House and Building Foreclosure

ፀደይ ባንክ አ.ማ. የመኖሪያ ቤት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የኃራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

ፀደይ ባንክ አ.ማ አቶ ለማ ተፈራ ሶሪ ለሰጠው ብድር በመያዣ የያዘውን በኦሮሚያ ክልል ቢሾፍቱ ከተማ የካርታ ቁጥር OR003075014013 በአቶ ጌታሁን ወዳይ ደረሰ ተመዝግቦ የሚገኘውን የመኖሪያ ቤት በአዋጅ ቁጥር 97/90 በተሰጠዉ ስልጣን መሰረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

በመሆኑም ተጫራቾች ለጫረታ ከመቅረባቸዉ በፊት የሚከተሉትን ደንቦች በመገንዘብ መመረት እንዲችሉ ይጋብዛል፦

1. የቤቱ የጨረታ መነሻ ዋጋ ብር 609,650.62 /አራት ሚሊዮን ስድስት መቶ ዘጠኝ ሽህ ስድትስ መቶ ሃምሳ ብር 62/100/

2. ተጫራቾች የቤቱ ጨረታ መነሻ ዋጋ ብር 1/4 (በጥሬ ገንዘብ ወይም በሲፒኦ) በጸደይ ባንክ ኢማ ስም በማሰራት ለጫረታ ማስክበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

3 የጫረታዉ አሸናፊ አሸናፊነቱ የሚረጋገጠዉ የጫረታዉ ዉጤት በሚመለከተዉ አካል ጸድቆ በባንኩ ደብዳቤ ሲሰጠዉ ብቻ ይሆናል።

4. በጫረታዉ የሚሳተፈዉ በህግ ሰዉነት ያገኘ ከሆነ የድርጅቱ መመስረቻ ጽሁፍ ወይም መተዳደሪያ ደምብ፤ ህጋዊ ሰዉነት ያገኘበት የምዝገባ የምስክር ወረቀት እንዲሁም ህጋዊ ዉክልና ማቅረብ አለበት።

5. የጫረታዉ አሸናፊ አሸናፊነቱ በባንኩ በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ10 ቀናት ዉስጥ አጠቃሎ መክፈልና በጫረታ ያሸነፈዉን ንብረት መረከብ ይኖርበታል። አሸናፊዉ በ10 ቀናት ዉስጥ ገንዘቡን ካልከፈለ ጨረታዉ ተሰርዞ ለጨራታ ማስከበሪያ ያስያዘዉ ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል።

6. በጨረታዉ ለተሽነፉ ተጫራጮች ያስያዙት ጥሬ ገንዘብ ወይም ሲ.ፒ.ኦ ይመለስላቸዋል።

7. የጫረታ አሸናፊዉ ከሚገዛዉ ንብረት ዋጋ በተጨማሪ ከቤቱ ጋር የተያያዙ ማናቸዉም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎች፡ ግብር፤ ተጨማሪ እሴት ታክስ 15% እና ከስም ዝዉዉሩ ጋር የሚገናኙ ማንኛዉንም ወጭዎች ገዢ ይሸፍናል ይከፍላል። ዉዝፍ የሊዝ ክፍያ ካለ ባንኩ የሚከፍል ሆኖ ለቀረዉና የክፍያ ጊዜዉ ላልደረሰ የሊዝ ክፍያ ገዢ ከሚመለከተዉ የመንግስት አካል ጋር እንዲዋዋል ይደረጋል።

8. ተጫራቾች ቤቱን /ድርጀቱን/ በባንኩ አማካኝነት መጎብኘት ወይም ማየት ይችላሉ።

9. ጨረታዉ የሚካሄደዉ መሰከረም 05/2019 ከጠዋቱ 3.00-500 የተጫራቾች ምዝገባ፤ ከ5፡00 እስከ ቀኑ 6:00 ሰዓት ጫረታ በኦሮሚያ ክልል ጨለለቃ ክ/ከተማ ቢሾፍቱ ሆዳነቢይ

10.ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጫረታዉን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የጠተበቀ ነዉ።

ለተጨማሪ መረጃ፡- ፀደይ ባንክ ቢሾፍቱ ቅርንጫፍ

በስ.ቁ 01143303062/0912292609 ደዉሎ መጠየቅ ይቻላል።


Tender details

  • Deadline: 2026-09-15
  • Bid closing time: 11:00
  • Bid opening: 2026-09-15 11:00
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Tsedey Bank S.C.
  • Buyer address: Legahar Orda Building, 8th Floor room No-804
  • Bid bond: 25%
  • Published on: Reporter (Aug 16, 2026)
  • Posted at: 2026-08-17T11:27:34.000Z
← Back to all tenders