Accounting and Auditing, Accounting System Design
ተፈዘር የገበያ ማዕከል አክሲዮን ማህበር ከ2018 ዓ.ም ለ3 ተከታታይ ዓመት የማህበሩን ሂሳብ ኦዲት መስጠት ይፈልጋል
Description
የኦዲት ጨረታ ማስታወቂያ
ተፈዘር የገበያ ማዕከል አክሲዮን ማህበር ከ2018 ዓ.ም ለ3 ተከታታይ ዓመት የማህበሩን ሂሳብ ኦዲት መስጠት ይፈልጋል::
ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለፁትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ ትችላላችሁ::
1. የኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ ወይም እሱ ከሚወክለው አካል ሂሳብ ለመመርመር የሚያስችለውን የሙያ ፈቃድ ያገኘና የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል፣
2. በሀገሪቱ ህግ መሰረት የኦዲት ስራ ለመስራት የሚያስችል ወቅታዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣የቫት ሰርተፍኬት፣ቲን፣የታደሰ የታክስ ክሊራንስ ሰርተፍኬት ልምድ ማስረጃዎች የሥራ እቅድ እና ዘዴዎች ያለው፣
3. ተወካዩ የሂሳብ መርማሪ ወይም ከሂሳብ መርማሪው ቡድኑ አባላት ውስጥ ቢያንስ አንዱ ከዚህ በፊት የገበያ ማዕከል ሂሳብ የመረመረ ቢሆን ቅድሚያ ይሰጠዋል፣
4. የገበያ ማዕከል ሂሳብ ለመመርመር ብቁ ባለሙያዎችን በሥራ ላይ ማሰማራት የሚችል፣ይህ ሳይሆን ቀርቶ ለሚከተለው ማንኛውም ኪሳራና ችግር አስቀድሞ ኃላፊነቱን የሚወስድ፣
5. እንደአስፈላጊነቱ አግባብ ባለው ባለስልጣን የሚጠየቁ ሌሎች መረጃዎችን ማቅረብ የሚችል እንዲሁም የኦዲት ሪፖርቱን በአማርኛና በEnglish ማቅረብ የሚችል፣
6. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በስም በታሸገ ኤንቨሎፕ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ ለ15 የሥራ ቀናት ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2፡30–6፡30 እና ከሰዓት 7፡30-11፡30 ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
7. የጨረታው ምዝገባው በተጠናቀቀ በቀጣይ የሥራ ቀን ከሰዓት 10፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል:: ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በራሳቸው ምክንያት መገኘት ካልቻሉ ጨረታው በተገኘው ሰው ይከፈታል::
አድራሻችን፡- ሰዓሊተ ምህረት ቤተክርስቲያን አጠገብ በሚገኘው የድርጅቱ ቢሮ /አዲስ አበባ ከሚገኘው የስራ አመራር ኢንስቲትዩት ፊት ለፊት ያለ ተፈዘር የገበያ ማዕከል አክሲዮን ማህበር ግቢ ውስጥ በሚገኘው ቢሮ/
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 09-07-37-41-44 ወይም 09-04-77-72-22 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፣
Tender details
- Deadline: 2026-09-03
- Bid closing time: 16:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ ለ15 የሥራ ቀናት ቆይቶ በቀጣይ የሥራ ቀን ከሰዓት 10፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-09-03 16:00
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ ለ15 የሥራ ቀናት ቆይቶ በቀጣይ የሥራ ቀን ከሰዓት 10፡00 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Tefezer Commercial Share Company
- Published on: Reporter (Aug 16, 2026)
- Posted at: 2026-08-17T12:26:36.000Z