Land Lease & Real Estate

የሐረሪ ሕዝብ ክልላዊ መንግሥት የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ባለሥልጣን ለንግድ እና ለመኖሪያ አገልግሎቶች የተዘጋጁ ቦታዎችን በመደበኛ የሊዝ ጨረታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የሐረሪ ሕዝብ ክልላዊ መንግሥት የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ባለሥልጣን የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀፅ 8 ንዑስ አንቀፅ 1 በፊደል ተራ (ሀ - ሠ) በተዘረዘረው መሠረት በሐረሪ ክልል ስምንት (8) በተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ፦

>ኢንዱስትሪ ዞን አካባቢ >Kim Cafe አካባቢ >ደከር ኬሌ አካባቢ >SOS አካባቢ >ኦሜድላ አካባቢ >Guesthouse አካባቢ >ሪፍት ቫሊ (Rift Valley) አካባቢ ቀላደንባ አካባቢ

ለእነዚህ ቦታዎች ለንግድ እና ለመኖሪያ አገልግሎቶች የተዘጋጁ ቦታዎችን በመደበኛ የሊዝ ጨረታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል።

የተጫራቾች መመሪያ እና የመወዳደሪያ መስፈርቶች፦

1. የሰነድ ሽያጭ፦ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተወዳዳሪ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን 12/12/2018 ዓ.ም ጀምሮ የቦታውን ዝርዝር መረጃ የያዘውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 1,500 (አንድ ሺህ አምስት መቶ ብር) በመክፈል በሐረሪ ክልል ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ የግዥና ፋይናንስ ሂደት (3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 32) ዘወትር በሥራ ቀናትና በሥራ ሰዓት መግዛት የሚችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

2. የሰነድ ማስገቢያ ጊዜ፦ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስር (10) ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ሰነዱን በመግዛት ለቦታዎች በካሬ ሜትር የሚያቀርቡትን ዋጋ እና የሚከፍሉትን የሊዝ ቅድመ ክፍያ በጨረታ መወዳደሪያ መልስ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ በመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ 25/12/2018 ዓ.ም ከቀኑ 11:00 ሰዓት ድረስ ብቻ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

3. የሳጥን መዘጋትና መክፈቻ፦ የጨረታ ሳጥኑ በ25/12/2018 ዓ.ም ከቀኑ 11:00 ሰዓት ተዘግቶ በሁለተኛው ቀን 26/12/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ 4ኛ ፎቅ በሚገኘው አዳራሽ የሚከፈት ይሆናል።

4. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (CPO)፦ ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ቦታ የጠቅላላው የቦታ ስፋት በመነሻ ዋጋው ተባዝቶ ከሚገኘው ውጤት አምስት በመቶ (5%) በባንክ በተረጋገጠ የገንዘብ ክፍያ ትዕዛዝ (CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

5. የግምገማ ነጥብ አሰጣጥ፦ ተጫራቾች የሚያቀርቡት የሊዝ ዋጋ 70 በመቶ (70%) ነጥብ የሚኖረው ሲሆን፣ የቅድመ ክፍያ መጠን ደግሞ 30 በመቶ (30%) ነጥብ ይኖረዋል። የጨረታው አሸናፊ የሚለየው በሁለቱ ነጥቦች ድምር በሚገኘው ከፍተኛ ውጤት ይሆናል።

6. የቅድመ ክፍያ ወለል (Minimum Down Payment)፦ ተጫራቾች የሚያቀርቡት የቅድመ ክፍያ መጠን ከአጠቃላይ የሊዝ ዋጋ ለንግድ ከ30% እንዲሁም ለመኖሪያ ከ20% ማነስ የለበትም።

7. የCPO ተመላሽ፦ የተጫራቾች አሸናፊ ተለይቶ በማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ በግልጽ በይፋ ከተገለጸ በኋላ በጨረታው የተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ (CPO) ተመላሽ ይደረግላቸዋል።

8. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ አልያም በባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ ይፋዊ ድረ-ገፅ https://www.hararilanddev.gov.et  ማግኘት ይችላሉ።

9. (ባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።)

የሐረሪ ሕዝብ ክልላዊ መንግሥት የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ መሬት ልማትና ማኔጅመንት ባለሥልጣን


Tender details

  • Deadline: 2026-08-31
  • Bid closing time: 17:00
  • Bid opening: 2026-09-01 10:00
  • Region: Hareri
  • Publishing entity: Harari City Government City Development Construction Office
  • Bid bond: የጠቅላላው የቦታ ስፋት በመነሻ ዋጋው ተባዝቶ ከሚገኘው ውጤት 5%
  • Bid document price: 1,500 (አንድ ሺህ አምስት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Aug 17, 2026)
  • Posted at: 2026-08-18T08:21:19.000Z
← Back to all tenders