House and Building Sale
በድጋሚ የወጣ የቦታው ስፋት 171 ካ/ሜ ቤት የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
Description
በድጋሚ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
የፍ/ባለመብት አቶ ሲሳይ ገ/ማርያም እና የፍ/ባለዕዳ እነ አለማየሁ ገ/ማርያም መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 310986 30/4/2016 ዓ ም በ24/11/2015 ዓ/ም እና በኮ/መ/ቁ 315829 በ14/06/2016 ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 4 ውስጥ የሚገኝ የቤት ቁጥር 579 የሆነው በአመልካችና በተጠሪዎች ስም ተመዝግቦ የሚገኝ መኖርያ ቤት በቁጥር ል.4/22/4190/01 የተመዘገበ የተነፃፃሪ ካርታ ያለው ጠቅላላ በፕሮፖርሽን ለግለሰቡ የሚደርሰው የቦታው ስፋት 171 ካ/ሜ ቤቱ (ቦታው) የሚገኝበት አካባ ከዚህ ቀደም በጌጃ መልሶ ማልማት ፕሮጀክት የተያዘ መሆኑና እስከ አሁን ያልተነሳ የባለሙያ ግምት 5,948,721 (አምስት ሚሊዮን ዘጠኝ መቶ አርባ ስምንት ሽህ ሰባት ሀያ አንድ ብር) ሆኖ የትራክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ህዳር 3 ቀን 2017 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል። የሚል ማስታወቂያ ወጥቶ በእለቱ ተጫራች ያለቀረበ በመሆኑ ጨረታው ተቋርጧል :: በዚህ መሰረት ለፍ/ቤት ተጽፎ ፍ/ቤቱ በ11/3/2017 ዓ.ም በሰጠው ትዕዛዝ በድጋሚ እንዲወጣ ባዘዘው መሰረት መጫረት የሚፈልግ የግምቱ 1/4 ብር 1,487,180.25 (አንድ ሚሊዬን አራት መቶ ሰማንያ ሰባት ሺ አንድ መቶ ሰማንያ ብር ከ25/100 ሳንቲም) ምዝገባ ሆኖ የትራክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ መስከረም 11 ቀን 2019 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ 8፡30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።
የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፓርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጎብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ኛው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት ስም CPO አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251 112 730 852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
የፌዴራል ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-09-21
- Bid closing time: 14:30
- Bid opening: 2026-09-21 14:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Federal Courts Judgement Execution Directorate
- Bid bond: 25%
- Published on: Addis Zemen (Aug 14, 2026)
- Posted at: 2026-08-14T08:39:39.000Z