Building Construction

የአዲሰ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ከተማ አስተዳደሩ በልዩ ትኩረት እየተገበረ ለሚገኘው መጠነ ሰፊ የቤት ልማት ፕሮግራም በግንባታው ዘርፍ ላይ የተሰማሩና መስፈርቱን የሚያሟሉ ሥራ ተቋራጮችን አወዳድሮ ለማሰራት ይጋብዛል

Description

ማስታወቂያ

የአዲሰ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ከተማ አስተዳደሩ በልዩ ትኩረት እየተገበረ ለሚገኘው መጠነ ሰፊ የቤት ልማት ፕሮግራም በግንባታው ዘርፍ ላይ የተሰማሩና መስፈርቱን የሚያሟሉ ሥራ ተቋራጮችን አወዳድሮ ለማሰራት ይጋብዛል።

በዚሁ መነሻ

1. ለስራ ተቋራጮች ምዝገባ መሟላት ያለባቸው መረጃዎች፡-

ሀ) የታደሰ የንግድ ፍቃድ፣የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ስለመመዝገቡ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል 

በምዝገባው ወቅት የሰነዶቹን ዋና እና አንድ የማይመለስ ቅጂ በአካል የሚቀርብ ሆኖ የስራ ተቋራጩ የበላይ ኃላፊ፣ ባለቤት ወይም ህጋዊ ውክልና ያለው ተወካይ ፊርማ እና የድርጅቱ ህጋዊ ማህተም በማድረግ ማቅረብ ይጠበቅበታል።

2. ከደረጃ 1-4 ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ (GC) እና (BC) ህንፃ ተቋራጭ እንዲሁም ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ (GC) ደረጃ 5 የብቃት ማረጋገጫ ያላቸው በግንባታው ዘርፍ ላይ የተሰማሩ ስራ ተቋራጮች ተሳታፊ መሆን ይችላሉ።

3. ቅዳሜ 09/12/2018 ዓ/ም (ከጠዋቱ 2፡30) ቅዳሜ ሙሉ ቀን ጨምሮ ለ5 (አምስት)  ተከታታይ የስራ ቀናት (እስከ ሐሙሰ 14/12/2018 ከሰዓት 11፡30) ድረስ በአካል በመቅረብ በኮርፖሬሽኑ 11ኛ ወለል በሚገኝ አዳራሽ ላይ ምዝገባ በማድረግ መረጃዎቹ መሟላታቸው በመዝጋቢው ሲረጋገጥ ለዚሁ የተዘጋጀ የቴክኒካል ሰነድ መግዛት ይቻላል።

4. ተገቢውን ሰነድ በማቅረብ የምዝገባ ሂደቱን በሚገባ ያሟሉ ተቋራጮችን በተመለከተ ምዝገባው በተጠናቀቀ በ24 ሰዓት ውስጥ በቀን 15/12/2018 ዓ/ም በተቋሙ ማህበራዊ  ድህረ ገጽ እና በኮርፖሬሽኑ የማስታወቂያ ቦርድ 11ኛ ወለል የሚለጠፍ ይሆናል።

5. ተቋራጮች የቅድመ ምዝገባ ውጤት ከታወቀበት ቀን ጀምሮ በአስር (10) ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ቅጂ የቴክኒካል ፕሮፖዛላቸውን ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን እስከ ቀን 27/12/2018 ዓ/ም ከሰዓት 11፡30 ድረስ ብቻ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

6. ተቋራጮች ለምዝገባ እና ለቴክኒካል ሰነድ ግዢ የማይመለስ ብር ለደረጃ 1 ብር 7500 ለደረጃ 2 ብር 6500 ለደረጃ 3 ብር 5500 ለደረጃ 4 ብር 5000 ለደረጃ 5 ብር 4500 መክፈል  ይጠበቅባቸዋል።

አድራሻ
አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቂርቆስ ክ/ተማ ወረዳ 01 ባምቢስ አከባቢ ግሪክ ት/ቤት ፊት ስፊት በሚገኘው የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ህንፃ
https://linktr.ee/aahdc 
የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን


Tender details

  • Deadline: 2026-09-02
  • Bid closing time: 17:30
  • Bid opening: 2026-09-02 17:30
  • Bid opening (note): የጨረታ መክፈቻ ቀንና ሰዓት አልተገለጸም
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Addis Ababa Housing Development Corporation
  • Buyer address: በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ 1 ባንቢስ አካባቢ ግሪክ ት/ቤት ፊት ለፊት የሚገኘው አዲስ ሕንፃ
  • Bid document price: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Published on: Addis Zemen (Aug 15, 2026)
  • Posted at: 2026-08-15T08:50:21.000Z
← Back to all tenders