Accounting and Auditing, Accounting System Design
ግሬስ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃ/የተወሰነ መሰረታዊ ኅብረት ሥራ ማኅበር የ2017/2018 የበጀት ዓመት የሂሳብ እንቅስቃሴውን እና የፋይናስ ሰነዶቹን በሕጋዊ እና በውጪ የተመሰከረለት የኦዲት ድርጅት /External Audit firm/ ለማስመርመር ይፈልጋል
Description
የኦዲት አገልግሎት የጨረታ ማስታወቂያ
የድርጅቱ ስም፡ ግሬስ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃ/የተወሰነ መሰረታዊ ኅብረት ሥራ ማኅበር
የማስታወቂያ ቀን፡ 08/12/2018
የጨረታ ቁጥር፡ 003
መግቢያ
ግሬስ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃ/የተወሰነ መሰረታዊ ኅ/ሥ/ማኅበር የ2017/2018 የበጀት ዓመት የሂሳብ እንቅስቃሴውን እና የፋይናስ ሰነዶቹን በሕጋዊ እና በውጪ የተመሰከረለት የኦዲት ድርጅት External Audit firm/ ለማስመርመር ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም በዘርፉ የተሰማሩ እና መስፈርቱን የሚያሟሉ የኦዲት ድርጅቶችን በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡
ተወዳዳሪዎች ማሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች
- የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለው/ላት፣
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር TIN Certificate ያለው/ላት፣
- የቫት ምዝገባ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችል/ምትችል፣
- የሂሳብና ኦዲት ቦርድ AABE የምዝገባ ሰርተፊኬት ያለው/ላት
- የዘመኑን ግብር የከፈለ እና ከግብር ሰብሳቢ አካል የታደሰ የግብር ክሊራንስ ማቅረብ የሚችል /ምትችል፣
- ተመሳሳይ የስራ ልምድ ያላቸው እና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
አመላለስ እና የማስገቢያ ጊዜ
- የሰነድ ማቅረቢያ ቦታ፡ ከአያት አደባባይ ወደ ጎሮ በሚወስደው መንገድ ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ፊትለፊት ሃላል ሕንጻ 3ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የማኅበሩ ዋና ጽ/ቤት
- የጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት፡ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቅዳሜን ጨምሮ በ5 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ እስከ 13/12/2018 ጠዋት 5፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ይሆናል፡፡
- ጨረታው የሚከፈትበት ጊዜ፡ በ14/12/2018 ከሰዓት 7፡30 ላይ ተወዳዳሪዎች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በማኅበሩ ጽ/ቤት ይከፈታል፡፡
ማሳሰቢያ
- ኅ/ሥ/ማኅበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለበለጠ መረጃ፡ በ09-72-88-77-77 በስራ ሰዓት ይደውሉ፡፡
መልካም ዕድል
ግሬስ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃ/የተወሰነ
መሰረታዊ ኅብረት ሥራ ማኅበር
Tender details
- Deadline: 2026-08-21
- Bid closing time: 11:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቅዳሜን ጨምሮ በ5 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ እስከ 13/12/2018 ጠዋት 5፡00 ሰዓት ድረስ
- Bid opening: 2026-08-22 13:30
- Bid opening (note): በ14/12/2018 ከሰዓት 7፡30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: ግሬስ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃ/የተወሰነ መሰረታዊ ኅብረት ሥራ ማኅበር
- Published on: Addis Zemen (Aug 17, 2026)
- Posted at: 2026-08-18T11:09:05.000Z