House and Building Sale

የቦታው ስፋት 3,435 ካ.ሜ የሆነ ድርጅት ቤት የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

Description

የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

የፍ/ባለመብት ሰኢድ አህመድ ነር እና የፍ/ባለዕዳ ብሉ ናይል ጥቃቅንና አነስተኛ ንግድ ስራዎች አክሲዮን ማህበር መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር335823 በ30/10/2017 ዓ/ም እና በኮ/መ/ቁ/344562 በ18/05/2018 ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት ፍርድ ያረፈበት በብሉናይል ጥቃቅንና አነስተኛንግድ ስራዎች አክሲዮን ማህበር ስም የተመዘገበ በካርታ ቁጥር የካ/239771/13 በሰሪያል ቁጥር 0161894 የቦታው ስፋት 3,435 ካ/ሜ የቤቱ አገልግሎት ለድርጅት የሆነ በለሚ ኩሪ ክ/ከተማ ወረዳ 02 የሚገኝ በአሁኑ ጊዜ ጅምር ቤትና አንድ ወለል ስራ የተከናወነ ግንባታየሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 272,145,376.75 (ሁለት መቶ ሰባሁለት ሚሊዮን አንድ መቶ አርባ አምስት ሺህ ሶስት መቶ ሰባ ስድስት ከ75/100) ሆኖ የትራክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆነ ታውቆ መስከረም 13 ቀን 2019 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል የተጫራቾች ምዝገባ 4፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።

የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራትየሥራቀናቶች ውስጥ ባለመብቱለማስጎብኘት በሚመርጧቸውሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻበመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፓርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል። ከ1/4ኛው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም። በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት ስም CPO አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን። 

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251 11 273 0852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

የፌዴራል ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-23
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-09-23 10:00
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Federal Courts Judgement Execution Directorate
  • Bid bond: 25%
  • Published on: Addis Zemen (Aug 15, 2026)
  • Posted at: 2026-08-15T09:55:47.000Z
← Back to all tenders