07:28:25.000Z
← Back to all tenders