Building Construction

የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት በአዋሽ ኦፕሬሽናል ነዳጅ ዴፖ ውስጥ የተለያዩ የሲቪል የግንባታ ሥራዎች ለማሠራት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡06/2019

የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት በአዋሽ ኦፕሬሽናል ነዳጅ ዴፖ ውስጥ የተለያዩ የሲቪል የግንባታ ሥራዎች በመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን ለመንግስት ልማት ድርጅቶች በተዘጋጀው ለኮንስትራክሽን ስራዎች የሚውል የጨረታ ሰነድ መሰረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል::

ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መመዘኛዎች ማሟላት የሚችሉ ደረጃ 5 እና ደረጃ 6 የሆነ ሥራ ተቋራጮች ብቻ መወዳደር ይችላሉ::

1. ተጫራቾች የሚከተሉትን ሠነዶች ከመጫረቻ ሠነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል:: የዘርፉ ሕጋዊ የንግድ ፍቃድ ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስክር ወረቀት (VAT)፣የግብር ከፋይነት ሠርተፍኬት (TIN)፣ የአቅራቢዎች ምዝገባ የምስክር ወረቀት እና ስለ ግብር አከፋፈል የተሰጠ ማስረጃ

2. በተ.ቁ 1 ከተጠቀሱት በተጨማሪ ተጫራቾች ደረጃቸውን የሚገልጽ የታደሰ የምስክር ወረቀት፣ ለሥራው የሚያስፈልጉ መሣሪያዎችና ተሽከርካሪዎች ዝርዝር መግለጫ ለሥራው የሚያስፈልጉ የባለሙያዎች መግለጫና ዝርዝር እና በጨረታው ለተጠየቀው ሥራ ወይም ተመሳሳይ የሥራ ልምድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል::

3. ተጫራቾች በCPO ወይም በባንክ ጋራንቲ ብር 400,000.00 የጨረታ ማስከበሪ ከመጫረቻ ሠነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል::

4. ተጫራቾች ለግንባታ ስራው አንድ ኦሪጂናልና አንድ ኮፒ የመወዳደሪያ ሰነድ በታሸገ ኢንቨሎፕ እስከ 8/1/2019 ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ በድርጅቱ የስብሰባ አዳራሽ ቢሮ ቁጥር 602 ለዚህ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል::

5. ጨረታው በዚሁ ቀን 8/1/2019 ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ዕለት 4፡05 ሰዓት ተጫራች ወይም ሕጋዊ ወኪሎች በተገኙበት በቢሮ ቁጥር 602 ይከፈታል::

6. ተጫራች የሥራውን ዓይነትና ሁኔታ በአካል በመገኘት ማየትና ማብራሪያ ማግኘት ይችላሉ

7. ተጫራች የጨረታውን ሠነድ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን አንስቶ ከድርጅቱ ግዥና ትራንስፖርት ክፍል ቢሮ ቁጥር 011 መውሰድ ይችላሉ::

8. ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው: አድራሻ፡- ሜክሲኮ አደባባይ ወይ ሣርቤት በሚወስደው መንገድ 300 ሜትር ዝቅ ብሎ

የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ስልክ ቁጥር 011-551-32-88
የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-18
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-09-18 10:05
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Ethiopian Petroleum Supply Enterprise
  • Buyer address: ሜክሲኮ አደባባይ ወደ ሳርቤት በሚወስደው መንገድ 300 ሜትር ዝቅ ብሎ ስልክ ቁጥር 011-551-3288 ፖ.ሣ.ቁ 3375 አአ
  • Bid bond: 400,000.00 ብር
  • Bid document price: 300.00 (ሶስት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Aug 17, 2026)
  • Posted at: 2026-08-18T09:11:28.000Z
← Back to all tenders