Accounting and Auditing, Accounting System Design

የኮንሶ ምሁራን ማህበር (Konso Intellectual Association) የ2018 በጀት ዓመት የሂሳብ ሰነዶቹን በሕጋዊ እና በውጭ ኦዲተር አወዳድሮ ለማስመርመር ይፈልጋል

Description

የኦዲት ጨረታ ጥሪ ማስታወቂያ

የኮንሶ ምሁራን ማህበር (Konso Intellectual Association) የ2018 በጀት ዓመት የሂሳብ ሰነዶቹን በሕጋዊ እና በውጭ ኦዲተር አወዳድሮ ለማስመርመር ይፈልጋል። በመሆኑም ሕጋዊ የኦዲት ድርጅቶች ባለሙያዎች በሚከተሉት መስፈርቶች መሠረት እንዲወዳደሩ ይጋብዛል።

ተጫራቾች ሊያሟሏቸው የሚገቡ መስፈርቶች፦

የንግድ ፈቃድ፦ በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ የኦዲት ሥራ ንግድ ፈቃድ ያላቸው።

የምዝገባ ምስክር ወረቀት፦ ከኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝ እና ኦዲት ቦርድ (AABE) የተሰጠ ሕጋዊ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ

የግብር ከፋይ መለያ፦ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) እና የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ምዝገባ ሰነድ ማቅረብ የሚችሉ።

  • የሥራ ልምድ፦ ለትርፍ ያልተቋቋሙ ማህበራትን ወይም የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችን ኦዲት በማድረግ ረገድ በቂ የሥራ ልምድ ያላቸው እና ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ (ቅድሚያ ይሰጣል)።
  • የማመልከቻ አቀራረብ እና የጊዜ ገደብ፦
  • ተጫራቾች የቴክኒክ እና የፋይናንሻል (የዋጋ) ማቅረቢያ ሰነዶቻቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  • ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 6 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ሰነዳቸውን ማስገባት ይችላሉ።
  • የማስረከቢያ ቦታ፦ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ጀርሜን አደባባይ አጠገብ ባለው የጉዲና ቱምሳ ሕንፃ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 401።
  • ለበለጠ መረጃ በ 09 95 80 31 31 ይደውሉልን።

የኮንሶ ምሁራን ማህበር

(Konso Intellectual Association)


Tender details

  • Deadline: 2026-08-20
  • Bid closing time: 17:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 6 ተከታታይ የሥራ ቀናት
  • Bid opening: 2026-08-20 17:00
  • Bid opening (note): የጨረታው መክፈቻ ቀንና ሰዓት አልተገለፀም
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Konso Intellectual Association
  • Published on: Addis Zemen (Aug 14, 2026)
  • Posted at: 2026-08-14T08:01:56.000Z
← Back to all tenders