Financial

ኦሮ-ፍሬሽ ኢንተርፕራይዝ የውጭ ኦዲት አገልግሎት እና የ5 ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅድ ዝግጅት አማካሪዎች ይፈልጋል

Description

የክፍት ጨረታ ማስታወቂያ

ኦሮ-ፍሬሽ ኢንተርፕራይዝ በሚከተሉት የአማካሪነት አገልግሎቶች ላይ ብቁና በሕግ የተመዘገቡ አማካሪ ድርጅቶችን በአገር አቀፍ ክፍት ጨረታ (National Competitive Bidding) እንዲወዳደሩ ይጋብዛል።

ሎት 1፡ የውጭ ኦዲት አገልግሎት

የኦሮ-ፍሬሽ ኢንተርፕራይዝ የ2017 የበጀት ዓመት የፋይናንስ ሂሳብ በኢንተርናሽናል ኦዲቲንግ ስታንዳርዶች (ISA) እና በኢትዮጵያ ሕጎች መሠረት የውጭ ኦዲት ለማካሄድ የሚችሉ ፈቃድ ያላቸው የኦዲት ድርጅቶች እንዲወዳደሩ ይጋበዛሉ።

ሎት 2፡ የ5 ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅድ ዝግጅት

ኢንተርፕራይዙ የ2019 -2023 የ5 ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅድ፣ የአፈፃፀም ማዕቀፍ (Implementation Framework)፣ የክትትልና የግምገማ ስርዓት (Monitoring & Evaluation Framework)፣ የKPl ማዕቀፍ፣ የአደጋ አስተዳደር ማዕቀፍ እና የአፈፃፀም መለኪያዎችን የሚያካትት ስትራቴጂክ ዕቅድ ለማዘጋጀት ብቁ የአማካሪ ድርጅቶችን ይጋብዛል።

የመሳተፍ መስፈርቶች ተጫራቾች፦

  • ለ2018 የታደሰ የንግድ ፈቃድ የTIN ምዝገባ ሰርቲፊኬት
  • የVAT ምዝገባ ሰርቲፊኬት የ2018 የግብር ክሊራንስ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
  • በዘርፉ የሙያ ፈቃድ እና ቢያንስ 5 ዓመት ተመሳሳይ የሥራ ልምድ ሊኖራቸው ይገባል።
  • ለሎት 1 የፌዴራል የኦዲት ባለሙያ ፈቃድ ያለው ድርጅት መሆን አለበት።
  • ለሎት 2 በስትራቴጂክ ዕቅድ ዝግጅት፣ ድርጅታዊ ለውጥ፣ KPl እና  Performance Management ላይ በቂ ልምድ ማሳየት አለበት።

የጨረታ ሰነድ

ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ከኦሮ-ፍሬሽ ኢንተርፕራይዝ ዋና መሥሪያ ቤት በመደበኛ የሥራ ሰዓት መውሰድ ይችላሉ።

የጨረታ ዋስትና

ሎት 1 (ኦዲት አገልግሎት): ብር 20,000.00 ሎት 2 (ስትራቴጂክ ዕቅድ)፡ ብር 20,000.00 ዋስትናው በCPO ወይም በባንክ ጋራንቲ መቅረብ አለበት።

የሰነድ ማቅረቢያ

የቴክኒክ እና የፋይናንስ ሰነዶች በተለያዩ የታሸጉ ፖስታዎች (Two Envelope System) መቅረብ አለባቸው።

ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከታተመበት ቀን ጀምሮ በ14ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በፊት መቅረብ አለበት።

ጨረታው በዚያው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት በተጫራቾች ወይም በሕጋዊ ወኪሎቻቸው ፊት ይከፈታል።

የኢንተርፕራይዙ መብት

ኦሮ-ፍሬሽ ኢንተርፕራይዝ ማንኛውንም ወይም ሁሉንም ጨረታዎች በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱን ያስጠብቃል።

አድራሻ

አዲስ አበባ፣ ደንበል ሲቲ የገበያ ማይክል 10ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 1001

ስልክ:+251 96 633 4593//+251 11 014 488/+251 94 599 9994/+251 91 344 0291

ኦሮ-ፍሬሽ ኢንተርፕራይዝ


Tender details

  • Deadline: 2026-08-29
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከታተመበት ቀን ጀምሮ በ14ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-08-29 10:30
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከታተመበት ቀን ጀምሮ በ14ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: ኦሮ-ፍሬሽ ኢንተርፕራይዝ
  • Bid bond: 20,000.00 ብር ለእያንዳንዱ ሎት
  • Bid document price: 500.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Aug 16, 2026)
  • Posted at: 2026-08-17T09:21:03.000Z
← Back to all tenders